የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ስጋት ማሳደሩ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ያለው አለመረጋጋትና ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ስጋት ማሳደሩ ተገለጸ። በተለይ አየር መንገዱ በአንጎላ እና ናይጀሪያ ሃገራት ያለው ሰፊ የጉዞ እንዲሁም የትኬት ሽያጭ ገበያ ባለፉት በርካታ ወራቶች መቀዛዝቅዝ ማሳየቱን ብሉምበርግ የተለያዩ መርጃዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ለንባብ አብቅቷል። በእነዚሁ ሁለት ሃገራት ብቻ ከትኬት ሽያጭ ከ200 ሚሊዮን ዶላር ...

Read More »

አሜሪካ አንድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መወሰኗን ይፋ አደረገች

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ስጋቷን ስትገልጽ የቆየችው አሜሪካ አንድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መወሰኗን ሰኞ ይፋ አደረገች። የዴሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከረቡዕ ጀመሮ በአዲስ አበባ የአራት ቀን ጉብኝት እንደሚያደርግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የአራት ቀን ቆይታ የሚኖራቸው ቶም ...

Read More »

ህወሃት ዶ/ር መረራን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን በአስቸኳይ እንዲፈታ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) መራሹ አገዛዝ ሃገርን ከጥፋት ለመታደግ ዶ/ር መረራ ጉዲናንም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን በአስቸኳይ እንዲፈታ የኢትዮጵያ ሃገራትዊ ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የፖለቲካ ሜዳውን ክፍት በማድረግ ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉበትን አገር አቀፍ ጉባዔ እንዲካሄድ ሁነታዎችን ማመቻቸት አለበት። ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት ሰባትንና የኦርሞ ነጻነት ግንባርን (ኦነግን) ተቀላቅለዋል የተባሉ አምስት ወታደሮችና ግለሰቦች ተከሰሱ

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) የአገር መከላከያ ሰራዊትን በመክዳት አርበኞች ግንቦት ሰባትና የኦርሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግን) ተቀላቅለዋል የተባሉ አምስት ወታደሮችና ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው። የአየር ሃይል የደህንነት ሃላፊን ለመግደል በደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ሲሰሩ እንደነበርም ተመልክቷል። የፌዴራል አቃቤ ህግ የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ያቀረበባቸው እነዚሁ ተከሳሾች ሁለቱ የአገር መከላከልያ ሚኒስቴር አባላት የነበሩ ሶስቱ ደግሞ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና ኦነግ አባላት መሆናቸው በሃገር ውስት ያሉ ...

Read More »

በጋምቢያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተሸነፉት ያህያ ጃምህ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም ማለታቸውን ተከትሎ በአገሪቱ ውጥረት መንገሱ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) የጋምቢያው ፕሬዚዳንት የምርጫ ሽንፈታቸውን የተቀበሉበት ብሄራዊ ምርጫ በድጋሚ እንዲካሄድ ያቀረቡ አዲስ ሃሳብ በሃገሪቱ ውጥረት ማንገሱ ተገለጸ። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የጋምቢያው ፕሬዚደንት ያህያ ጃምህ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን እንዲያደርጉ ቢያሳስቡም በ24 ሰዓት ውስጥ ቃላቸውን የቀየሩት ፕሬዚደንቱ የምርጫው ግድፈት ነበረው በማለት ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ጠይቀዋል። ይሁንና በ22 አመት የስልጣን ዘመናቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲፈጸሙ የሚነገርላቸው ፕሬዚደንት ያህያ ከእሁድ ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት በሰሜን ጎንዳር አካባቢዎች ያወጣው የጉዞ ጥንቃቄ ቀጣይ እንዲሆን ወሰነ

