በትግራይ ክልል ፕሬዚደንት መዘግየት የተስተጓጎለው የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ኮሚሽን ስብሰባ በመቀሌ ተጀመረ

ኢሳት (የካቲት 10 ፥ 2009) በትግራይ ክልል ፕሬዚደንት መዘግየት ለአንድ ቀን የተስተጓጎለው የኢትይጵያና የሱዳን የድንበር ኮሚሽን ስብሰባ መቀሌ ላይ ተጀመረ። የአማራ ክልል ፕሬዚደንት እና ምክትል ፕሬዚደንቱ ያልተገኙ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ክልል ፕሬዚደንት እንዲሁም የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ተሳታፊ መሆናቸው ተመልክቷል። የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት አቶ አባይ ወልዱ ልዑካኑ ትግራይ ሲገቡ፣ እርሳቸው አዲስ አበባ ስለነበሩ ስብሰባው ለአንድ ቀን እንዲራዘም ምክንያት ሆኗል። የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ...

Read More »

የፌዴራል ከሳሽ አቃቤ ህግ አቶ በቀለ ገርባ ኢሳትን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ያደረጓቸው ንግግሮች በማስረጃነት ማስደመጥ ጀመረ

ኢሳት (የካቲት 10 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከሳሽ አቃቤ ህግ የሽብርተኛ ክስ በተመሰረተባቸው አቶ በቀለ ገርባ ላይ የሰው ምስክር ማቅረብ ባለመቻሉ ተከሳሽ ኢሳትን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ያደረጓቸውን ንግግር በማስረጃነት ማስደመጥ ጀመረ። አቃቤ ህግ ተከሳሽ አመፅን የሚያነሳሱ ንግግር አድርገዋል ብሎ በቀረበው በዚሁ ማስረጃ በተቃራኒው ተከሳሽ ከአመጽ የጸዳ (ጸረ-አመፅ) ትግል እንዴት መካሄድ እንዳለበት ሲናገሩ በቪዲዮው መደመጡ ታውቋል። አቃቤ ህግ የአቶ በቀለ ገርባ ንግግር ...

Read More »

ብኢኮ ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላን ለማስራት ከ235 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለሁለት አገራት ኩባንያዎች ክፍያ ፈጸመ ።

የካቲት ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ሚኒስቴር ስር የሚገኘውና አብዛኛውን የመከላከያን ግዢ በኮንትራት ወስዶ የሚሰራው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላኖችን በአገር ውስጥ ለማሰራት ከ235 ሚሊዮን 500 ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይም 4 ቢሊዮን 710 ሚሊዮን ብር መክፈሉን ከድርጅቱ የተገኙ የሂሳብ መዝገብ ሰነዶች አመለከቱ። ብኢኮ በፈንጆች አቆጣጠር ከ2011 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ብቻ ከ1 ...

Read More »

1 ሚሊዮን የሚሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቤት እናገኛለን በሚል ገንዘብ እየቆጠቡ ቢሆንም ቶሎ ቤት የማግኘት ተስፋቸው የደበዘዘ ሆኗል

የካቲት ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 997 ሺ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለያዩ የቤት ግንባታ መርሃግብሮች በመመዝገብ ከምግብና ከሌሎች ፍጆታቸው በመቀነስ በየወሩ እየቆጠቡ ባንክ ያስገባሉ። አብዛኛው ህዝብ 20 በ 80 በሚባለው መርሃ ግብር ተመዝግቦ ቤቶችን በመጠባባቅ ላይ ቢሆንም፣ መስተዳዳሩ ባጋጠመው ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ የተጀመሩ ግንባታዎችን 80 በመቶ ለማድረስ የነበረውን እቅድ ሳይሳካ የቀረ ሲሆን፣ በአብዛኛው የግንባታ ...

Read More »

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በሱዳን ፖሊሶች ጥቃት ተፈጸመባቸው አንድ ኢትዮጵያዊም ተገሏል

የካቲት ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪነታቸው በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ የሆነ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኤንባሲው ቅጽር ግቢ በመገኘት መብታቸውን በመጠየቃቸው በኢትዮጵያ ኤንባሲ ትእዛዝ ሰጭነት በሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ጥቃት ተፈጸመባቸው። ባለፈው ሳምንት ከኤንባሲው ጋር ለመነጋገር በያዙት ቀነ ቀጠሮ መሰረት ወደ ኤንባሲው የሄዱ ቁጥራቸው ከ2 ሽህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በስፍራው ሲደርሱ በወታደራዊ ተሽከርካሪ ተጭነው የመጡ ሱዳናዊያን ...

