የጥምቀት በአል በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥርና በቀዘቀዘ ስሜት ተከበረ

ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዘንድሮውን የጥምቀት በአል ህዝቡ በስርዓቱ ላይ ያለውን ቅሬታ የገለጸበት ነው። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊሶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥበቃ ሲያደርጉ ታይተዋል። በሰሜን ጎንደር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የጸጥታ ቁጥጥሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠብቆ ታይቷል። በጎንደር የበአሉ ስነስርዓት ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆና በመተማ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎች ደረሱ

ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት እና ዛሬ በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ በተባለው ቦታ ሁለት የእጅ ቦንቦች የፈነዱ ሲሆን፣ ነጋዴ ባህር በተባለ ቦታ ላይም ተመሳሳይ ቦንብ ፈንድቷል። ይህን ተከትሎም አካባቢው በወታደሮች የተከበበ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችም ታፍሰዋል። ከትናንት ጀምሮ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ጥቃቱ በነጻነት ሃይሎች መፈጸሙን ከመግለጽ ውጭ በዝርዝር ጥቃቱን ...

Read More »

የግንባታ ኩባንያው በብሄራችን ምክንያት አባሮናል ሲሉ ሰራተኞች ተናገሩ

ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በውጭ ምንዛሬ እጥረት በሚል ሰበብ ከተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽንና እህት ኩባንያዎች የተሰናበቱት ከ500 በላይ ሰራተኞች ከስራቸው የተቀነሱት በብሄራቸው ምክንያት መሆኑን ተናገረዋል። የተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽንና እህት ኩባንያዎች እንደ አብዛኛዎቹ የሃገሪቱ ኩባንያዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር እንደገጠማቸው ቢታወቅም ከስራቸው የተቀነሱት ሰራተኞች ማንነት ሲጣራ ሙሉ በሙሉ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች መሆናቸው ቅነሳው ...

Read More »

በፍኖተሰላም የቅስቀሳ ጽሁፎች ተበትነው አደሩ

ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት በምእራብ ጎጃሟ የፍኖተሰላም ከተማ በርካታ የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶች ተበትነው አድረዋል። ይህን ተከትሎም ወታደሮች በብዛት ወደ ከተማዋ ገብተዋል። በወረቀቱ ላይ “ ሞት ለወያኔ” የሚል መፈክር የሰፈረ ሲሆን፣ 9 ነጥቦችም ተዘርዝረው ቀርበዋል። የአርሶአደሩ መሬት አልባነትና  የከተማው ነዋሪ  ቤት አልባነት እንዲቆም እንዲሁም  በ1 ለ 5 የጥርነፋ ስልት አገዛዙ ...

Read More »

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው የተከሰሱ እስረኞች የክስ ሂደታቸው በዝግ ችሎት እንዲታይ ጠየቀ

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2009) ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው የተከሰሱ እስረኛ ተከሳሾች የክስ ሂደታቸው በዝግ ችሎት እንዲታይ ጠየቀ። ጥያቄውን ለፍርድ ቤት ያቀረበው ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ምስክርነት መስጠት የጀመሩ ግለሰቦች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው ሲል ቅሬታውን እንዳቀረበ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ባለፈው አመት ነሃሴ ወር በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ በነበረው የእሳት አደጋ ...

Read More »

አሜሪካ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ወደ አዲስ አበባ መላኳን አስታወቀች

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ስላለው የፓለቲካ ሁኔታ ስጋቷን በመግለጽ ላይ የምትገኘው አሜሪካ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ወደ አዲስ አበባ መላኳን አስታወቀች። ነገ ሃሙስ አዲስ አበባ የሚገቡት የሀገሪቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፌልድ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በመገናኘት በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል። ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የሚመክሩት ሚኒስትሯ አዲስ ...

Read More »

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው የተከሰሱ እስረኛ ተከሳሾች የክስ ሂደታቸው በዝግ ችሎት እንዲታይ ጠየቀ

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2009) ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው የተከሰሱ እስረኛ ተከሳሾች የክስ ሂደታቸው በዝግ ችሎት እንዲታይ ጠየቀ። ጥያቄውን ለፍርድ ቤት ያቀረበው ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ምስክርነት መስጠት የጀመሩ ግለሰቦች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው ሲል ቅሬታውን እንዳቀረበ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ባለፈው አመት ነሃሴ ወር በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ በነበረው የእሳት አደጋ ...

Read More »

ከግብፅ ጋር የተደረገው ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም ለመጉዳት ያለመ አይደለም ሲል የሱዳን መንግስት አስታወቀ

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን መንግስት በቅርቡ ከግብፅ ጋር ያደረግነው ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም ለመጉዳት ያለመ አይደለም ሲል አስተባበለ። መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉት የሃገሪቱ አምባሳደር ጀምስ ፒታ-ሞርጋ ፕሬዚደንት ሳል-ቫኪር በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት የተለመደና በሁለቱ ሃገራት ትብብር ዙሪያ ለመምከር ያለመ እንደነበር ለኢትዮጵያ ቴለቪዥን በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል። ይሁንና የደቡብ ሱዳን መገናኛ ብዙሃን የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ የግብጹ ፕሬዚደንት አብደል ፈታህ ...

Read More »

በናይጀሪያ በስደተኛ ጣቢያ ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ ከ50 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2009) የናይጀሪያ አየር ሃይል በአንድ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ላይ በስህተት ፈጽሞታል በተባለ የአየር ጥቃት ከ50 የሚበልጡ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ሃገሪቱ ከጎረቤት ካሜሮን ጋር በሚያዋስናት የድንበር አካባቢ በጦር አውሮፕላን የተፈጸመው ይኸው ጥቃት ቦኮ ሃራም ተብሎ በሚጠራው ታጣቂ ሃይል ላይ ሊካሄድ የነበረ ጥቃት እንደነበር የናይጀሪያ አየር ሃይል ይፋ ማድረጉን CNN ዘግቧል። ይሁንና ጥቃቱ ራን ተብሎ በሚጠራ ከተማ ...

Read More »

በኦሮምያና ሶማሊያ ክልል የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

ጥር ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የሚመራው የሶማሊያ ልዩ ሃይል ወደ ቦረናና ጉጂ ዞኖች በማምራት በህዝቡ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የአካባቢው ታጣቂዎች በወሰዱት እራስን የመከላከል እርምጃ በርካታ የሚሊሺያ አባላት ሲገደሉ 4 መትረየሶችን ጨምሮ በርካታ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ተማርከዋል። ጉጂና ቦረናዎች የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎ በምስራቅ ሃረርጌ የጉርሱም፣ ሚደጋ ቶላ እና ጪናቅሶ ወረዳዎች ነዋሪዎች እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን ...

Read More »