መንግስት ከቱርኮች ጋር በሽርክና የከፈተው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ለጨረታ ቢቀርብም ገዢ አለመገኘቱ ተገለጠ

ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2009) መንግስት ከአንድ የቱርክ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ጋር በሽርክና ለመስራት የገባው ውል ትርፍ ሊያስገኝ ባለመቻሉ ፋብሪካው ለጨረታ ቀርቦ ገዢ ማጣቱ ተገለጠ። ሳይጊን ዲማ የተሰኘው ይኸው የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከአምስት አመት በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት ወደምርት ቢገባም ፋብሪካው የታሰበውን ያህል ገቢ ሊያስገኝ አለመቻሉን በሃገር ቤት ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ለሃገሪቱ ከፍተኛ ውጭ ምንዛሪ ያስገኛል ተብሎ ...

Read More »

አንድ የባህርዳር ነዋሪ በኮማንድ ፖስቱ አባላት በመኖሪያ ቤቱ ተገደለ

ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2009) በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆነ እስማዔል አህመድ የተባለ ኢትዮጵያዊ በወታደራዊ ዕዝ ወይም ኮማንድ ፖስቱ አባላት በመኖሪያ ቤቱ ደጃፍ ተገደለ። ከአራት ህጻናት ልጆቹና ከባለቤቱ ነጥለው ከመኖሪያ ቤቱ ካወጡት በኋላ ደጃፍ ላይ ገድለውት መሄዳቸውን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። መታወቂያ አሳይተው በመግባት ግድያውን የፈጸሙት የኮማንድ ፖስቱ አባላት፣ በቁጥር አራት መሆናቸውም ተመልክቷል። ኢስማዔል አህመት የተባለውና ነዋሪነቱ በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆነው ...

Read More »

“ኢህአዴግ ከወሰነ በሁዋላ ለህዝብ ውይይት እያለ የሚያቀርብበት መንገድ ድርጅቱን እየጎዳው ነው” ሲሉ አባለቱ ተናገሩ

ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የብአዴን/ኢህአዲግ አባላት ስብሰባ ፣ ፓርቲው በ”ጥልቅ ታድሻለሁ!” ካለ በኋላም እየሰራ ባላቸው ስራዎች ህዝብን ከማማከር ይልቅ በራሱ ወስኖ መፈጸሙን እንዲያቆም በአባላቱ ተጠይቋል። በአብዮታዊና ልማታዊ መስመር እራመዳለሁ የሚል መንግስት ከህዝብ ጋር የሚሰራውን ስራ ህዝብን በማማከር ማከናወን እንደሚገባው የገለጹት አባላት፤ብአዴን/ኢህአዴግ ለረዥም ጊዜ ከህዝብ ጋር ሲያጋጨው የኖረውን “እኔ አውቅልሃለሁ!” አሰራር አሁንም ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ የአቶ ዲንቃ ደያሳን ንብረት አገደ

ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮሞያ የሚካሄደውን ተቃውሞ ይደግፋሉ እንዲሁም  ለአባገዳዎች ግብዣ አድርገዋል የተባሉትና በአሁኑ ሰአት ውጭ በስደት የሚገኙት አቶ ዲንቃ ደያሳ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ኮሌጃቸው ጨምሮ ሶደሬ አካባቢ የሚገኘው መዝናኛ ክበባቸው  እንዲታገዱባቸው ተደርጓል። ሰደሬ አካባቢ ያለው መዝነኛ 76 ሚሊዮን ብር የታክስ እዳ አለበት በሚል ሰበብ እንዲዘጋ መደረጉንም ምንጮች ገልጸዋል። ሪፍት ቫሊ  የዛሬ 17 አመት በ1.3 ...

Read More »

በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት እየታየ ነው፡፡

ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ በርካታ የነዳጅ ማደያዎች የቤንዚንና ናፍጣ እጥረት መታየቱን ወኪላችን ዘግቧል፡፡ ወጣ ገባ በሚል ሁኔታ ሲከሰት የቆየው የነዳጅ አቅርቦት ከያዝነው ወር መጀመሪያ አንስቶ ከዕለት ወደ ዕለት እጥረቱ እየተባባሰ መሄዱን አሽከርካሪዎች ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡ ከአሁን በፊት የነዳጅ እጥረት የሚከሰተው በወሩ መጨረሻ ከታሪፍ ጋር በተያያዘ መልኩ የገቢዎች ሰራተኞች ከማደያ ባለንብረቶች ጋር ...

