ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ11 አመታት በፖሊስነት ያገለገሉት አቶ ግርማ ፣ ከ1987 ዓም ወዲህ ስራቸውን በመልቀቅ በዲዛይነር ስራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል። አቶ ግርማ የኢትዮጵያን ባንዲራ በተለያዩ ዲዛይኖች እየሰሩ መሸጣቸውና ወደ ውጪ መላካቸው ወንጀል ሆኖ ተቆጥሮባቸዋል። ባለፉት ወራት የተከሰተውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የታሰሩት አቶ ግርማ፤ ፍርድ ቤት እስከቀረቡበት እስከዛሬ ማክሰኞ ድረስ “እኔ ነኝ ያሳሰርኳቸው” የሚል አካል ...
Read More »የብሪታንያ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሰራጩ የሙዚቃና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ያጸደቀው 5 ሚሊዮን ፖውንድ ተቃውሞ ገጠመው
ኢሳት (ታህሳስ 10 ፥ 2009) የብሪታንያ መንግስት በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተቋማት ለሚካሄዱ/ለሚሰራጩ የሙዚቃና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ድጋፍ ያጸደቀው 5 ሚሊዮን ፖውንድ በሃገሪቱ ባለስልጣናት ዘንድ ተቃውሞን ቀሰቀሰ። የሃገሪቱ መንግስት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ “የኛ” በሚሰኙ አባላት ዘንድ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የማህበራዊ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ናቸው በማለት ከጥቂት አመታት በፊት ድጋፍ መስጠት መጀመሩን ዴይሊ ሜይል የተሰኘ የብሪታኒያ ጋዜጣ ዘግቧል። ይህንኑ የሙዚቃና ድራማዊ ፕሮግራሞ ለቀጣዩ ሁለት ...
Read More »በሱዳን ከቤት ያለመውጣት ተቃውሞ ተጀመረ
ኢሳት (ታህሳስ 10 ፥ 2009) የሱዳን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በሃገሪቱ ተፈጥሯል ያሉትን ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት በመቃወም ከቤት ያለመውጣት ተቃውሞን ትናንት ዕሁድ ጀመሩ። የፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር መንግስት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የቆየውን ድጎማ ካነሳ በኋላ በሱዳን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መፈጠሩን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይሁንና የተፈጠረውን ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት መቃወም የጀመሩት ሱዳናዊያን በሃገሪቱ ባለው የሰብዓዊ መብት ዙሪያ ተመሳሳይ ቅሬታን ማቅረብ እንደጀመሩ ታውቋል። የሱዳን የሰብዓዊ ...
Read More »ኬንያ በኢትዮጵያ በእስር ላይ እንዳለ ህይወቱ ያለፈ ዜጋዋን ጉዳይ ምርመራ እንዲካሄድበት ይፋዊ ጥያቄን አቀረበች
ኢሳት (ታህሳስ 10 ፥ 2009) ኬንያ በኢትዮጵያ በእስር ላይ እንዳለ ህይወቱ ያለፈ ዜጋውን ጉዳይ ምርመራ እንዲካሄድበት ይፋዊ ጥያቄን አቀረበች። የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የነበረው ዛካዬ ሙሪኪ ለአንድ አመት ያህል ጊዜ በእስር ቤት ከቆየ በኋላ ባለፈው ሳምንት ህይወቱ ማለፉንና አስከሬኑ ወደ ኬንያ መጓጓዙን መዘገባችን ይታወሳል። የሟቹ አስከሬን ወደ ሃገሪቱ መጓዙን ተከትሎም የኬንያ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ አካላት በድርጊቱ ቁጣቸውን ሲገልጹ መሰንበታቸውን ዴይሊ ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሺ መበለጡ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 10 ፥ 2009) ከአስቸኳይ አዋጁ ተግባራዊ መደረግ በኋላ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ20ሺ መብለጡ ተገለጸ። ከመካከላቸው 20 ያህል የጸጥታ ሰራተኞች እንደሚገኙበት መንግስት አስታውቋል። ለእስር የሚደረጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ ከወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት በተጨማሪ የተለያዩ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለጊዜያዊ እስር ቤት እየዋሉ መሆኑንም ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ...
