በአማራ ክልል ከሚገኙ ሆስፒታሎች የቀዶ ጥገና ህክምና መስጠት የሚችሉት ከ7 አይበልጡም ተባለ።

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ 55 ሆስፒታሎች ቢኖሩም የቀዶ ህክምና የሚሰጡት ሰባቱ ሪፈራል ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው።እነዚህም በአግባቡ መስጠት የሚያስችል አቅም የላቸውም::ሆስፒታሎች በጣም አነስተኛ ከመሆናቸው ጋር ታካሚዎች ህክምናውን ለማግኘት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለተለያዩ ወጪዎች ይጋለጣሉ። ሁሉም ሆስፒታሎች ከፍተኛ የባለሙያ እና የቁሳቁስ እጥረት አጋጥሟቸዋል። ገዢው ፓርቲ በጤናው መስክ የሚሊኒየሙን የልማት እቅድ አሳክቻለሁ ቢልም፣በአገሪቱ በሚገኙ የጤና ተቋማት ከፍተኛ የሆነ ...

Read More »

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ መጠናቀቅ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እፎይታን ሰጠ።

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ አገራት 28ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ የኅብረቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ሰሞኑን ሲካሄድ ሰንብቷል። ከስብሰባው መቃረቢያ ሰሞን ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ የከተማ ነዋሪዎች በፀጥታ ሃይሎች ከመጠን ያለፈ ቁጥጥር ምክንያት የሰብዓዊ መብታቸው ተጥሶ የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ ለከፍተኛ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች ተዳርገዋል። በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች አቅራቢያ ...

Read More »

የአሜሪካ ፍ/ቤት የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ አሜሪካዊ ዜጋ ላይ ፈጽሞታል የተባለው የኢንተርኔት የስለላ ወንጀል ድርጊት በይግባኝ እንዲታይ የቀረበን ጥያቄ ማድመጥ ጀመረ

ኢሳት (ጥር 26 ፥ 2009) በአሜሪካ አገር በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሚገኝ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ አሜሪካዊ ዜጋ ላይ ፈጽሞታል የተባለን የኢንተርኔት የስለላ ወንጀል ድርጊት በይግባኝ እንዲታይ የቀረበን ጥያቄ ማድመጥ ጀመረ። የስለላ ድርጊቱ የተፈጸመባቸውን አሜሪካዊ ሾልኮ የሚገኘው የኤለክትሮኒክስ ፍሮንቲየር ፋውንዴሽን የተሰኘ ተቋም ሃሙስ መደመጥ የጀመረው የክስ ሂደት ከአንድ እስከ ስድስት ወራቶች ሊወስድ እንደሚችል አስታውቋል። ሁለት ታዋቂ የህግ አካላትን ይዞ ኪዳኔ ...

Read More »

ለስኳርና ኤሌክትሪክ ግንባታዎች ከይዞታቸው እንዲነሱ የተደረጉ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ

ኢሳት (ጥር 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ሶስት ክልሎች ለስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ እና ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጄክቶች ከይዞታቸው እንዲነሱ የተደረጉ ወደ ሶስት ሺ አካባቢ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ። በኦሮሚያ ክልል አርጆ ዴዴሳ፣ በአማራ ክልል ጣና በለስ የስኳር ልማት እንዲሁም በደቡብ ክልል ጊቤ ሶስት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጄክቶች ከቀያቸው እንዲነሱ የተደረጉት ወደ 3ሺ አካባቢ አርሶ አደሮች ምትክ መሬትና ካሳ ሳይሰጣቸው ...

Read More »

የድርቅ አደጋ እየደረሰባቸው ያሉ ወረዳዎች ቁጥር ከ200 በላይ ማሻቀቡን ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አዲስ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ ወረዳዎች ቁጥር ከ200 በላይ ማሻቀቡን የአለም ምግብ ፕሮርግራም (FAO) አስታወቁ። በአራት ክልሎች በመዛመት ላይ ባለው በዚሁ የድርቅ አደጋ 86 ወረዳዎች ደግሞ ክትትልን የሚፈልጉ ተብለው በአንደኛ ደረጃ ተለይተው መቀመጣቸውን ድርጅቱ ድርቁን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። የአለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በበኩላቸው የአለም ማህበረሰብ ችግሩን ለመታደግ አፋጣኝ ርብርብ በአውቅቱ ...

