የኢትዮጵያ መንግስት ከጉለን ንቅናቄ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ትምህርት ቤቶችን ለቱርክ አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ ተቃውሞን አስነሳ

ኢሳት (የካቲት 7 ፥ 2009) ኢትዮጵያ የቱርክ መንግስት የሽብርተኛ ድርጅት ነው ሲል ከፈረጀው የጉለን ንቅናቄ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ትምህርት ቤቶችን ለቱርክ አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ ተቃውሞን አስነሳ። ባለፈው ሳምንት በቱርክ ጉብኝትን ያደረጉ ፕሬዚደንት (ዶ/ር) ሙላቱ ተሾመ መንግስታቸው በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶችን ለቱርክ መንግስት ለማስተላለፍ መወሰኑ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና ነጃሺ ኢትዮ-ቱርኪሽ ኢንተርናሽናል በመባል የሚጠሩትት አምስት ትምህርት ቤቶች ...

Read More »

የግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት በኬንያውያን ላይ ተፅዕኖ ማሳደር መጀመሩን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 7 ፥ 2009) በቅርቡ ግንባታው የተጠናቀቀው የግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት በኬንያ የቱርካና ሃይልና በኢትዮጵያ በታችኛው የስምጥ ሸለቆ በሚኖሩ በግማሽ ሚሊዮን ነዋሪዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር መጀመሩን ሂውማን ራይትስ ዎች ማክሰኞ አስታወቀ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የቱርክና ሃይቅ የውሃ ከፍታ መጠን ካለፈው የፈረንጆች አመት ጀምሮ በ1.5 ሜትር ቀንሶ መገኘቱን የአሜሪካ የዕርሻ መምሪያ መረጃን ዋቢ በማድረግ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ...

Read More »

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሽብርተኝነትን አስመልቶ ከናይጀሪያ እና ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንቶች ጋር ውይይት አደረጉ

ኢሳት (የካቲት 7 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከናይጀሪያና ደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንቶች ጋር በአህጉሪቱ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚደረጉ ትብብሮች ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ። ፕሬዚደንት ትራምፕ ከሁለቱ ሃገራት መሪዎች ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት አሜሪካ ሃገሪቱ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚያደርጉት ጥረት ድጋፍና ትብብር እንደሚደረግላቸው ቃል መግባታቸው ታውቋል። በፕሬዚደንት ትራምፕ ከናይጀሪያው ፕሬዚደንት መሃሙድ ቡሃሪ ጋር የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው የናይጀሪያ ፕሬዚደንታዊ ጽ/ቤት ሁለቱ መረጃዎች ...

Read More »

ነዋሪዎች በላያቸው ላይ ቤቶች እንደፈረሱባቸው ተናገሩ።

የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ሰኞ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አፍራሽ ግብረሃይል ከ500 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን አፍርሷል። ታዛቢዎች እንደሚናገሩት አፍራሽ ግብረሃይሉ በድንገት በመሄድ በወሰደው እርምጃ 2 ከወለዱ ሳምንት ባልሞላቸው እናቶች ላይ ቤታቸውን በላያቸው ላይ አፍርሰዋል። እርጉዞች ፣ ህናጻትና አሮጊቶች በተወሰደው እርምጃ ሲያነቡ አርፍደዋል። እቃቸውን እንኳ በወጉ እንዳያወጡ በመደረጋቸው ብዙዎች ለአመታት ደክመው የገዙዋቸውን እቃዎች ሳይቀር ...

