ኢሳት (ታህሳስ 14 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጨማሪ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ መሆኑንና አሁንም ድረስ በርካታ ሰዎች ለእስር በመዳረግ ላይ እንደሚገኙ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታወቀ። መንግስት በህዝባዊ ተቃውሞ ተሳትፈዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ከ20 ሺ በላይ ሰዎች መካከል ወደ 10 ሺ የሚጠጉትን መልቀቁ ጥሩ ዜና ቢሆንም፣ ለአዋጁ መውጣት ምክንያት የሆኑ የህዝብ ጥያቄዎች ግን ...
Read More »ተመድ በደቡብ ሱዳን ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣል በቀረበ ሃሳብ ላይ አርብ ድምፅ እንደሚሰጥ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 14 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣል በቀረበ ሃሳብ ላይ አርብ ድምፅ እንደሚሰጥ ተገለጸ። በአሜሪካ የቀረበው ይኸው ሃሳብ በፈረንሳይና በብሪታኒያ መንግስታት በኩል ድጋፍን ቢያገኝም በምክር ቤቱ ድምፅን በድምፅ የመጣል መብት ባላቸው ቻይንናና ሩሲያ በኩል ድጋፍን አያገኝም ተብሎ ተሰግቷል። አሜሪካ በሃገሪቱ ላይ እንዲጣል የምትፈልገው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በሃገሪቱ ያለውን ግጭት ዕልባት ...
Read More »በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሳማንታ ፖወር ለእስር የተዳረጉ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ታህሳስ 14 ፥ 2009) በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ሳማንታ ፖወር መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጥሪን አቅርበዋል። በሃገራቸው ለእስር የተዳረጉ እና በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የከፈተችውን ዘመቻ በማስተባበር ላይ የሚገኙ አምባሳደሯ ኢትዮጵያ ለእስር የዳረገቻቸውን የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት የሃገሪቱ ዜጎች በህገ መንግስቱ የተቀመጡ መብቶቻቸውን እንዲከበሩ አሳስበዋል። ዛሬ ሃሙስ ለእስር ከተዳረጉ አንደኛ አመት የሞላቸውን አቶ በቀለ ...
Read More »በሞዛምቢክ ኢትዮጵያውያን ሲጓዙበት የነበረ ተሽከርካሪ በመጋጨቱ በትንሹ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 14 ፥ 2009) ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት ላይ ነበሩ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ሲጓዙበት የነበረ ተሽከርካሪ የመጋጨት አደጋ አጋጥሞት በትንሹ ሰባት መሞታቸውን የሞዛምቢክ ባለስልጣናት አርብ አስታወቁ። ከአደጋው የተረፉ 34 ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ እየደረሰባቸው ካለ እንግለት ለመታደግ ሲባል የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ስደተኞቹ ሃሙስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓጓዙ ማድረጉ ታውቋል። ኢትዮጵያውያን ስተደኞቹ አምስት ወር የፈጀ ጉዞን አድርገው ሞዛምቢክ ከደረሱ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካ ...
Read More »ሴኔጋል የጋምቢያውን ፕሬዚደንት ከስልጣን ለማስወገድ ወታደሮቿን ወደ ሃገሪቱ ልታሰማራ ነው
ኢሳት (ታህሳስ 14 ፥ 2009) ሴኔጋል የጋምቢያው ፕሬዚደንትን በወታደራዊ ዕርምጃ ከስልጣን ለማስወገድ ወታደሮቿን ወደ ሃገሪቱ ልታሰማራ መሆኑ ተገለጸ። የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ተወካዮች ፕሬዚደንት ያህ’ያ ጃም’ህ የምርጫ ሽንፈታቸውን ተቀብለው ከስልጣን እንዲወርዱ ማግባባትን ቢያደርጉም፣ ፕሬዚደንቱ ለሃገራት ተወካዮች አሻፈረኝ ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በሃገሪቱ ተወካዮች ሲካሄድ የቆየው ድርድር ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎም የቀጠናው ሃገራት ሴኔጋል ወታደራዊ ዕርምጃውን እንድትወስድ ሃላፊነት መስጠታቸው ታውቋል። ሴኔጋል በበኩሏ ...