Read More »

በዝምባብዌ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል ገቡ

የካቲት ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ዝምባብዌ ውስጥ ተይዘው የታሰሩ 54 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በርሃብ እና ድካም ተጎሳቁለው ራሳቸውን በመሳት ወድቀዋል። ከኢትዮጵያኑ ስደተኞች ውስጥ ስምንቱ በከፍተኛ ሕመም ራሳቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ሆስፒታል ገብተዋል። ማንነታቸውን የሚገልጽ ምንም ዓይነት ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶች ሳይዙ በምእራባዊ ዝምባብዌ ኒኮልሰን ክፍለሃገር በጊዋንዳ ግዛት ሲያቆራርጡ ባለፈው ዓርብ በጸጥታ ...

Read More »

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ትኩረት እንድትሰጥ ጠየቀ

ኢሳት (የካቲት 9: 2009) በነሃሴ 2009 በብራዚል ሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን የብር ሜዳሊያ ያሸነፈው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ትኩረት እንድትሰጥ ጠየቀ። በቢሊዮኖች በሚከታተሉት መድረክ ተቃውሞውን ካቀረበ ከስድስት ወራት በኋላ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያም ባለቤቱና ሁለት ልጆቹ ጋር በአሜሪካ ተገናኘ። በአለም አቀፍ የኦሎምፒክ መድረክ በኢትዮጵያ የሚካሄደው የሰብዓዊ መብት ረገጣ በመቃወም የአለም ሚዲያ መነጋገሪያ የነበረው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ, ...

Read More »

የህንድ የጨርቃጨርቅና የልብስ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ነጻ መሬት ተሰጥቷቸው በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ የማግባባት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 9: 2009) በህንድ ጉብኝትን እያደረጉ ያሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሃገሪቱ የጨርቃጨርቅና የልብስ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ነጻ መሬት ተሰጥቷቸው በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ማግባባት እያደረጉ መሆኑን የሃገሪቱ መገኛኛ ብዙሃን ዘገቡ። በህንድ በኮንጉ-ናዱ ግዛት ስር በምትገኘው የትሪፑር ከተማ ጉብኝትን እያደረጉ ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታደሰ ሃይሌ ህንዳዊያን ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መግባት ቢፈልጉም ነጻ መሬት እንደሚቀርብላቸው ቃል መግባታቸውን ዎርልድ ኦፍ ጋርመንት መጽሄት አስነብቧል። ...

Read More »

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በ90 አመታቸው አረፉ

ኢሳት (የካቲት 9: 2009) በኢትዮጵያ ታሪክ ለረጅም አመታት ጥናትና ምርምር በማካሄድ የሚታወቁት ታዋቂው የኢትዮጵያ ወዳጅ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በ90 አመታቸው አረፉ። የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ኢንስትቲዩት በመመስረት የሚታወቁት የብሪታኒያ ዜግነት ያላቸው ፕሮፌሰር ፓንክረስት እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በኢትዮጵያ መኖር እንዲጀምሩ ስለህይወታቸው ከተጻፉ ታሪኮች ለመረዳት ተችሏል። በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ከ20 በላይ መጽሃፎችን በማሳተም ለአለም ለንባብ ያበቁት የታሪክ ምሁሩ ለበርካታ ...

Read More »

ለእስር የተዳረጉ የፖለቲካ አመራሮችና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲለቀቁ አንድ የስዊድን የፓርላማ አባል ጥሪ አቀረቡ

ኢሳት (የካቲት 9: 2009) በኢትዮጵያ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ምክንያት ለእስር የተዳረጉ የፖለቲካ አመራሮችና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲለቀቁ አንድ የስዊድን የፓርላማ አባል ጥሪ አቀረቡ። በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ለሃገሪቱ ፓርላማ ንግግርን ያቀረቡት የፓርላማ አባሉ እንደርስ አስተርበርግ፣ የስዊድን መንግስትና የአለም አቀፍ ማህብረሰብ በኢትዮጵያ በመፈጸም ላይ ይገኛል ላሉት የሰብዊ መብት ጥሰቶች ትኩረትን እንዲሰጡም አሳስበዋል። በቅርቡ ለእስር የተዳረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲናን እና ጋዜጠኛ እስክንድር ...

Read More »