ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2009) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ስልሳ የመንግስት ልማት ድርጅቶች በኪሳራ ሊዘጉ መሆኑን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ አስታወቀ። ባለፉት 15 አመታት ወደ ግል ከተዛወሩ 263 የመንግስት ልማት ድርጅቶች ውስጥ በ60 ድርጅቶች ስም የነበሩ ተሰብሳቢና ተከፋይ ዕርምጃዎች ማግኘት ባለመቻሉ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ እንደሚሰርዝ የቦርዱ ሃላፊዎች ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ...
Read More »በኬንያ የሃኪሞች ማህበር የጠራውን ተቃውሞ የግል ተቋማት ሃኪሞች ተቀላቀሉ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2009) የኬንያ ፍርድ ቤት ለሁለት ወር የቆየውን የሃኪሞች የስራ ማቆም አድማ እንዲያበቃ አላደረጉም ባላቸው ሰባት የሃኪሞች ማህበር አባላት ላይ ያስተላለፈውን የእስር ቅጣት በመቃወም በግል ተቋማት የሚሰሩ ሃኪሞች ተቃውሞን ተቀላቀሉ። መንግስት ከአራት አመት በፊት የገባውን የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ አላደረገም ያሉ ወደ 5ሺ አካባቢ የሚጠጉ የሃገሪቱ የህክምና ባለሙያዎች ተቃውሞአቸውን ለሁለተኛ ወር መቀጠላቸውን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል። ይሁንና የኬንያ ...
Read More »ከልማት ባንክ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ዝርፊያ የምርመራ ሂደት ቀጥሎአል
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መላኩ ፋንታ ከእስር ቤት ተጠርተው ተጠይቀዋል፤ የባንኩ ከፍተኛ ባለስልጣናት የነበሩ መጥሪያ ደርሷቸዋል፤ የህወሃት መካላከያ አባላት ሰነድ አጥፍተዋል፤ ከአገር የወጡም አሉ። የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን የሰሩትና የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፋንታ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ መሬት ዝርፊያ ጋር ...
Read More »በምስራቅ ሃረርጌ ከ20 ያላነሱ የልዩ ሃይል አባላት በደፈጣ ውጊያ መገደላቸው ታወቀ
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ አብዲ ሙሃመድ የሚመሩት የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በጉርሱምና ቦምባሴ አካባቢ ያደረጉትን ወረራ ተከትሎ ፣ በደፈጣ ውጊያ ከ20 ያለነሱ የልዩ ሃይል አባላት መገደላቸውን የደህንነት ምንጮች ገለጹ። እርምጃውን የወሰዱት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሲሆኑ፣ 12 የጦር መሳሪያዎችን እና በአማካኝ እስከ 44 የሚደርሱ ካርታ ጥይቶች ተወስደዋል። የሶማሊ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በ7 የኦሮምያ ...
Read More »በጅጅጋ በመከላከያ በአል ላይ የአየር ላይ ትርኢት ለማሳየት የነበረው እቅድ ተሰረዘ
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጅጅጋ በተከበረው የመከላከያ ቀን ላይ በአየር ሃይል ሄሊኮፕተሮች የአየር የበረራ ትርኢት ለማሳየት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በአብራሪዎች ችሎታና የአይሮፕላኖች ቴክኒካዊ ብቃት ጉድለት ምክንያት እንደታሰበው ሳኪያሄድ ቀርቷል። በአሉ አስቀድሞ በደብረዘይት ከተማ በሚገኘው የአየር ሃይል ዋና አዛዠ በሆነዉ ሰፈር ለማክበር ታስቦ የነበር ሲሆን፣ ዘግይቶ በመጣ ትዕዛዝ በዓሉ በጂጂጋ እንዲከበር መወሰኑን የመከላከያ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ...
Read More »በአማራ ክልል ህዝቡ በደን ኢንተርፕራይዝ ላይ ተቃውሞ ማሰማቱን ተከትሎ ድርጅቱ ሊዘጋ ነው
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ደን ኢንተራፕራይዝ በህዝብ ተቀባይነት ማግኘት ባለመቻሉ እና በኪሳራ ውስጥ በመግባቱ የክልሉ መንግስት በክልሉ 14 ቦታዎች ካቋቋመ በኋላ ሊዘጋው እንደሆነ ታውቋል፡፡ በርካታ አነስተኛ የጣውላ ማሽኖችን ከአንዶነዥያ በማስመጣት ወጣቶችን የስራ ዕድል በመንጠቅ እና ግዙፍ ደኖችን በማውደም በርካታ ጣውላዎች ማምረት ቢችልም ፣ ላለፉት አምስት አመታት ያመረታቸው ጣውላዎች አገልግሎት ላይ መዋል ባለመቻላቸው ለብልሽት ...
Read More »በኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ አስታወቀ::
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሚያካሂደው 34ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈፀሙትን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶት አትኩሮት በመስጠት እንዲያወግዝ ሲል የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ ጥሪውን አቅርቧል። በኢትዮጵያ የአስቸኳይ የጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ በተለይ በወጣት የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ግድያ፣ እስራት፣ ከአገር ማሳደድ፣ አካላዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የተለያዩ ...
Read More »የግልገል ጊቤ ሦስት ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ላይ አደጋ ጋርጧል ተባለ
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የገነባችውን ግድብና እያካሄደች ያለውን ልማት ተከትሎ የኬንያ ቱርካና ሀይቅ የውሃ መጠን መቀነሱ በግማሽ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ህይወት ላይ አደጋ መጋረጡት ዓለማቀፉ የስብ አዊመብት ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋሙ በዩናይትድ ስቴትስ የእርሻ ዲፓርትመንት ለሕዝብ ክፍት የሆኑ የዳታ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ በምዕራብ እና አርሲ ዞን ብቻ ከ240 ሰዎች በላይ መገደላቸው ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 7 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ መታወጁን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብና አርሲ ዞን ብቻ በ20 ቀናት ውስጥ 240 ሰዎች መገደላቸውን የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ ገለጸ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ከመስከረም 28/2009 እስከ ጥቅምት 18/2009 በአርሲ ነገሌ ብቻ 70 ሰዎች ሲገደሉ፣ 335 መታሰራቸውን የገለጸው የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ፣ ከዚህ በተጨማሪም በሻላ እና አጄ በተባሉ አካባቢዎች 85 ሰዎች ሲገደሉ ...
Read More »በሶማሌ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮች በጊዚያዊ መጠለያ እንዲሰባሰቡ በመደረግ ላይ መሆኑን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (የካቲት 7 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል የተከሰተው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮች በጊዚያዊ መጠለያ እንዲሰባሰቡ በመደረግ ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታወቀ። የአርብቶ አደሮችን ህይወት ለመታደግ ሲባል እየተወሰደ ባለው በዚሁ ዘመቻ አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማትና መንግስት ለተጎጂዎቹ የምግብ አቅርቦት እንደሚያደርጉ ድርጅቱ ገልጿል። ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በክልሉ በተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ...
Read More »