Read More »በአምቦ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከተማዋ ለሁለተኛ ቀን ውጥረት ሰፍኖባት ዋለ
ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትናንት ትምህርት በማቆም በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች እንዲፈቱ እንዲሁም በተማሪዎች ላይ ጉዳት ያደረሱት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሲጠይቁ ከዋሉ በሁዋላ፣ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ግቢው በመግባት በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመዋል። በርካታ ተማሪዎችንም ይዘው አስረዋል። ዛሬ ሃሙስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ወታደር ወደ ከተማዋ በማምራት ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ከቦ ያረፈደ ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም በደቡብ ኦሞ ባደረጉት ጉብኝት የዞኑ ፖሊሶች እንዳይገኙ ተደረገ
ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ – ታህሳስ 9/2009 ዓ.ም አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ፕሬዝዳንትና ከደህዲን አመራር አባላት ጋር በደቡብ ኦሞ የሚገኙትን የኩራዝ አንድና ሁለት የስኳር ፕሮጀክትና የጂንካን ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ መጎብኘታቸውንና በዚያው ቀን ተመልሰው አዲስ አበባ መሄዳቸውን የገለጹት ምንጮች፣ በዚህ ጉብኝታቸው የዞኑ ፖሊሶች እንዳይገኙ ተደርጓል። የአቶ ሃይለማርያም ጉብኝት በከፍተኛ ሚስጢር ተይዞ እንደነበርና ከደህንነቶች ...
Read More »የአፋሯ አርቲስትና አክቲቪስት ማፋራ መሀመድ ላሌ ተፈታች
ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከህዝባዊ አመጹ ጋር በተያያዘ ላለፉት ወራት ታስራ የቆየችው የአፋሯ አርቲስትና አክቲቪስት ማፋራ መሀመድ ላሌ ከትናትን በስቲያ ከእስር ተፈታች። በአውሮፓ የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ገአስ አህመድ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ከዱብቲ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተቃውሞ አስነስተሻል ተብላ ለወራት ለእስር የተዳረገችው አርቲስት ማፋራ የተፈታችው በዋስ ነው። ፍርድ ቤት በዋስ እንድትፈታ ሲወስን ...
Read More »የተወሰኑ መምህራን፣ ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ከእስር ተለቀቁ
ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ከመኖሪያ ቤታቸው ከስራ ገበታቸው እንዲሁም ከመንገድ ላይ እየተያዙ ከአንድ ወር በላይ በእስር ሲንገላቱ ከነበሩት ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መካከል የተወሰኑት ተፈተዋል። የዞን 9 አምደመረብ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ፣ የበይነ መረብ አምደኛው ስዩም ተሾመ፣ ወጣት ብሌን መስፍን፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ሰሎሞን ስዩም፣ መምህር አበበ አካሉ እና ወጣት እያስፔድ ተስፋዬ እና ሌሎችም ...
Read More »በኬንያ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
ኢሳት (ታህሳስ 13 ፥ 2009) የኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመንግስት ጋር በምርጫ ህግ ማሻሻያ ላይ ያደረጉት ውይይት መግባባት አለማምጣቱን ተከትሎ በሃገሪቱ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። ኬንያ በቀጣዩ አመት ፕሬዚደንታዊ ምርጫን የምታካሄድ ሲሆን፣ በተለይ በድምፅ ቆጠራ ሂደት ላይ የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲደረገ መንግስትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድርድር ሲያካሄዱ መሰንበታቸው ታውቋል። ይሁንና በሁለቱ የፓርላማ አባላት ዘንድ መግባባት ባልተደረሰበት ሁኔታ ገዥው የኬንያ ፓርቲ በፓርላማ ...
Read More »