Read More »

በደሴ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ስብሰባ የጸጥታ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ሆኖ ቀረበ

ጥር ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢህአዴግ አባላት እየተሳተፉበት ባለው ስብሰባ የጸጥታ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል። በተለያዩ መድረኮች በተደረጉት ስብሰባዎች ላይ በክልሉ የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ በአባላት ዘንድ ተደጋግሞ የቀረበ ጥያቄ ነበር። በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ጥሩ እንደሆነ ገለጻ የሰጡት የመድረኩ መሪዎች፣ ይህንን እንዲያረጋግጡ ከወልቃይት፣ አርማጭሆ እና ቋራ ...

Read More »

በባህርዳር ከተማ የህወሃት አባላት ጥቃት ደረሰባቸው

ጥር ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ምሽት በአንድ ሆቴል ውስጥ ዳሸን ቢራ ሲጠጡ የነበሩ 9 የህወሃት አባላት በስካር መንፈስ ውስጥ ሆነው ክብርና ማንነትን የሚነካ ንግግር በመናገራቸው ስሜታቸውን መቆጣጠር ያልቻሉ በሆቴሉ ሲገለገሉ የነበሩ ወጣቶች ተጠራርተው በመሰባሰብ በህወሃት አባላቱ ላይ ጥቃት አድርሰውባቸዋል። የህወሃት አባላቱ “ አናፋችሁ አናፋችሁ አሁን ጸጥ አላችሁ፣ ድሮም ከእኛ አታመልጡም” እያሉ ሲዝቱ እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች፣ ...

Read More »

የውጭ ዘርፍ ንግድ ገቢ እያሽቆለቆለ ነው

ጥር ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዋንኛነት በኦሮሚያና እና በአማራ ክልሎች ባለፈው ዓመት የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በኢትዮጵያዊያን 2009 ግማሽ የበጀት ዓመት ከማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተገኘው የኤክስፖርት ገቢ እያሽቆለቆለ ነው። ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው ከሐምሌ 1 ቀን 2008 እስከ ታህሳስ 30/2009 ዓ.ም ባሉት ስድስት ወራት ከማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ 349 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ የነበረ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የ26.5 ቢሊዮን ብር ቦንድ ሽያጭ አጸደቀ

ኢሳት (ጥር 25 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ያጋጠመውን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ የ26.5 ቢሊዮን ብር ቦንድ ሽያጭ እንዲካሄድ ያቀረበው ጥያቄ ረቡዕ በፓርላማ ጸደቀ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በበኩላቸው ሊካሄድ የታሰበው የቦንድ ሽያጭ የሃገሪቱን አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ሊያባብስ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውም ገልጸዋል። በፓርላማ የጸደቀው ይኸው አዋጅ መንግስት ከተለያዩ አካላት ወለድ የሚከፈልበት የቦንድ ሽያጭ እንዲያከናውን ይሁንታ መስጠቱ ታውቋል። የአዋጁ መፅደቅን ተከትሎ መንግስት ከተለያዩ አበዳሪ ...

Read More »

ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞች ይፈጸምብናል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ለተመድ ደብዳቤ ጻፉ

ኢሳት (ጥር 25 ፥ 2009) የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞች ይፈጸምብናል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደብዳቤ ጻፉ። ከወራት በፊት ለእስር የተዳረጉት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና አናኒያ ሶሪ ለእስር በተዳረጉ ጊዜ በሽብርተኛ ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አድርጋችኋል ቢባሉም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ አለመቻላቸውን በደብዳቤያቸው ማስፈራቸውን አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ዘግቧል። በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ...

Read More »