ጥር ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገዛዙ በመላ አገሪቱ የሚታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ህዝብን ያረጋጋልኝ ይሆናል በማለት በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ ከፍተኛ ውግዝት ማስተናገዱን ቀጥሎአል። በከተማ ልማትና ቤት ሚ/ር ከሰኞ ታህሳስ 23 እስከ ዓርብ ታህሳስ 28/ 2009 ዓ.ም. በተደረገው የ5 ቀናት የጥልቅ ተሃድሶ ውይይት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ማለቅ ባለመቻሉ ተጨማሪ ሁለት ቀናት ወስዶ ባለፈው ማክሰኞ ተጠናቋል፡፡ ሠራተኞቹ በውይይቱ ማሃል ...
Read More »የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሽያጭ መቅረቡ በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ ስጋት አሳድሯል
ጥር ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ 40 በመቶ ለሽያጭ መቅረቡን በተመለከተ ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ከዘገበ ወዲህ የድርጅቱ ሰራተኞች ”ድርጅቱ አትራፊ ሆኖ እያለ ለምን ለሽያጭ እንዲቀርብ ተደረገ?” በማለት ቅሬታ ማሰማት ጀምረዋል። ሰራተኞቹ ከስራ ገበታችን ልንነሳ እንችላለን የሚል ከፍተኛ ስጋት ላይም ወድቀዋል። ድርጅቱ ለቻይና ኩባንያ ለሽያጭ ይቀርባል መባሉ በድርጅቱ ሰራተኞች ዘንድ መነጋገሪያ አጀንዳ ...
Read More »አሜሪካ ከ20 አመት በፊት በሱዳን ላይ የጣለቸውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አርብ በይፋ እንደምታነሳ የአሜሪካ ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ
ኢሳት (ጥር 5 ፥ 2009) አሜሪካ ከ20 አመት በፊት በሱዳን ላይ የጣለቸውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አርብ በይፋ እንደምታነሳ የአሜሪካ ባለስልጣናት ይፋ ማድረጋቸው ተገለጸ። አሜሪካ ሃገሪቱ ሽብርተኝነትን ትደግፋለች በሚል በሱዳን መንግስት ላይ ከ20 አመት በፊት የንግድና የፋይናስ ማዕቀብን ጥላ የነበረ ሲሆን፣ ሃገሪቱ ሽብርተኛነትን ለመዋጋት ተጨባጭ ጥረት በማድረጓ እገዳው ሊነሳላት መቻሉን ቢቢሲ ዘግቧል። ተሰናባቹ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በቀጣዩ ሳምንት ስልጣናቸውን ለተመራጩ ፕሬዚደንት ...
Read More »ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት በአለም የንግድ እንቅስቃሴ መዋዠቅ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ዕድገታቸው ፈታኝ እንደሚሆን የአለም ባንክ አስታወቀ
ኢሳት (ጥር 5 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት በአለም የንግድ እንቅስቃሴ መዋዠቅ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ዕድገታቸው ፈታኝ እንደሚሆን የአለም ባንክ አስታወቀ። የፈንረጆቹ 2017 አም አዲስ አመት የአለም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን አስመልክቶ ሪፖርትን ያወጣው ባንኩ በተያዘው አመት ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት የኢኮኖሚ ዕድገት በአማካኝ 2.9 በመቶ አካባቢ ሊያድግ እንደሚችል ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያ በዚሁ አመት ኢኮኖሚያዊ ዕድገቷ በሁለት አህዝ እንደሚያድግ ብትገልጽም ...
Read More »በጎንደርና በባህርዳር ከተሞች የደረሱት የቦምብ ፍንዳታዎች በቱሪዝም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላል ተባለ
ኢሳት (ጥር 5 ፥ 2009) በአማራ ክልል በጎንደርና ባህር ዳር ከተሞች ሰሞኑን የደረሰው የቦምብ አደጋ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን ሊያሳድር እንደሚችል አንድ አለም አቀፍ የደህንነት ተቋም አርብ ገለጸ። በመከላከያና የደህንነት ዙሪያዎች የሚሰራውና አይ ኤች ኤስ (IHS) ጄንስ 360 የሚል መጠሪያ ያለው ይኸው ተቋም ሁለቱ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ አለም አቀፍና የሃገር ውስጥ ቱሪስቶችን የሚያስተናግዱ በመሆኑ አደጋው ለቱሪስቶቹ የደህንነት ስጋት ...
