የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት ማስመዝገቡ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 15 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ያለፉት አምስት ወራቶች የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት ማስመዝገቡ ተገለጸ። መንግስት ከዘርፉ ወደ 279 ሚሊዮን ዶላር ኣካባቢ ለማግኘት እቅድን ይዞ የነበረ ሲሆን፣ በአምስት ወራቶች ውስጥ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ግን 166 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለመንግስት መገኛኛ ብዙሃን አስታውቋል። ጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ቆዳና የቆዳ ውጤቶችን ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ...

Read More »

የግል ባንኮች በብሄራዊ ባንክ የተቀመጠላቸውን መነሻ ካፒታል ማሟላት ካልቻሉ ውህደት እንዲፈጸሙ እንደሚገደዱ የብሄራዊ ባንክ ይፋ አደረገ

ኢሳት (ጥር 15 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተሰማርተው የሚገኙ የግል ባንኮች በብሄራዊ ባንክ የተቀመጠላቸውን መነሻ ካፒታል ማሟላት ካልቻሉ ውህደት እንዲፈጸሙ እንደሚደረግ የብሄራዊ ባንክ ይፋ አደረገ። የባንኩ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የግል ባንኮች ሊኖራቸው በሚገባው መነሻ ካፒታል ላይ አዲስ ጥናት መካሄዱን የገለጸ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ባንኮች ካፒታላቸውን ሁለት ቢሊዮን ብር ማድረስ እንዳለባቸው በብሄራዊ ባንክ በኩል መነገሩ ይታወሳል። ይሁንና፣ በአዲስ ጥናት የግል ባንኮች ...

Read More »

በአልሸባብ ስልጠና ሊወስዱ በዝግጅት ላይ ነበሩ የተባሉ ሰባት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

ኢሳት (ጥር 15 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ ስልጠና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ሰባት ግለሰቦችን እስከ አራት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ሰኞ ወሰነ። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በ2009 አም የጅሃድ ጦርነት በኢትዮጵያ ለማወጅ በማቀድ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ በዚያ ከሚገኝ የአክራሪ የሽብር ቡድን ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ለሽብር ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር በመካሄድ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

ኢሳት (ጥር 15 ፥ 2009) የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ መጀመሩን ተከልትሎ በከተማዋ ፍተሻን ጨምሮ የጸጥታ ቁጥጥር በመካሄድ ላይ መሆኑንም ነዋሪዎች ገለጹ። ልዩ ጉባዔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ተደርጎ ባለበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከመቼውም ጌዜ በላይ የተጠናከረ የጸጥታ ቁጥጥር መጀመሩን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በመዲናይቱ አዲስ አበባ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ፍተሻ በመካሄድ ላይ መሆኑን ...

Read More »

የሰራዊት ምልመላ በደላሎች መካሄድ ጀመረ

ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ አገሪቱ የሚወጡ አዳዲስ የመከላከያ ሰራዊት የቅጥር ማስታወቂያዎች በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት በማጣታቸው ገዢው ፓርቲ አዳዲስ ስልቶችን እየተጠቀመ ነው። ቀደም ብሎ በየቀበሌዎች የሚጣለው ኮታ ውጤት ባለማምጣቱ አሁን ደግሞ በደላሎች አማካኝት ቅጥር ለመፈጸም ሙከራ እየተደረገ ነው። በመከላከያ ብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር የሚታደደረው የቢሸፍቶ አውቶሞቲቭ ሰሞኑን የወታደሮች ቅጥር ማስታወቂያ ቢያወጣም፣ የሚመዘገብ ሰው ...

Read More »

በሶማሊላንድ የአማራና ኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ተያዙ

ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ከ250 ያላነሱ የአማራ እና ኦሮሞ ብሄር ተወላጆች በሶማሊላንድ ፖሊሶች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ከእስሩ ጀርባ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት እጅ እንዳለበት ታውቋል። የኦነግ እና የአርበኞች ግንቦት7 ወኪሎች በሶማሊላንድ መኖራቸውን መረጃ ደርሶናል በሚል የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት አባላት ከሶማሊላንድ የጸጥታ አባላት ጋር በመሆን የተያዙት ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲተላለፉ እየጣሩ ነው። ብዙዎቹ የተባበሩት መንግስታት ...

Read More »

አዲስአበባ ሌላ አወዛጋቢ ማስተር ፕላን ልታጸድቅ ነው

ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ እና ፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንደሚሆን ዝግጅት መኖሩን በመቃወም ሕዝባዊ ቁጣ ከተቀሰቀሰ በኋላ የተከለሰው የአዲስአበባ ማስተር ፕላን ላይ በየደረጃው ያሉ አካላት እየተወያዩበት ሲሆን የአዲስአበባ ከተማ ነዋሪዎችም ያሳተፉ ውይይት ለማካሄድ መታቀዱ ተሰምቷል፡፡ በአዲስአበባ እስካሁን ዘጠኝ ማስተር ፕላኖች ተዘጋጅተው ተግባራዊ የተደረጉ ሲሆን፣ የመጨረሻውና ዘጠነኛው ማስተር ፕላን የአገልገሎት ጊዜውን ...

Read More »

አንድ ወጣት አንድ የሚሊሺያ አዛዥ ገድሎ ተሰወረ

ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር ዞን በአጅሬ ጃኖራ አወቀ ካሴ የተባለ ወጣት ከአርበኛ ማሳፍንት ጋር በተያያዘ ታስሮ ስቃይ ሲደርስበት ከቆየ በሁዋላ፣ ወደ ዋና ከተማው ዳባት ሲመጡት “ ድልድልዬ” ከተባለ ቦታ ላይ፣ ኮማንደር መሰለ ጥጋቡ የሚባለውን ሚሊሺያ መሳሪያ በመቀማት እና በ3 ጥይቶች በመግደል የራሱንና የአባቱን መሳሪያ ይዞ በማምለጥ የነጻነት ሃይሎችን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ወራት ሊራዘም እንደሚችል ተጠቆመ

ኢሳት (ጥር 12: 2009) በኢትዮጵያ ታውጆ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈለገውን ሰላም ባለማምጣቱ፣ ለተጨማሪ ወራት ሊራዘም እንደሚችል አንድ በደህንነት ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚይቀርብ ጋዜጣ አስታወቀ። ከአንድ አመት በላይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ በሃገሪቱ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት ለውጥ እንዳላመጣ ጋዜጣው ዘግቧል። አፍሪካ ኮንፊደንሻል የተባለው ይኸው ጋዜጣ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስና ህዝባዊ ተቃውሞ ...

Read More »

በዱባይ ኢትዮጵያውያን ደማቅ ድል አስመዘገቡ

ኢሳት (ጥር 12: 2009) በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ደማቅ ድል አስመዘገቡ። የኢትዮጵያውያኑ ታምራ ቶላ እና ወርቅነሽ ደገፉ በዱባይ ማራቶችን አንደኛ በመሆን ማሸነፋቸው አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን በአንደኝነት በማሸነፋቸው እያንዳንዳቸው የአንድ መቶ ሺህ ዶላር ሽልማት ማግኘታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በወንዶች በተደረገው ውድድር በ5ኛ ደረጃ መሃል ላይ ከገባው አንድ የኬንያ ሯጭ በስተቀር ከ1ኛ እስከ 10 ተከታትለው ...

Read More »