በጎንደር የጥምቀት በዓል በቀዘቀዘ ሁኔታ መከበሩ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 12: 2009) በጎንደር የጥምቀት በዓል ከመቼውም ባነሰ ሁኔታ በተቀዛቀዘ ሁኔታ መከበሩን የአይን እማኞች ገለጹ። እማኝነታቸውን ለኢሳት የገለጹት አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ፣ ህዝቡ አደባባይ ከመውጣት ተቆጥቦ በአብዛኛው በቤቱ መዋሉን አስታውቀዋል። ይህም ሆኖ ግን ከተለያዩ ወረዳዎችና አካባቢዎች አበል እየተከፈለ በርካታ ቄሶችን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ ካድሬዎች ወደ ጎንደር እንዲሄዱ በማድረግ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ጥረት መደረጉ ተገልጿል። በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር ...

Read More »

የጋምቢያም መሪ ያ’ህያ ጃሜህ ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ግፊት እየተደረገባቸው ነው

ኢሳት (ጥር 12: 2009) በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጋምቢያ ባለፈው ታህሳስ በተደረገው አገር-አቀፍ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተሸነፉት ያህያ ጀሜህ፣ ስልጣናቸውን ለአሸናፊው አዳማ ባሮው እንዲያስረክቡ የምዕራብ አፍሪካ መሪዎች ማግባባታቸውን ቀጥለዋል። የጊኒው ፕሬዚደንት አልፋ ኮንዴ እና የማውርታኒያው ፕሬዚደንት ሞሃመድ ኦልድ አብደል አዚዝ ከሚስተር ጃሜህ ጋር ለመነጋገር ባንጁል እንደሚገኙ ታውቋል። ያህያ ጀምህ ከስልጣን የሚለቁበትን ቀነ-ገደብ ዓርብ ከሰዓት በኋላ ያበቃ ሲሆን፣ ከስልጣናቸው በፈቃደኝነት የማይወርዱ ከሆነ የምዕራብ ...

Read More »

በአዲስአበባ ክፍለከተሞች በደንብ አስከባሪ ስም በርካታ ቁጥር ያላቸውን በህዝቡ ውስጥ የጸጥታ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ የሚያከናውኑ ወጣቶችን መመልመል ተጀመረ፡፡

ጥር ፲፪ ( አሥራ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለስራ መደቡ በመስፈርትነት የተቀመጠው ዕድሜ ከ18 ዓመት ያላነሰ ከ30 ዓመት ያልበለጠ ሆኖ የስነምግባር ችግር እንደሌለበት ከሚኖርበት ወረዳ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ወይንም ቀድሞ ከሚሰራበት ድርጅት በስነምግባር ችግር ያልተቀነሰ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች በእኩልነት ማገልገል የሚችል እንዲሁም በቀድሞ የሁለተኛ ደረጃ ያጠናቀቁ ወይንም በአዲሱ ካሪኩለም 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ የሚል ይገኝበታል። ምልመላውን ለማከናወን በየወረዳው ኮሚቴ ...

Read More »

ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተመዘገበውን የባለስልጣናት ሃብት ይፋ ማድረግ አልቻለም

ጥር ፲፪ ( አሥራ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብአዴን አንጋፋ አባሉ አቶ ዓሊ ሱሌይማን የሚመራው የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የባለሥልጣናትን ሐብት መመዝገብ ከጀመረ ሰባት ዓመታት ቢያስቆጥርም እስካሁን የምዝገባ መረጃውን ለህዝብ እና ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑ እያነጋገረ ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን አንዳንዶቹ በስም በመጥቀስ የባለስልጣናቱ የሐብት ምዝገባ መረጃ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፣ ኮምሽኑ የተለያዩ ምክንያቶችን ...

