የጃዊ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ለሁለተኛ ጊዜ በእሳት ተቃጠለ

ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በመገንባት ላይ ያለው እና ከመጠናቀቂያ ጊዜው ለአንድ አመት ያክል የዘገየው የስኳር ፋብሪካ ንብረት የሆነ 60 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ሙሉ በሙሉ በእሳት ጋይቷል። ድርጊቱን ማን እንደፈጸመው በስም ያልጠቀሱዋቸው አካላት እያጣሩት ነው ሲሉ፣ የጠቀሱት የፋብሪካው ሃላፊ አቶ ባይነሳኝ፣ ጥናቱ ሳያልቅ መንስኤውን ይፋ ማድረግ አይቻልም ይላሉ። ሌሎች ወገኖች ደግሞ ድርጊቱ ...

Read More »

በሳኡዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ሊያደርግ ነው

ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር በሚል ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2009 ዓም ይካሄዳል። ጥሪውን ያስተላለፈው በአገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሲሆን፣ ዘመዶቻቸው በግፍ የተገደሉባቸውም ሆኑ አገዛዙን የሚቃወሙት ሁሉ በኢምባሲው ተገኝተው ተቃውሞአቸውን እንዲያሰሙ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።

Read More »

አሜሪካውያን ወደኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳሰቢያ አወጣ

ኢሳት (ኅዳር 28 ፥ 2009) የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሃገሪቱ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ በድጋሚ ማሳሰቢያን አወጣ። ባለፈው አመት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ፖለቲካዊ ውጥረትና አለመረጋጋት ማስፈኑን ያስታወቀው የአሜሪካ መንግስት፣ አሜሪካዊያን ችግሩ ዕልባት ወደአላገኘባት ኢትዮጵያ ቢጓዙ የደህንነት ስጋት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል አሳስቧል። ዜጎቹ ወደ ሃገሪቱ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ተጥሎ ያለው ...

Read More »

ሰላም ባስ በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የ8.5 ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 28 ፥ 2009) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የ8.5 ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገለጸ። በጎንደር በተነሳውና በአማራ ክልል ከተስፋፋው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የደረሰበትን ኪሳራ ይፋ አላደረገም። አዲስ ፎርቹን ሳምንታዊ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ሰላም ባስን በመጥቀስ ባቀረበው ዘገባ እንደተመለከተው ባለፈው አመት ወደ ነቀምትና አሶሳ የሚያደርገው ጉዞ በመስተጓጎሉ 650 ምልልሶች ተሰርዘዋል። በዚህም የ8.5 ሚሊዮን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብር ከዶላር ጋር ያለው የመግዛት አቅም ማስተካከያ እንዲደረግበት የአለም ባንክ ጠየቀ

ኢሳት (ኅዳር 28 ፥ 2009) የአለም ባንክ ኢትዮጵያ አጋጥሟት ያለውን የውጭ ንግድ ገቢ ለማነቃቃት የሃገሪቱ መገበያያ ገንዘብ የሆነው ብር ከዶላር ጋር ያለው የመግዛት አቅም ማስተካከያ እንዲደረግበት አሳሰበ። ባንኩ ከአምስት አመት በፊት ያቀረበውን ተመሳሳይ ሃሳብ ተከትሎ ብር ከዶላር ጋር ያለው የመግዛት አቅም በ15 በመቶ አካባቢ እንዲቀንስ መደረጉ ይታወሳል። ከአምስት አመት በፊት ሁለተኛ ዙር ማስተካከያ በብር ላይ እንዲደረገ ያሳሰበው የአለም ባንክ እየተዳከመ ...

Read More »

የአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ የሰብዓዊ መብት እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ዙሪያ ሊወያዩ ነው

ኢሳት (ኅዳር 28 ፥ 2009) በአፍሪካ አሳሳቢ እየሆኑ በመጡ የሰብዓዊ መብት እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ዙሪያ  የአህጉሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች በአዲስ አበባ ሊሰባሰቡ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ረቡዕ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ ውጥረት ተደጋጋሚ መግለጫን ሲያወጣ የቆየው ህብረቱ አባል ሃገራቱ በአፍሪካ የሰብዓዊ መብት የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ለሁለት ቀን እንደሚመክሩ ገልጿል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ተደርጎበት በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ሃሙስና ...

Read More »

የጋምቢያው ፕሬዚደንት ያ’ህያ ጀምህ ክስ ሊመሰርትባቸው ነው ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 28 ፥ 2009) በቅርቡ በጋምቢያ በተካሄደ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በተቃዋሚ ፓርት እጩ የተሸነፉት የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ክስ ሊመሰርትባቸው መሆኑ ተገለጸ። ከ20 አመት በላይ በስልጣን ቆይተው የነበሩት ተሸናፊው ፕሬዚደንት ያ’ህያ ጃምህ በስልጣን ጊዜያቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣን ሲፈጽሙ እንደነበር በተለያዩ አካላት ሲገለጽ ቆይቷል። አዲሱ የጋምቢያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ፕሬዚደንቱ በፈጸማቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊከሰሱ በመሆኑ ከጋምቢያ እንዳይወጡ ትዕዛዝ መተላለፉን ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ውጊያው ቀጥሎአል በርካታ ቤቶችም ተቃጥለዋል

ኅዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር በነጻነት ሃይሎች እና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ውጊያ እንደቀጠለ ሲሆን፣ ያልጠበቀው ጉዳት የደረሰበት አገዛዙ የአርሶአደሮችን ቤቶችን በማቃጠል የበቀል እርምጃ እየወሰደ ነው። በወገራ ወረዳ በእንቃሽ ከትናንት በስቲያ ከ10 በላይ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን፣ ዛሬ ማክሰኞ ደግሞ በጃኖራ አቶ መስፍን የተባሉ ታጋይ ሁለት ቤቶቻቸው የተቃጠሉባቸው ሲሆን፣ ከጠዋት እስካሁን የተኩስ ለውውጥ እየተካሄደ ነው። ...

Read More »

የኢትዮጵያ ገቢ ንግድ ከወጪ ንግድ ገቢ ያለው ልዩነት እየጨመረ መምጣቱ የአለም ባንክ አስታወቀ

ኢሳት (ኅዳር 27 ፥ 2009) የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ገቢ ንግድ ከወጪ ንግድ ገቢ ያለው ልዩነት እየጨመረ መምጣቱንና ከ10 በመቶ በላይ መድረሱን ማክሰኞ ይፋ አደረገ። በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዙሪያ አምስተኛ ሪፖርትን ያወጣው ባንኩ የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድ አለመመጣጠን በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ  ማሳደሩን ገልጿል። የኢትዮጵያ የስራ አጥ ችግርም ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ሲነጻጸት በመጠን ከፍተኛ መሆኑን የባንኩ ሪፖርት አመልክቷል። ባለፉት ጥቂት ...

Read More »

በየመን በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደህንነታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁ ተገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 27 ፥ 2009) በየመን እየተካሄደ ካለው የእርስ በርስ ጦርነት መውጫን አጥተው የሚገኙ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ደህንነታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን የአለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት (IOM) ማክሰኞች አስታወቀ። ድርጅቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመታደግ የህይወት አድን ዘመቻ በቅርቡ ቢጀምርም በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከየመን ለመውጣት የሚፈልጉ ስደተኞችን ማውጣት እንዳልቻለ ገልጸዋል። ይሁንና ባለፈው ወር ብቻ የስደተኞቹ ተቋም 150 ኢትዮጵያውያንን ከየመን ማስወጣት ...

Read More »