Read More »ያለፈው የፈረንጆች አመት ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ቀውስ ውስጥ የገባችበትና በ10ሺ የሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎችም ለእስር ተዳርገው የነበረበት ነበር ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጸ
ኢሳት (ጥር 5 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2016 አም የሰብዓዊ መብት ቀውስ ውስጥ የገባችበትና በ10ሺ የሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎችም ለእስር ተዳርገው እንደሚገኙ መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገው ሂውማን ራይስት ዎች አስታወቀ። በአለም ዙሪያ ስላሉ የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎች የ2017 አም ሪፖርቱን ያወጣው የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አፈናና ረገጣ ከመቼው ጊዜ በላይ የከፋ ሆኖ መቀጠሉን ገልጿል። ባለፈው አመት በተለይ ...
Read More »በኢትዮጵያ ለወራት በዕስር ላይ የቆዩ ሶስት ግብጻውያን መለቀቃቸው ተገለጸ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2009)) ግብጽ በኢትዮጵያ ለወራት በዕስር ላይ የቆዩ ሶስት ዜጎቿ መለቀቃቸውን ሃሙስ አስታወቀች። በኢትዮጵያ በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ሲካሄድ ከቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ሶስቱ ግብጻውያን እጃቸው አለበት ተብሎ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። የግለሰቦቹን መታሰር ተከትሎ በሁለቱ ሃገራት መካከል ከሁለት ወር በላይ የፈጀ ድርድር ሲካሄድ ቆይቶ ሶስቱ ግብጻውያን ሊለቀቁ መቻላቸው አህራም የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል። ሶስቱ ግብጻውያን ረቡዕ ምሽት ...
Read More »አልሸባብ ለኢትዮጵያ ሰራዊት ሲሰልል ነበር ባለው አንድ የሃገሪቱ ተወላጅ ላይ የሞት ቅጣት መፈጸሙን ገለጸ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2009)) የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ በሃገሪቱ ተሰማርቶ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሲሰልል ነበር ባለው አንድ የሃገሪቱ ተወላጅ ላይ የሞት ቅጣት መፈጸሙ ተገለጸ። ሰይድ መሃመድ አሊ የተባለው የሶማሊያ ተወላጅ የተለያዩ መረጃዎችን ለኢትዮጵያ ወታደሮች በማቀበል አልሸባብ የጥቃት ኢላማ እንዲሆን ማድረጉን ታጣቂ ሃይሉ ማስታወቁን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በርካታ ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ የተካሄደው የሞት ቅጣት በማዕከላዊ የጁባ ግዛት ስር በምትገኘው ...
Read More »200 አካባቢ የሚሆኑ ወረዳዎች በአንደኛ ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚፈልጉ ሆነው መለየታቸውን ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2009)) በሶስት ክልሎች አዲስ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ወደ 200 አካባቢ የሚጠጉ ወረዳዎች በአንደኛ ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚፈልጉ ሆነው መለየታቸውን የተባበሩት መንግስት ድርጅት አስታወቀ። የድርቁ አደጋ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የገለጸው ድርጅቱ ባለፈው አመት በተመሳሳይ ደረጃ ውስጥ ተመድበው የነበሩት ወረዳዎች በድጋሚ አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ተረጂ መሆናቸውን በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አስፍሯል። በኦሮሚያ፣ ሶማሊ እና ...
Read More »በአዲስ አበባ በፉሪ አካባቢ የተፈናቀሉ ሰዎች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል
ጥር ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ፉሪ አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው በላያቸው ላይ የፈረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና ብቻውን የቀረው የፉሪ ደብረገነት ኡራኤል ቤተክርስቲያን ሕልውና አደጋ ላይ መሆኑን ምንጮቻን ተናግረዋል። በአካባቢው ነዋሪ የነበሩ 7 ሽህ 500 አባውራዎች በአጠቃላይ በድምሩ ከ30 ሽህ በላይ የሚገመቱ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። የተገደሉም መኖራቸውን አባቶች ይናገራሉ። ተፈናቃይ ነዋሪዎች በአፍራሽ ግብረሃይሉ በአስገዳጅ ሃይል ከ ...
Read More »