ኢሳት (ጥር 17 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከሃገር ውስጥ እና ከውጭ አበዳሪ አካላት የወሰደው ብድር ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱንና ብድሩ የበጀት እጥረት ውስጥ እንደከተተው ይፋ አደረገ። ሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወር ስራ አፈጸጸሙን አስመልክቶ ሪፖርቱን ያቀረበው ኮርፖሬሽኑ በተያዘው በጀት አመት የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ ለማግኘት ፍላጎት ቢኖርም 31 በመቶ ብቻ የሚሆነው ገንዘብ ...
Read More »ባለፉት አምስት ወራት የውጭ ንግድ ገቢ የ700 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ጉድለት ማስመዝገቡን የንግድ ሚኒስቴር ገለጸ
ኢሳት (ጥር 17 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አጠቃላይ የውጭ ንግድ ገቢ ባለፉት አምስት ወራቶች የ700 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ጉድለት ማስመዝገቡን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሃገሪቱ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ከውጭ ንግድ ገቢ ወደ 1.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት እቅድን ይዛ የነበረ ቢሆንም፣ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ግን ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴር ይፋ ማድረጉን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሃገሪቱ 70 በመቶ ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኙት የዶርዜ ተወላጆች ጉዳያቸውን የሚያይ አካል መጥፋቱን ተናገሩ
ጥር ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙት 35 የዶርዜ ብሄረሰብ ተወላጆች ላለፉት 2 ወራት ያለ ጠያቂ በአርባምንጭ እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ጉዳያቸው በፍጥነት ታይቶ ፍርድ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ግለሰቦቹ የተያዙት የማንነት ጥያቄ አነስታችሁዋል በሚል ነው። የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ጉዳያቸውን እስከ ጠ/ሚኒስትሩ ድረስ ቢያቀርቡም መልስ የሚሰጣቸው አካል አላገኙም። ይልቁንም የብሄረሰቡ ዋና ዋና ወኪሎች የሚባሉ ...
Read More »በኦሮምያ ከ1200 በላይ ዜጎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ድርጀቱ አስታወቀ
ጥር ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ ካለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ በኦሮምያ 1200 ወጣቶች፣ እናቶችና አባቶች ሲገደሉ፣ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታስረዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ መሰደዳቸውን እንዲሁም በርካታ ሴቶች በአጋዚ ወታደሮች መደፈራቸውንም የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጿል። በታሃድሶ ስልጠና ስም በርካቶች ወደ ጦላይ፣ ሁርሶ እና ዲዴሳ ካምፖች መወሰዳቸውን የገለጸው ድርጅቱ፣ ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ተጨማሪ ሃይል ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲገባ ወሰነ
ጥር ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የቀጠለው ግጭት አሳስቦኛል ያለው ድርጅቱ፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ቦታዎች የሰብአዊ እርዳታ ሊደርስ እንዳልቻለ ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት በዝግ ባደረገው ምክክር ተጨማሪ ሃይል ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲላክ መወሰኑን የድርጅቱ የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ስዊድናዊው ኦሎፍ ስኮግ ተናግረዋል። ሰኮግ የደቡብ ሱዳን መንግስት ከጸጥታው ምክርቤት ጋር እንዲተባበርና የድርጅቱ የሰላም አስከባሪ ሃይል ...
Read More »የኬንያ ገዢ ፓርቲ ህገወጥ ኢትዮጵያውያንና የዩጋንዳ ተወላጆችን በቀጣይ ነሃሴ ለሚካሄደው ምርጫ ድምፅ እንዲሰጡ እየመዘገበ ነው ተባለ
ኢሳት(ጥር 16 ፥ 2009) የኬንያ ገዢው ፓርቲ ህገወጥ ኢትዮጵያውያንና የዩጋንዳ ተወላጆችን በሃገሪቱ በነሃሴ ወር ለሚካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ድምፅ እንዲሰጡ እየመዘገበ መሆኑን የኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት አጋለጠ። የተቃዋሚ ጥምረቱ መሪ ራይላ ኦዲንጋ የሃገራቸው ብሄራዊ የስለላ አገልግሎት የድምፅ መመዝገቢያ ወረቀቶችን ወደ ሁለቱ ሃገራት በማጓጓዝ ለኢትዮጵያውያንና የዩጋንዳ ተወላጆች የኬንያ መታወቂያ እየሰጠ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ማድረጋቸውን ዘስታንዳርድ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። የፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ...
Read More »ዶናልድ ትራምፕ ከአብደል ፈታህ አልሲሲ ጋር ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ
ኢሳት(ጥር 16 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከግብፁ አቻቸው አብደልፈታህ አል ሲሲ ጋር ሽብርተኝነትን በጋራ ለመወጋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ። ስልጣናቸውን ከተረከቡ ከአራት ቀን በኋላ ከፕሬዚደንት አል ሲሲ ጋር የስልክ መልዕክት የተለዋወጡት ፕሬዚደንት ትራምፕ፥ ሃገራቸው ከግብፅ ጋር ሁለገብ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትፈልግ መግለጻቸውን ሮይተርስ ባለስልጣናት ዋቢ በማደረግ ዘግቧል። የግብፅ ፕሬዚደንት በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ጉብኝት እንዲያደርጉ የጠየቁት ...
Read More »በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የድርቅ አደጋ የከፋ እንደሆነ የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ
ኢሳት(ጥር 16 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ዳግም የተከሰተው የድርቅ አደጋ በ120 ወረዳዎች ውስጥ የከፋ እየሆነ መምጣቱን የአለም ምግብ ፕሮግራም (FAO) ይፋ አደረገ። ካላፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በአራት ክልሎች የተከሰተው ይኸው የድርቅ አደጋ ሃገሪቱ በምግብ ምርት ራስን ለመቻል እያደረገች ባለው ጥረት ላይ ስጋት አሳድሮ እንደሚገኝ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ስላለው የድርቅ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ድርቁ የከፋ ጉዳት እያደረሰባቸው ካሉት 120 ወረዳዎች መካከል 86ቱ ...
Read More »ለአለም ጤና ድርጅት ቀጣይ ዳይሬክተር ለመሆን ከቀረቡ ስድስት ተወዳዳሪዎች የመጨረሻ ሶስቱን ለመምረጥ የመለየት ስራ ተጀመረ
ኢሳት(ጥር 16 ፥ 2009) የአለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ የተቋሙ ቀጣይ ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ከቀረቡ ስድስት የተለያዩ ሃገራት ተወዳዳሪዎች መካከል የመጨረሻ ሶስቱን የመምረጥና የመለየት ስራ ተጀመረ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ የጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ፣ ፓኪስታንና የሃንጋሪ ተወዳዳሪዎች በስዊዘርላንድ መዲና ጀኔቫ ለዚሁ ምርጫ መሰባሰባቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ከአለም ጤና ድርጅት አባል ሃገራት መካከል በድርጅቱ ከሶስት አመት ...
Read More »የድርቅ አደጋን ተከትሎ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች 600 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተገለጸ
ኢሳት (ጥር 15 ፥ 2009) በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን አዲስ የድርቅ አደጋ ተከትሎ ወደ 600 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተገለጸ። በሶማሌ ክልል ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ብቻ በምግብና ውሃ አቅርቦት ችግር 442 ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን፣ 183 ሺ ተማሪዎችም ከትምህርት ገበታቸው መቅረታቸውን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰኞ ይፋ አድርጓል። በተመሳሳይ ሁኔታ በኦሮሚያ ክልል በቦረናና ጉጂ ዞን ስር በሚገኙ ...
Read More »