ኢሳት (ታህሳስ 13 ፥ 2009) የታዋቂው ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ የአቶ ተሾመ ገብረማሪያም የቀብር ስነ-ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ። በ86 አመታቸው ድንገት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው የተገለጸው አቶ ተሾመ ገብረማሪያም በአጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት በጠቅላይ አቃቤ-ህግነት እንዲሁም የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው አገልግለዋል። የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ሲወገድ ወደ እስር ቤት ከተጋዙት የመንግስት ባለስልጣናት አንዱ የነበሩት አቶ ተሾመ ገ/ማሪያም ለ8 ዓመታት በወህኔ ...
Read More »በግል ባንኮች ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ ሸጠው እንዲወጡ የተገደዱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከመሬት ጋር የተያያዘ መመሪያ እየተዘጋጀላቸው መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 13 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ ሸጠው እንዲወጡ የተገደዱት ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ከመሬት ጋር በተያያዘም ተጨማሪ መመሪያ እየተዘጋጀቸው መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በተሰጠ ልዩ መብት ቤት የሰሩ እንዳይሸጡ፣ ከእነርሱም የገዙ ስም እንዳያዛውሩ ዕገዳ መጣሉን መረዳት ተችሏል። ይህም ከቅርቡ መመሪያ ጋር የተያያዘ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። የውጭ ሃገር ዜግነት የያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተሰጣቸው ልዩ መብት ...
Read More »ከቱሪስት ዘርፍ የሚገኘው ገቢ መቀነስ እንዳሳሰበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ
ኢሳት (ታህሳስ 13 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉ የቱሪስቶች ቁጥር መቀነስና የሚገኘው ገቢ መሻሻል አለማሳየቱ ስጋት ማሳደሩን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ አለም አቀፍ ቱሪስቶች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መቀነሱ በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት የሚኒስቴሩ ባለስልጣናት ባለፉት ሶስት ወራት የጎብኚዎች ቁጥር እየቀነሰ በመሄድ ላይ መሆኑን ለሃገር ውስጥ መገኛኛ ...
Read More »በሽብርተኛ ወንጀል ክስ የሚመሰረትባቸው ጋዜጠኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን ሲፒጄ አስታወቀ
ኢሳት (ታህሳስ 13 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለእስር የሚዳረጉና የሽብርተኛ ወንጀል ክስ የሚመሰረትባቸው ጋዜጠኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣት አሳሳቢ መሆኑን አንድ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትላንት ረቡዕ በሁለት ጋዜጠኞች ላይ በሽብርተኛ ወንጀል ክስ ያስተላለፈው የጥፋተኝነት ብይን በኢትዮጵያ ያለውን የጋዜጠኞች አፈና አመላካች እንደሆነ ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ (ሲፒጄ) ገልጿል። በድርጅቱ ምክትል ሃላፊ ሮበርት ማሆኒ በጋዜጠኞች ካሊድ ...
Read More »የኢትዮጵያ የብድር ዕዳ መጠን በእጥፍ መጨመሩ ተነገረ
ኢሳት (ታህሳስ 12 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አጠቃላይ የብድር ዕዳ መጠን ባለፉት ሁለት አመታት በእጥፍ በመጨመር ከ23 በመቶ ወደ 55 በመቶ መድረሱ ተገለጸ። በሃገሪቱ ተመዝግቦ ያለው ይኸው የብድር መጠን ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ሆኖ የተቀመጠ ሲሆን፣ በሰብ-ሰሃራን አፍሪካ ሃገራት የእዳ መጠኑ በአማካኝ ከአመታዊ አጠቃላይ ምርታቸው እስከ 40 በመቶ የሚሸፍን መሆኑን የፋይናንስ ተቋማት መረጃ ያመለክታል። በተያዘው የፈረንጆች አመት ኢትዮጵያ ከተለያዩ ...
Read More »ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ መንግስት “ሽብርተኛ” ተብለው ከተፈረጁት አካላት ጋር አድርገውታል የተባለው መረጃ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 12 ፥ 2009) በቅርቡ ለእስር የተዳረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኛ ቡድን ከተፈረጁት አካላት ጋር አድርገውታል የተባለው መረጃ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን በቤልጅየም ብራሰልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምላሹን ሰጠ። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመራር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ ጉብኝታቸው በኋላ ለእስር የተዳረጉበት ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጠው የአውሮፓ ፓርላማ ጥያቄን አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል። ለዚሁ ጥያቄ ምላሽን የሰጠው ኤምባሲው የፓርቲው ...
Read More »በምስራቅ አፍሪካ ለምግብ እርዳታ ከተጋለጡት ግማሽ ያህሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 12 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ በጎረቤት ሶማሊያና ኬንያ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ከተጋለጡ ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። በቀጣዮቹ ሁለትና ሶስት ወራቶች በሃገሪቱ ያለው የድርቅ አደጋ እየተባባሰ ሊሄድ የሚችል በመሆኑን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባው ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስፍሯል። በተለይ በኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት ተከስቶ የነበረው የድርቅ አደጋ ዕልባት ሳያገኝ ...
Read More »በቆዳና ውጤቶች ምርት ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ አንድ የብሪታኒያ ኩባንያ ገቢው ክፉኛ መጎዳቱን ይፋ አድረገ
ኢሳት (ታህሳስ 12 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን በቆዳና በቆዳ ውጤቶች ምርት ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ አንድ የብሪታኒያ ኩባንያ በክልሉ ሲካሄድ በቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ በተያዘው በጀት አመት ገቢው ክፉኛ መጎዳቱን ረቡዕ ይፋ አድረገ። ፒታርድስ የተሰኘው ይኸው ግዙፍ ኩባንያ ያጋጠመውን የምርትና የትርፍ መቀነስ ተከትሎም የድርጅቱ የአክሲዮን ድርሻ በ14 በመቶ ማሽቆልቆሉን ድርጅቱ በድረ-ገጹ ላይ አስፍሯል። በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ በቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ...
Read More »የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 20 ተከሳሾችን በቀረበባቸው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ናቸው ሲል ብይን አስተላለፈ
ኢሳት (ታህሳስ 12 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ተከሳሾችን በቀረበባቸው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ናቸው ሲል ረቡዕ ብይን አስተላለፈ። የጥፋተኝነት ብይኑን የሰጠው ፍርድ ቤቱ በእነ ከድር ሞሃመድ የሱፍ ክስ መዝገብ የተለያዩ ክሶች ቀርቦባቸው በነበሩት ተከሳሾች ላይ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔን ለመስጠት ለቀጣዩ ሳምንት ቀጠሮ መያዙ ታውቋል። ከሁለት አመት በፊት ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት ተከሳሾች የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር የሚታየው ተቃውሞ ያሰጋው የኢህአዴግ መንግስት ሰራባ ላይ አዲስ ክፍለ ጦር ሊያቋቁም መሆኑ ተሰማ
ታኅሣሥ ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር የነጻነት ሃይሎች፣ አርሶአደሮችና የታጠቁ ሃይሎች በገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመሩን ተከትሎ፣ አገዛዙ ሰራባ ላይ 46ኛ ክፍለ ጦር ለማቋቋምና ሰራባን የጦር መሳልጠኛ ለማድረግ ማሰቡንም ምንጮች ገልጸዋል። ሰራባ የሚገነባው ክፍለጦር፣ አዘዞ ሎዛ ማሪያም ላይ ያለው 24ኛው ክፍለ ጦር ፈርሶ ይሁን ወይም ተጨማሪ አልታወቀም። በዞኑ ወታደራዊ ፍተሻው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ፍተሻው ...
Read More »