ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል አዊ ዞን ከአገዛዙ ጋር የሚፋለሙ የነጻነት ሃይሎችን ለመውጋት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እየተንቀሳቀሰ ነው። የአይን እማኖች እንደገለጹት ትናንት በጃዊ አድርጎ አንድ ታንክ በሎቤድ ተጭኖ ተዋጊዎቹ ይገኙበታል ተብሎ ወደ ሚገመተው ሱዋታ ወይም አይማ ተንቀሳቅሷል። አይማ በደቡብ ምእራብ ቋራና ሰሜን ጃዊ ወረዳ የሚገኝ ቦታ ሲሆን፣ ከታንኩ ጋር በርጃታ የአገዚ ወታደሮች ወደ አካባቢው ...
Read More »የደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን ገለጹ
ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ የብሄር ብሄረሰቦችን በአል ለማክበር በሚል በዩኒቨርስቲው በተጠራ ዝግጅት ላይ ተማሪዎች ጩትና ተቃውሞ እያሰሙ ከአዳራሹ ሲወጡ፣ መምህራን ደግሞ በቀረበው የመወያያ ጽሁፍ ላይ ምንም ሳይናገሩ በዝምታ ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ዝግጅቱ ተዘግቷል። ምሳ ሰአት አካባቢ ተማሪዎች ውሸት በቃን ፣ አጋዚ ግቢያችን አይግባ፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይመስረት፣ መብታችን ይከበር በማለት ከ1 ሰአት በላይ ግቢያቸውን እየዞሩ አገዛዙን ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ ያለበትን አድራሻ ማወቅ አለመቻላቸውን ቤተሰቦቹ ገለጹ
ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ይገኝ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ ቤተሰቦቹ ወደታሰረበት ዝዋይ እስር ቢሄዱም ሊገኙት አልቻሉም። በሳምንት ሁለት ቀናት ሀሙስ እና እሁድ በቤተሰቦቹ ብቻ እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ጋዜጠኛ ተመስጌን ፣ ከህዳር 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኋላ ግን ሊጎበኙት የሄዱት ቤተሰቦቹ ሊያገኙት አልቻሉም። ቤተሰቦቹ መግባት እንደማይችሉ በጥበቃ ሰራተኞች የተነገራቸው ሲሆን፣ አድራሻውን ለማወቅ ወደ ቂሊንጦ ...
Read More »የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ አረፉ
ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደርግ ስርዓት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት እና ጠቅላይ ሚንስርነት ሆነው ያገለገሉት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ያዴሳ በተወለዱ በ77 ዓመታቸው ህዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በ1932 ዓ.ም በቀድሞው ሸዋ ክ/ሃገር አንቦ ከተማ ውስጥ የተወለዱት አቶ ተስፋየ ፣ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አንቦ በሚገኘው ማዕረገ ሕይወት ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ትምህርት ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ...
Read More »በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ የምትገኘው የጋፍጋዱድ ከተማ በታጣቂ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) በቅርቡ የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ መጠነ ሰፊ ውጊያ ያካሄዱበትና በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ የሚገኘው የጎፍጋዱድ ከተማ በታጣቂ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ። በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሚገኙበት የባይደዋ ከተማ በ35 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኘው በዚህ ስፍራ ባለፈው ወር ውጊያ ተካሄዶ የጎፍ ጋዱድ ከተማ በመንግስት እጅ ገብቶ እንደንበር ሸበሌ ሬዲዮ ዘግቧል። ይሁና ከቀናት በፊት በአካባቢው ጥቃትን ...
Read More »የእስራዔል መንግስት በሃገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደም እንዳይለግሱ ጥሎ የቆየውን እገዳ አነሳሁ አለ
ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) የእስራዔል መንግስት በሃገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደም እንዳይለግሱ ጥሎ የቆየውን እገዳ አነሳ። የእስራዔል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሃገሪቱ ውጭ የተወለዱ ወይም የHIV/AIDS ስርጭት ባለባቸው ሃገራት ለአንድ አመት ያህል ቆይታ ያደረጉ ቤት-እስራዔላዊያን ደም እንዳይለግሱ ከ10 አመት በፊት እገዳ መጣሉ ይታወሳል። ይሁንና የእስራዔል መንግስት ጥሎ የነበረው እገዳ በአግባቡ ለህዝብ ይፋ ባልተደረገበት ወቅት ማሪቭ (maiariv) የተሰኘ የሃገር ጋዜጣ ከኢትዮጵያውያን ይወሰድ ...
Read More »በኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸውን ህጻናት ህይወት ለመታደግ አለም አቀፍ የዕርዳታ ማሰባሰብ ስራ ተጀመረ
ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ምክንያት የከፋ የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ህጻናት ህይወት ለመታደግ አለም አቀፍ የዕርዳታ ተቋማት የአምስት አመት ዘመቻን ጀመሩ። በመንግስትና በ11 የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች የሚካሄደው ይኸው ዘመቻ 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት ሲሆን፣ ዘመቻው በከፋ የምግብ እጥረት ምክንያት የአካል መመናመን እየደረሰባቸው ያሉ ህጻናትና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑ ታውቋል። በአማራ ክልል 46 በመቶ ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ቤት አለመኖሩ ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) በዝዋይ እስር ቤት በእስር ላይ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ቤቱ አለመኖሩንና ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ የጋዜጠኛውን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት ለኢሳት ገለጹ። የጋዜጠኛው ቤተሰቦች በበኩላቸው የማህበራዊ ድረገጾች ባሰራጩት መረጃ ዝዋይ እስር ቤት ተመስገንን ለመጠየቅ ሁለት ቀን ቢሄዱም፣ በእስር ቤቱ ተመስገን የሚባል የመንግስት እስረኛ አናውቅም የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው አረጋግጠዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማፈላለግ ላይ ያሉ የቤተሰቡ አባላት ...
Read More »የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በደርግ ኢህድሪ መንግስት ውስጥ በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉትና በመጨረሻ ለከፍተኛው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስፍራ የበቁት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ያረፉት በስደት በሚገኙበት በዩ ኤስ አሜሪካ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የህይወት ታሪካቸው እንደሚያስረዳው የዛሬ 77 አመት በምዕራብ ኢትዮጵያ አምቦ አቅራቢያ የተወለዱት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ...
Read More »46 ወታደሮች እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው አርበኞች ግንቦት7ትን ተቀላቀሉ
ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት7 የኢትዮጵያ ክፍል ወኪሎች ለኢሳት እንደገለጹት ከረጅም ጊዜ ድርድር በሁዋላ 46 ወታደሮች የተለያዩ መሳሪያዎችን ይዘው ተቀላቅለዋል። ወታደሮቹ ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር ተቀላቅለው በስልጣን ላይ ያለውን ሃይል ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን የግንባሩ የአመራር አባል ገልጸዋል። ወታደሮቹ 9 መትረጊስ፣ 6 ስናይፐር፣ሁለት ዲሽቃና አንድ አርፒጂ መያዛቸውን አመራሩ ተናግረዋል። “ወታደሮቹ ግንባሩን የተቀላቀሉት ኤርትራ ነው ወይ ተብሎ ...
Read More »