Read More »

በአዲስ አበባ ቤታቸው ይፈርስባቸዋል የተባሉት ነዋሪዎች ለመስተዳድሩ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ መስተዳደር በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በወረዳ 9፣ 10፣ 11፣ 12 እና 13 የሚገኙ ቤቶችን ለማፍረስ ማስታወቂያ ካወጣ በሁዋላ፣ በወረዳ 10 እሁድ ህዝቡ ለስብሰባ የተጠራ ሲሆን፣ በከፍተኛ የቁጣ ስሜት ውስጥ የነበረው ህዝብ “ እኛ የእናንተን ውሸት መስማት ሰልችቶናል፣ በቃችሁን፣ ቤታችንን አታፈርሱትም፣ ደጃፋችን ላይ እንሞታለን፣ ሂዱልን” በማለት ስብሰባው እንዲበተን ተደርጓል። ህዝቡም መስተዳድሩ ...

Read More »

በቻይና አለም አቀፍ የማራቶች ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያን ድል ተቀዳጁ

ኢሳት (ታህሳስ 24 ፥ 2009) ዕሁድ በቻይና በተካሄደ አለም አቀፍ የማራቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ጾታዎች ተከታትለው በመግባት ድል ተቀዳጁ። ከ30 ሺ በላይ ሰዎችና የተለያዩ ሃገራት አትሌቶች በተሳተፉበት በዚሁ የቤጂንግ የማራቶን ውድድር አትሌት ለሚ ብርሃኑ እና መሰረት መንግስቱ በአንደኝነት ማጠናቀቃቸውን የቻይና መገናኛ ብዙሃን ሰኞ ዘግበዋል። ባለፈው አመት በዚሁ በአሜሪካ ቦስተን ከተማ ተካሄዶ በነበረው የማራቶን ውድድር አሸናፊ የነበረው አትሌት ለሚ፣ በ 2 ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን መንግስት በስደት ከሚገኙ የሃገሪቱ ዜጎች ጋር የሰላም ውይይት ለማማከር የብሄራዊ የዕርቅ ልዑክ ሊልክ ነው

ኢሳት (ታህሳስ 24 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ በስደት ላይ የሚገኙ የሃገሪቱ ዜጎችን በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለማማከር የብሄራዊ የዕርቅ ልዑክ ወደ ጋምቤላ ክልል ለመላክ መወሰኑ ተገለጸ። በሪክ-ማቻር የሚመራው አማጺ ቡድን በበኩሉ የፕሬዚደንት ሳልባኪር መንግስት በደቡብ ሱዳን ዕርቅ ላማምጣት ነው በሚል የወጠነው ሃሳብ የአፍሪካ ህብረትንና ሌሎች አለም አቀፍ አካላትን ለማታለል የተወሰደ ዕርምጃ ነው ሲል ድርጊቱን አጣጥሎታል። የተለያዩ የህብረትሰብ ክፍል ተወካዮች ...

Read More »

የአትሌት ምሩፅ ይፍጠር የቀብር ስነስርዓት በመንበረ-ጸባዖት ቅድስት ስላሴ-ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጸመ

ኢሳት (ታህሳስ 24 ፥ 2009) የአንጋፋው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር የቀብር ስነስርዓት እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ በመንበረ-ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጸመ። የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ በርካታ የአትሌቱ ደጋፊዎችና ቤተሰቦች እንዲሁም መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ተወካዮች በቀብር ስነስርዓቱ መታደማቸው ታውቋል። ዕሁድ ከሰዓት በተፈጸመው በዚሁ የቀብር ስነስርዓት ወቅት ለአትሌቱ ክብር ሲባል ዘጠኝ ጊዜ መድፍ መተኮሱ ታውቋል።  በዚሁ ዝግጅት ሻምበል ምሩፅ ...

Read More »

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጦማሪያን ላይ የቀረበለትን የይግባኝ ጥያቄ ለመመልከት የተሟላ ማስረጃ እንዳልቀረበለት ገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 24 ፥ 2009) በነጻ በተሰናበቱ ጦማሪያን ላይ የቀረበለትን የይግባኝ ጥያቄ በመመልከት ላይ የሚገኘው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሟላ ማስረጃ እንዳልቀረበለት ገለጸ። በዚሁ ውሳኔ ለማሳለፍ መቸገሩን ገልጿል። በከሳሽ አቃቤ ህግ የቀረበለትን የይግባኝ ጥያቄ በመመልከት ላይ የሚገኘው ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ በታችኛው ፍርድ ቤት እንዳቅረባቸው በይግባኙ የገለጸው የሰነድና የሲዲ ማስረጃ ሊያገኝ አለመቻሉን እንዳስታወቀ ሪፖርተር አዲስ አበባ ላይ ዘግቧል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ...

Read More »