Read More »ግብፅ የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት የአባይ ግድብ ፕሮጄክትን በመጎብኘታቸው ተቃውሞን አሰማች
ኢሳት (ታህሳስ 10 ፥ 2009) የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ ባለስልጣናት የአባይ ግድብ ፕሮጄክት መጎብኘታቸውን ተከትሎ ግብፅ ድርጊቱ “አደገኛ” ነው ስትል ተቃውሞን አቀረበች። የሳውዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን አማካሪ የሆኑት አህመድ አል-ካቲብ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያን ግንኙነት በሚጠናክረበት ዙሪያ በአዲስ አበባ ጉብኝንትን ማድረጋቸው ይታወሳል። በሃገሪቱ የሶስት ቀን ቆይታ የነበራቸው አል-ካቲብ በአባይ ግድብ ያልተጠበቀና ቀድሞ ባልተያዘ ፕሮግራም ጉብኝት ማድረጋቸውን የግብፅ ባለስልጣናት ለመገናኛ ...
Read More »ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጋር በተያያዘ በጎንደር አንገረብ እስር ቤት ውጥረቱ ቀጥሎአል
ታኅሣሥ ፲ (አሥር)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮ/ል ዶመቀ ዘውዴን ከጎንደር አውጥቶ ለመውሰድ ከሚደረግ ሙከራ ጋር በተያያዘ በእስር ቤቱ ውስጥ በተነሳ ተቃውሞ 1 እስረኛ ሲገደል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ እስረኞች ደግሞ ቆስለዋል። አንዳንድ ወገኖች የሟች እስረኞች ቁጥር 3 ነው ይላሉ። ኮ/ል ደመቀን ከሌሎች እስረኞች ለይቶ በማውጣት በአንድ ክፍል ውስጥ ለማስቀመጥ የተደረገውን ሙከራ ኮሎኔሉም ሆኑ እስረኞች የተቃወሙት ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ ተኩስ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ለሽማግሌዎች ማስጠንቀቂያ ሰጡ
ታኅሣሥ ፲ (አሥር)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ከአምባጊዮርጊስ እስከ ደባት መሽገው የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች እጃቸውን እንዲሰጡ አግባቡልን” በማለት የህወሃት/ኢህአዴግ ካድሬዎች በ31 ቀበሌዎች ስብሰባ አድርገው በእያንዳንዱ ቀበሌ 30 ሽማግሌዎችን አስመርጠዋል ። ካድሬዎች፣” እኛ አንድ ሺ ወታደር ቢገደልብን ሌላ አንድ ሺ እናመጣለን፣ አንድ አርሶአደር ቢገድል ግን አይተካም” የሚል ቅስቀሳ የጀመሩ ሲሆን፣ የነጻነት ታጋዮቹ በበኩላቸው፣ ማንኛውም ሽማግሌ፣ የሃይማኖት አባትም ሆነ ሌላ ግለሰብ፣ ...
Read More »ሁለት የነጻነት ታጋዮች አራት ወታደሮችን ገድለው ተሰው
ታኅሣሥ ፲ (አሥር)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በኮሚቴ አባልነት ተመርጦ ሲንቀሳቀስ እና የነጻነት ተጋድሎ ሲያደርግ የነበረው አቶ ዘውዱ ገ/እግዚአብሄርና ሌላው ጓደኛው አቶ ሙላው ከበደ ታህሳስ 9 ቀን 2009 ዓም መተማ ቁጥር 2 በሚባለው አካባቢ እነሱን ለመያዝ ከመጡ ወታደሮች ጋር ተፋልመው 4 ወታደሮችን ገድለው ተሰውተዋል። ከኮርመር የተነሱት ወታደሮች፣ ታጋዮቹን በቀላሉ እንይዛለን ብለው ቢሄዱም ያልጠበቁት ...
Read More »ከኤርትራ ጋር በሚዋሰኑ ቦታዎች ተጨማሪ ራዳሮች እየተተከሉ ነው
ታኅሣሥ ፲ (አሥር)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ከኤርትራ ጋር በሚዋሰኑ ድንበሮች አካባቢ ዘመናዊ ካሜራዎችንና ራዳሮችን እያስተከለ ነው። በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች በቅርቡ ዘመናዊ ራዳሮችና የርቀት ካሜራዎች እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ ተገዝተው የተተከሉ ሲሆን፣ ትናንት እሁድ ደግሞ በአፋር ክልል በእንድፎና አዳይቱ በሚባሉ ከተሞች መሃል ላይ የራዳር ተከላው ሲከናወን ውሎአል። የሩሲያና ቻይና ስሪት የሆኑት መሳሪያዎች በሚሊዮን ...
Read More »