በርካታ የዶርዜ ብሄረሰብ ተወላጆች በሽብርተኝነት ተከሰሱ

ጥር ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የማንነት ጥያቄ አንስታችሁዋል በሚል ከ35 በላይ የዶርዜ ተወላጆች ላለፉት 2 ወራት በአርባምንጭ እና በጨንጫ  እስር ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። የዶርዜ ተወላጆች በአካባቢያችን ልማት የለም፣ መብታችንም አይከበርም በማለት ጥያቄያቸውን ከጠ/ሚኒስትሩ እስከ ፌደሬሼን ምክር ቤት አቅርበዋል። ዋና ዋና የሚባሉት የዶርዜ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች እየተፈለጉ በመታሰር ላይ መሆናቸውም ታውቋል። የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው እነዚህ ...

Read More »

ያለፈው የፈረንጆች ዓመት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ቀውስ ውስጥ የገባችበት አመት እንደነበር ሰየብአዊ መብት ድርጅቱ አስታወቀ

ጥር ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሂውማን ራይትስ ወች የአለምን የሰብአዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ባለፈው የፈረንጆች አመት በኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውንና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መታሰራቸውን ገልጿል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ  የተነሳ ዜጎች መብታቸው መገደቡ ብቻ ሳይሆን፣ አሁንም ድረስ ለቀጠለው አፈና ተዳርገዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈናን መፍቀዱ ብቻ ሳይሆን፣ ዜጎች ማህበራዊ የመገናኛ መንገዶችን እንዳይጠቀሙና ከውጭ አገራት ...

Read More »

አዲስ አበባ ውስጥ የታሰሩ የግብጽ ዜጎች ተፈቱ

ጥር ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ጋር በተያያዘ ለወራት በእስር ላይ የነበሩ ሶስት ግብጻዊያን ዜጎች ከእስር መስፈታታቸውን የግብጽ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት አስታወቀ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ከተገደሉበት የኢሬቻ እልቂት በኋላ ካለምንም ጥፋታቸው በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው ምንም ዓይነት ክስ ያልቀረበባቸው መሆኑንም መግለጫው አትቷል። ሶስቱም ግብጻዊያን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ...

Read More »

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ይካሄድባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ዕርምጃን ላይ የሚወስድ ሃገር አቀፍ ኮሚቴ መቋቋሙ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2009) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ይካሄድባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ዕርምጃን የሚወስድ ሃገር አቀፍ ኮሚቴ መቋቋሙ ተገለጸ። ከአንድ ሳምንት በፊት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ልዩ ትዕዛዝ የተቋቋመው ይኸው ኮሚቴ ሃገሪቱ ለከፋ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንድትዳረግ አስተዋጽዖ አድርገዋል በተባሉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃን እንደሚወስድ ካፒታል የተሰኘ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ ዘግቧል። በተለምዶ “ጥቁር ገበያ” ...

Read More »

አልሸባብ ሁለት ግብረሰዶማዊያንን እና አንድ ለኢትዮጵያ መንግስት ሲሰልል ነበረ ያለውን ግለሰብ ገደለ

ጥር ፫ (ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማክሰኞ እለት ጽንፈኛው ቡድን አልሸባብ 20 ዓመት ወጣት ኢሳቅ አብሽሮ እና የ15 ዓመት ታዳጊ አብዱረዛቅ ሸክ ዓሊ ግብረሰዶማዊ ምግባር ሲፈጽሙ በአልሸባብ ፖሊሲሶች ተይዘው ሞት ተፈርዶባቸው አንገታቸውን ተቀልተዋል። ከሁለቱ ወጣቶች በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶን ስር ለሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ሲሰልል ነበር በማለት ሰኢድ መሀመድ ዓሊ የተባለ አንድ የአካባቢው ...

Read More »

በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ደረሰ

ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማምሻውን በደረሰን ዜና መሰረት በጎንደር ቀበሌ 18 በሚገኘው  ኢንታሶል   ሆቴል ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል። በሆቴሉ ውስጥ ፋሲል የእግር ኳስ ቡድን የባንክን ቡድን ማሸነፉን ተከትሎ የሚዝናኑ ወጣቶች ነበሩ። ከ5 በላይ በጽኑ የቆሰሉ ሰዎች  ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለማውቅ የተቻለ ሲሆን፣ ወታደሮችና ፖሊሶች አካባቢውን በመክበባቸው በትክክል የሞቱና የቆሰሉ ሰዎችን ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም። ዛሬ ማክሰኞ ...

Read More »

ከህዝባዊ ተቃውሞው በሁዋላ በርካታ ድርጅቶች ሃብታቸውን ማሸሽ ቀጥለዋል።

ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባዊ አመጽ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ በአገዛዙ ተስፋ በመቁረጥ ሃብታቸውን የሚያሸሹ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮአል። ስማቻው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የባንክ ባለሙያ እንደገጸሉት፣ ባለፉት 4 ወራት በርካታ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን እያወጡ ጥገኝነት ወደ ሰጣቸው አገር ሲመለሱ፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት በመሄድ በንግድ እንቅስቃሴ ለመሳተፍ እየሞከሩ ነው፡። ...

Read More »

የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ኢትዮጵያ በነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ንግድ ሚንስቴር አስታውቋል። በዚህም መሰረት ቤንዚን በሊትር 16 ብር ከ61 ሳንቲም የነበረው አንድ ብር ከ13 ሳንቲም ጨማሪ ተደርጎበት17 ብር ከ92 ሳንቲም እንዲሸጥ ተብሎአል። ነጭ ናፍጣ 14 ብር ከ16 ሳንቲም የነበረው አንድ ብር ከ02 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበት 15 ብር ከ18 ሳንቲም ይሸጣል።  ኬሮሲን በሊትር 13 ...

Read More »

የወልድያ ነዋሪዎች  ለስታዲያም ማሰሪያና ለምረቃ በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ መገደዳቸውን ተናገሩ

ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለሀብቱ ሼክ ሁሴን አላሙዲን በራሳቸው ወጪ ወልድያ ከተማ ላይ ዘመናዊ ስታዲየም እንደሚያስገነቡ በተናገሩት መሰረት፣ የስታዲየም ግንባታው ተጠናቆ ጥር 6 ቀን 2009 ዓም ይመረቃል። ምንም እንኳ ባለሀብቱ የግንባታውን ሙሉ ወጪ እንደሚሸፍኑ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ የመንግስት ሰራተኛው የ1 ወር ደሞዙን በአመት፣ የከተማው ነጋዴዎችም እንዲሁ የተለያዩ መጠን ያላቸውን መዋጮዎች ሲከፍሉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ለስታዲየሙ ...

Read More »

በሁለት የቱርክ ባለሃብቶች የተቋቋመ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ለጨረታ ሽያጭ ቀረበ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2009) ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ ቢሊዮን ብር አካባቢ ብድር በመውሰድ በሁለት የቱርክ ባለሃብቶች የተቋቋመ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ባለሃብቶቹ ከሃገር በመኮብለላቸው ምክንያት ፋብሪካው ለጨረታ ሽያጭ ቀረበ። በሁለት ባለሃብቶች ከአምስት አመት በፊት የተቋቋመው ኤል ሲ አዲስ (L. C. Addis) የተሰኘው ይኸው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ግንባታን ለማከናወንና ማሽኖችን ለመግዛት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወደ 900 ሚሊዮን ብር አካባቢ በብድር መውሰዱ ታውቋል። የፋብሪካው ...

Read More »