Read More »

በስልጣን ላይ ያሉ ተሿሚ አመራሮች ምንም ዓይነት የፖለቲካ ዕውቀት የሌላቸው ናቸው ሲሉ አሰልጣኞች ተናገሩ፡፡

የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች በጥልቅ ተሃድሶ በመሰልጠን ሀገሪቱ ከወደቀችበት አዘቅት ነጻ ያወጣሉ ተብሎ የታመነባቸው አመራሮች ምንም ዓይነት የፖለቲካ ዕውቀት የሌላቸው መሆኑን አንድ አሰልጣኝ በተለይ ለኢሳት ተናገሩ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት አመራሮችን በማሰልጠን የተሳተፉት ግለሰብ እንደተናገሩት አመራሮች ለስልጠና ከመግባታቸው በፊት በተሰጣቸው የሀገሪቱን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በሚዳስሰው የመግቢያ ፈተና አብዛኛው ሰልጣኝ የግንዛቤ ችግር አለበት። በአሁኑ ሰዓት ...

Read More »

አለማቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ እጁን በፍጥነት አለመዘርጋቱ ጭንቀት ፈጥሯል

የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ወር መጀመሪያ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ጭምር በአባልነት የሚገኙበት የድርቅ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ኮምቴ ለቀጣዩ አንድ ዓመት ለድርቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ይፋ ቢያደርግም የዓለም አቀፉ ማህበረሰቡ ምላሽ እጅግ የተቀዛቀዘ መሆኑ አገዛዙን አሳስቦታል። ከብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ወቅት የመኽር ዝናብ ማለትም በያዝነው ዓመት ከጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት እስከ ታህሳስ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 በተለያዩ ከተሞች የተሳካ ስብሰባ ማድረጉን አስታወቀ

የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ እየታገለ ያለው አርበኞች ግንቦት7 ባለፈው ቅዳሜና እሁድ 46 ከተሞችን ያሳተፈ ስብሰባና የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ መስራቱን ታውቋል። የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በምስል ስልክ በተለያዩ አህጉራት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ከሁሉም አካባቢዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ድርጅታቸው ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ፣ ከተለያዩ ድርጅቶች ...

Read More »

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የዋስትና መብት ተከለከለ

የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሕግ አግባብ ውጪ የሸብር ክስ ተመስርቶበት በእስር ላይ የሚገኘው የነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የዋስትና መብት ተከልክሏል። ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ያቀረበውን የዋስትና መብት ጥያቄ የተመለከተ ሲሆን፣ ”ተከሳሹ በዋስ ቢወጣ በሕጋዊም ሆነ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ስለሚችል የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበልነውም” የሚል ውሳኔ ሰጥቷል። ይግባኝ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከር የማግባባት (Lobyying) ስራ ከሚሰራ ኩባንያ ጋር የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመች

ኢሳት (የካቲት 6 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት በተያዘው የፈረንጆች አመት ከአሜሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የማግባባት (ሎቢንግ) ስራ ከሚያካሄድ አንድ ድርጅት ጋር የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረሙ ታወቀ። በዚሁ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ግርማ ብሩ መንግስትን በመወከል SRG-LLC ከተሰኘ ኩባንያ ጋር የፈረሙት ሰነድ የውጭ ወኪሎችን ጉዳይ የሚዘግበው ፎሪን ኤጀንትስ ሬጂስትሬሽን በድረ-ገጹ ላይ ባፈረው መረጃ አመልክቷል። በዚሁ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ከአሜሪካው ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት ሰባት በአርባ አምስት ከተሞች የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባና የድጋፍ ማሰባሰብ ዝግጅቶች ማድረጉን አስታወቀ

ኢሳት (የካቲት 6 ፥ 2009) አርበኞች ግንቦት 7 “እኔ ለነጻነቴ” በሚል መሪ ቃል በአርባ አምስት ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባና የድጋፍ ማሰባሰብ ዝግጅት በስኬት ማጠናቀቁን ገለጹ። ንቅናቄው እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ፌብሯሪ 11 እና 12 ቀን 2017 “እኔ ለነጻነቴ” የሚል ውይይትና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ያደረገው በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች፣ በአውሮፓ፣ በካናዳና፣ ደቡብ አፍሪካ መሆኑ ታውቋል። ከተሞችን በሁለት ቀን በመክፈል በተመሳሳይ ሰዓት በቀጥታ ውይይት በተካሄደው ...

Read More »