Read More »

በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ወጣቶች እንዲሰጥ የተዘጋጁ ሸዶች ለባለሃብት መሰጠታቸው ቅሬታ ፈጠረ፡፡

ጥር ፲፪ ( አሥራ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ውስጥ ተገንብተው ለረዥም ጊዜ ያለ አገልግሎት ተቀምጠው የነበሩ ከ60 በላይ ሸዶች ለተደራጁ ስራ አጥ ወጣቶች እንዲሰጥ ቢወሰንም፣ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ጽህፈት ቤት ግን ሸዶችን ለባለሃብቶች በማከፋፈሉ ስርዓቱን ጠብቀው የተደራጁ ወጣቶች ከፍተኛ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለክልሉ ዘጋቢ ተናገሩ፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚናገሩት በ2008 እና ...

Read More »

ኦሮሚያ ክልልን ከሶማሌ ክልል ጋር በሚያዋስኑ ወረዳዎች በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2009) ኦሮሚያ ክልልን ከሶማሌ ክልል ጋር በሚያዋስኑ ወረዳዎች በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጸ። ግጭቱ ተቀስቅሶባቸዋል በተባሉት አካባቢዎች ከመሬት ይዞታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ግጭቶችን ሲካሄዱ መቆየታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ መግለጹ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት በሁላቱ አጎራባች አካባቢዎች ግጭት መኖሩን ቢገልጽም የሟች ቁጥርን ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት የኮሚኒኬሽን ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን አመራሮች በአዲስ አበባ እንደሚገኙ ታወቀ

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር የአማጺ ቡድንን ላለመደገፍ ስምምነት ብትፈራረምም፣ አሁንም ድረስ የሃገሪቱ አማጺ ቡድን አመራሮች በአዲስ አበባ መሆናቸው ተገለጸ። የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ንቅናቄ ምክትል ወታደራዊ ቃል አቀባይ የሆኑት ዲክሰን ጋትሉአክ (Dickson Gatluak) የቡድኑ አዛዥ ሪክ ማቻር በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪካ ቢሆኑም እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በአዲስ አበባ እንደሚገኙ ለቪኦኤ የእንግሊዝኛው ክፍል አስታውቋል። በጎረቤት ሱዳን ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ወደ አረብ አገር የሚሰዱ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በኩል ወደ ተለያዩ የአረብ አገራት ለመሰደድ የሚሞክሩ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው የሃረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ ሃረር ከተማን አቋርጠው በሶማሌ ክልል በኩል ድንበር ለማቋረጥ ሙከራ ያደረጉ ከ1ሺ 700 በላይ ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መደረጉን ፖሊስ ለሃገር ውስጥ መገኛኛ ብዙሃን ገልጿል። ባለፈው አመት ...

Read More »

ደቡብ ሱዳን ጥቅሟን ለማስጠበቅ በምታደርገው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያንም ሆነ ማንንም አገር አትፈራም ሲሉ የማስታወቂያ ሚኒስትር ገለጹ

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን መንግስት በቅርቡ ከግብፅ ጋር የደረሰውን የአባይ ወንዝ ስምምነት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ማብራሪያ እንደማይኖር የሃገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ገለጸ። ደቡብ ሱዳን ጥቅሟን ለማስጠበቅ በምታደርገው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያንም ሆነ ማንንም አገር አትፈራም ሲሉ የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሃላፊ ለመገኛኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ሃላፊው አቲ ዲንግ በአዲስ አበባ የሚገኙት የሃገሪቱ አምባሳደር በጉዳዩ ዙሪያ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ መደረጉንም ...

Read More »

የዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚደንታዊ በአለ ሲመት አርብ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ እንደከበር ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2009) ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አርብ በዚሁ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በሚካሄድ ደማቅ በአለ ሲመት የፕሬዚደንትነት ስልጣናቸውን እንደሚረከቡ ተልገጸ። የአሜሪካ የጸጥታ ሃይሎች በዚሁ ስነስርዓት ወቅት ዝግጅቱን ሊያውል የሚችል ተቃውሞ ሊካሄድ ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ የጸጥታ ቁጥጥሩ ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ መጠናከሩን አስታውቀዋል። በዚሁ በአለ ሲመት ላይ ለመታደም ከተለያዩ ግዛቶች በርካታ ሰዎች ወደ ዋና ከተማዋ በመግባት ...

Read More »