በሚዳ ወረሞ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በፖሊሶች ተበተነ

የካቲት ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ከተማ ወጣቶች ትናንት ምሽት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የበተኑ ሲሆን፣ ዛሬ ጠዋት ከያቅጣጫው ሲሰባሰቡ ከመርሃቤቴ የተነሱ ፖሊሶች እንደበታተኑ በማድረግ ከተማዋን ተቆጣጥረዋል። ወጣቶቹ በመሰባሰብ ላይ እያሉ ፖሊሶች ነጣጥለው በማጥቃት እንዲበተኑ ያደረጉ ሲሆን፣ባለፈው ሳምንት ታስሮ በድጋሜ ተለቆ የነበረው የቀድሞው የደህንነት ሰራተኛ ወጣት አብዩ ሰይድ በድጋሜ ታፍኖ ተወስዷል። ከተማዋ ሙሉ ...

Read More »

በቡሌ ሆራ ከተማ በርካታ ወጣቶች በእስር ቤት ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

የካቲት ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በምዕራብ ጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተለያዩ ክፍሎች፣ በእያንዳንዱ 3 በ 4 ሜትር በሆነ አነስተኛ ክፍል ውስጥ እስከ 50 ሰዎች ታጉረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። በአካባቢው ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰሩት በመቶዎች የሚቆጠሩት ወጣቶች፣ በምግብ እጥረት እየተሳቃዩ ነው። ፖሊስ ጣቢያ በሚታሰሩበት ወቅት ምግብ ...

Read More »

ኦህዴድ ከ18 ሺ በላይ አባላቱ ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

የካቲት ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ ባወጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በኦሮምያ ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ 4 ሺ 460 ነባር አመራሮችና 13 ሺ 578 የቀበሌ አመራሮች ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡ እርምጃ በተወሰደባቸው ሰዎች ቦታ ላይ 5 ሺ 832 አዳዲስ አመራሮችን መተካቱን ገልጿል። በክልል እና በወረዳ ደረጃ በኪራይ ሰብሳቢነት ምክንያት እርምጃ ከተወሰደባቸው 964 ሰዎች መካከል 260 ለህግ ይቀርባሉ ብሎአል። ...

Read More »

ዶ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት በተወለዱ በዘጠና ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የካቲት ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የታሪክ፣ ባህል እና የምጣኔ ሃብት ባለሞያ ዶ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 3 ቀን1927 እንግሊዝ ውድፎርድ ግሪን ከተማ ውስጥ ተወለዱ። ለንደን በሚገኘው ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የኢኮኖሚካዊ ታሪክ ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት ዶ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት እናታቸውን ወ/ሮ ሲልቪያ ፓንክኸርስት ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በቀድሞው ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ውስጥ መምህር በመሆን አገልግለዋል። በደርግ ...

Read More »

ሶማሊያ ውስጥ የተገደሉ ወታደሮች ሳይታወሱ መቅረታቸው ደማቸው በከንቱ እንደፈሰሰ እንቆጥረዋለን ሲሉ የመከላከያ አባላት ተናገሩ

የካቲት ፰ ( ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊ ከአስፈልጌ ወየን እስከ ሃልጌን ባሉ ቦታዎች፣ ከሰኔ 1 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተደረገው ጦርነት የ13ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሪጅመንት በርካታ አባላት እንዲሁም በኮሎኔል ጌጡ ዳምጤ የሚመራው ጦር ከፍተኛ እልቂት ደርሶበታል። ይሁን እንጅ ጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቀን ላይ ክፍለ ጦሩና አዛዡ ለሽልማት ቢታጭም ከፍተኛ መስዋትነት የከፈሉ ...

Read More »

የሲናሬ ወረዳ ወጣቶች በእስር ላይ የሚገኝ አባላቸውን አሰፈቱ

የካቲት ፰ ( ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በሲናሬ ወረዳ በአካባቢው ከሚካሄደው ትግል ጋር በተያያዘ አንድ የአካባቢው ወጣት መታሰሩን ተከትሎ፣ ራሳቸውን ያደራጁ ወጣቶች በምሽት ወደ እስር ቤት በመሄድ ጓዳቸውን ከማስፈታታቸውም በተጨማሪ ሌሎች እስረኞችም አምልጠዋል። ይህንን ተከትሎ አካባቢው በወታደሮች መከበቡን የአይን እማኞች ለኢሳት ተናግረዋል። በተመሳሳይ ዜና ትናንት የነጻነት ሃይሎችን ለመምታት ወደ እንቃሽ የተንቀሳቀሰው ያገዛዙ ሰራዊት፣ ያሰበው ...

Read More »

ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ማሽቆልቆሉ ተዘገበ

የካቲት ፰ ( ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመት (Foreign direct investment) በአንድ አምስተኛ ቅናሽ ማሳየቱ ብሉበርግ ዘግቧል። ሕዝባዊ አመጹን ተከትሎ ከባህር ማዶ የሚመጡ ባለሃብቶች መዋእለ ንዋያቸውን በማፍሰስ በኢንቨስትመንት መስክ ለመሳተፍ ፍላጎታቸው ተቀዛቅዟል። በውጭ ባለሃብቶች ንብረት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ለኢንቨስተሮች ፍሰት ማሽቆልቆል በምክንያትነት ተጠቅሷል። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 1.5 ቢሊዮን ...

Read More »

የመን እና ጅቡቲ በስደተኞች መጥለቅለቃቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ

የካቲት ፰ ( ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመን እና ጅቡቲ አገራቸውን ትተው በህገወጥ መንገድ በሚፈልሱ ስደተኞች መጨናነቃቸውን እና ሰብዓዊ ቀውስ መፈጠሩን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም አስታወቀ። በእርስበርስ ጦርነት ወደምትታመሰው የመን እና ጅቡቲ በየወሩ ቁጥራቸው ከ10 ሽህ በላይ ስደተኞች በበረሃና በባሕር አቆራርጠው ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው የሚገቡ ሲሆን አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ወደ የመን ከሚገቡት ስደተኞቹ ውስጥ 30 ...

Read More »

የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስት ተወካዮች የድንበር ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር በመቀሌ ተሰባሰቡ

ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2009) የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስት ተወካዮች በሁለቱ ሃገራት መካከል ስላሉ የድንበር ይገባኛል ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ሃሙስ በመቀሌ ከተማ ምክክር እንደሚጀምሩ ተገለጸ። በኢትዮጵያ በኩል ከአማራ፣ ቤኒሻንጉልና, የትግራይ ክልሎች የተወከሉ ባለስልጣናት ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን፣ ከሱዳን በኩል ደግሞ የጋዳሬፍ፣ የብሉናይል፣ የሴርናና፣ የከሰላ ግዛት ተወካዮች ለሁለት ቀን በሚቆየው ምክክር ተሳታፊ እንደሚሆኑ ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ዘግቧል። የኢትዮጵያና የጎረቤት ሱዳን ተወካዮች በሚሳተፉበት በዚሁ ...

Read More »

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ በአምስት በመቶ መቀነሱ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ሲካሄድ የቆየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የሃገሪቱ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ በአምስት በመቶ መቀነሱን አንድ አለም አቀፍ የፋይናንስ መጽሄት ረቡዕ ዘገበ። ለአንድ አመት ያህል በኦሮሚያ ክልል የዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ያስነበበው ፊን-24 የተሰኘው መጽሄት በግማሽ አመቱ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ኢንቨስትመንት ለማግኘት ታቅዶ እቅዱ ከ300 ...

Read More »