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) በቅርቡ በሰሜን ጎንዳር አካባቢዎች በመንግስትና በአርበኞች ግንቦት ሰባት መካከል ሲካሄድ የቆየ ውጊያ ተከትሎ የጉዞ ማሳሰቢያን አውጥቶ የነበረው የብሪታኒያ መንግስት ማሳሰቢያው ቀጣይ እንዲሆን ሰኞ በድጋሚ ወሰነ። ለሃገሪቱ ዜጎች ማሳሰቢያን ያሰራጨው የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጸገዴ፣ በምዕራብና ታች አርማጭሆ የሰሜን ጎንደር ስፍራዎች አስፈላጊ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዳይደረጉ በመግለጫው አመልክቷል። ከብሪታኒያ መንግስት በተጨማሪ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የሚደረጉ ውጊያዎችን በገዢው ፓርቲ በኩል ሆነው ሲመሩ የቆዩት የዞኑ የልዩ ሃይል አዛዥ ኮማንደር ዋኘው አዘዘው መታሰራቸውን ምንጮች ገልጹ።

ታኅሣሥስ ፫ (ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮማንደሩ ትናንት ምሽት ተይዘው ፣ በወታደራዊ እዙ (ኮማንድ ፖስት) የሚታሰሩ ሰዎች ወደ ሚገኙበት ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል። ኮማንደሩ ጦራቸውን ይዘው ተሰውረዋል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘገብ ቆይቷል። የኮማንደር ዋኘው ደጋፊዎችንና በእሱ ስር ያሉ ወታደሮችን ለመያዝ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ምንጮች ገልጸዋል። እርምጃው በህወሃት በሚመራው ወታደራዊ እዝ ( ኮማንድ ፖስት) እና በክልሉ ልዩ ሃይል መካከል ያለውን ...

Read More »

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መደንገጉን ተከትሎ በየቀኑ  በኦሮሚያ ክልል  በወጣቶችና ምሁራን ላይ ዘግናኝ የሆነ ስቃይ ሲፈጸም መቆዬቱን  የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ አጋለጠ።

ታኅሣሥስ ፫ (ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰብዓዊ መብት ሊጉ” ስድሳ እኩይ ቀናት በኦሮሚያ”በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ  መደንገጉን ተከትሎ  ባለፉት ስድሳ ቀናት እጅግ በርካታ  የኦሮሞ ወጣቶች፣  የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሁራን ላይ ያነጣጠረ  አፈናና ጥቃት ሲፈጸም መቆዬቱን አመልክቷል። የህወኃት ኢሃዴግ አገዛዝ በሰብዓዊ ነት ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ በሪፖርተሮቹ አማካይነት ሲያጠናቅር መቆዬቱን የጠቀሰው የሰብ ዓዊ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች እና ኢንሹራንሶች፣ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸውን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአክሲዩን ድርሻቸውን እንዲያስወጡ መመሪያ ተላለፈ፡፡

ታኅሣሥስ ፫ (ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መመሪያውን ተከትለው ሁሉም የባንክና የኢንሹራንስ ድርጅቶች ማስታወቂያ በማውጣት ደንበኞቻቸውን እያሰናበቱ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር FIS/01/2016 ባወጣው መመሪያ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 5.1 እና 5.2 መሰረት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ አገርዜግነት ያላቸው የባንክ ወይም ኢንሹራንስ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች ከህዳር 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 60 ቀናት ውስጥ ዋናውን የአክሲዮን የምስክር ወረቀታቸውን እንዲሁም ...

Read More »

በጃኖራ ቀበሌ የሚካሄደው ውጊያ ቀጥሎአል

ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ዛሬ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ታጋዮች የያዙትን ምሽግ ሰብሮ መግባት ያልቻለው የአገዛዙ ጦር፣ ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ከጦር ግንባሩ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአካባቢው በብዛት የሰፈሩት ወታደሮች ሞርታርና ዲሽቃ እየተኮሱ አካባቢውን ሲደበድቡ ውለዋል። የግንባሩን ቃል አቀባይ በቀጥታ ለማግኘት ...

Read More »