ፕሬዚደንት አልበሽር ግብፅ ለደቡብ ሱዳን ወታደራዊ የጦር መሳሪያዎችን እያቀረበች ነው አሉ

ኢሳት (የካቲት 17 ፥ 2009) የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር ግብፅ ለደቡብ ሱዳን መንግስት የተለያዩ ወታደራዊ የጦር መሳሪያዎችን እያቀረበች ነው ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን ገለጹ። ግብፅ ለጎረቤት ደቡብ ሱዳን እያቀረበች ያለው ይኸው የጦር መሳሪያ የሱዳን መንግስት የስለላ መረጃዎች ተጠቅሞ ሊረጋገጥ መቻሉን ፕሬዚደንት አልበሽር ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ይሁንና የሱዳኑ ፕሬዚደንት ግብፅ ለደቡብ ሱዳን መንግስት እያቀረበች ያለው የጦር መሳሪያ ለሃገራቸው መንግስት ስጋት እንደማይሆን አስታውቋል። ከአንድ ...

Read More »

ደቡብ ሱዳንና ከኢትዮጵያ አንዱ የሌላው ሃገር ታጣቂ ቡድኖች እንዳያስተናገዱ የሚያደርግ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢሳት (የካቲት 17 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ጉብኝትን እያደረጉ ያሉት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚደንት ሳልባኪር ከኢትዮጵይ ጋር አንዱ የሌላው ሃገር ታጣቂ ቡድኖች እንዳያስተናገዱ የሚያደርግ ስምምነት መፈራረማቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘግበዋል። በሁለቱ ሃገራት በድንበር፣ በጸጥታና በነዳጅ አቅርቦት ዙሪያ ተመሳሳይ ስምምነት መድረሳቸውም ታውቋል። ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በተለያዩ ጊዜያት ያደረጓቸውን መግባባቶች ተከትሎ የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን አመራር ሪክ ማቻር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መደረጉም ...

Read More »

300 ኪሎግራም የዝሆን ጥርስ በሳውዲ አረቢያ አውሮፕላን ቦሌ ላይ ተያዘ

ኢሳት (የካቲት 17 ፥ 2009) ንብረትነቱ የሳውዲ አረቢያ በሆነ አውሮፕላን በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ነበር የተባለ ከ300 ኪሎግራም በላይ የዝሆን ጥርስ በአዲስ አበባ ቦሌ አውርፕላን ማረፊያ ጣቢያ አርብ በቁጥጥር ስር ዋለ። የዝሆን ጥርሱ ከናይጀሪያ ተነስቶ ወደ ምዕራባዊያን አፍሪካዊት ማሊ ሊጓጓዝ እንደነበር የኢትዮጵያ ገበዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። ይኸው ድርጊት ከህግ ጥሰት ባሻገር በኮንትሮባንድ ወንጀል እንደሚያስጠይቅ መስሪያ ቤቱ ገልጿል። ይሁንና ...

Read More »

የዝዋይ ሃይቅ በኬሚካል በመበከሉ ህዝቡ ውሃውን እንዳይጠቀም ተከለከለ

የካቲት ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሆላንድ ዜጎች የተመሰረተውና ከፍተኛ መንግስታዊ ድጋፍ እንዳለው የሚነገርለት ሼር ኢትዮጵያ የአበባ እርሻ የሚጠቀምበት ኬሚካል የዝዋይ ሃይቅን በመበከሉ፣ ህዝቡ ውሃውን እንዳይጠቀም ተከልክሏል። ክልከላው በቀበሌ ደረጃ ከተላለፈ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ህዝቡ በከፍተኛ የውሃ ችግር እየተሰቃየ ነው። ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለፁት ከዝዋይ ሃይቅ ተጣርቶ የሚወጣው የቧንቧ ውሃ ሲመረመር ከፍተኛ የሆነ ለጤና አደገኛ ...

Read More »

በቢሊዮን የሚቆጠር ብር የፈሰሰበት የአባይ በረሃ መንገድ በተሰራ በአጭር ጊዜ ውስጥ አደጋ ላይ መውደቁ ታወቀ

የካቲት ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዛሬ 9 ዓመት የአባይ ድልድይ እንደገና ሲገነባ የመንግስቱ የመገናኛ ብዙሃን ብዙ ብለዋል። በወቅቱ አገሪቱን ይገዙ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ድልድዩን መርቀው ሲከፍቱ ድልድዩ የጃፖን የጥበብ ደረጃ የታየበት፣ የሁለቱን አገራት ዘላለማዊ ግንኙነት የሚያበስር ነው በማለት አሞካሽተውት ነበር። ድልድዩም አባይ ድልድይ መባሉ ቀርቶ ህዳሱ ድልድይ እንዲባል ተወስኖ ነበር። በጊዜው በጃፓን የኢትዮጵያ ...

Read More »

ገዥው ፓርቲ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚያደርገውን የመከላከያ ሰራዊት ምልመላ እንዲያቆም ተጠየቀ

የካቲት ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በተደጋጋሚ በሚደረገው የመከላከያ ሰራዊት ምልመላ ያልተሳካላቸው የጦር ኃይሉ የቅጥር ቡድን፣ በመሰናዶና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚያደርጉትን የወታደር ምልመላ ቅስቀሳ ሊያቆሙ እንደሚገባ መምህራን ጠይቀዋል፡፡ በተለይ በባህር ዳር ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎችን ሆን ብሎ ለመቀስቀስ በትምህርት ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የቅጥር ማስታወቂያውን በመለጠፍ ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ ዳግም የውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አገረሹ ኢትዮጵያንም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።

የካቲት ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ደርባንን ጨምሮ በፕሪቶሪያ በሌሎች የአገሪቱ ከተሞች በውጭ አገር ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ዳግም አገርሽተዋል። ፀረ ስደተኛ አቋም ያላቸው ደቡብ አፍሪካዊያን የተለያዩ የእጅ መሳሪዎችን በመያዝ በስደተኞች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በበኩላቸው ድርጊቱን ”ፀያፍ” ሲሉ ኮንነውታል። አንድ የውጭ አገር ስደተኛ ”ለምን ትጠሉናላችሁ?” ”ስለምን ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና የሽብርተኝነት ክስ በይፋ ተመሰረተባቸው

ኢሳት (የካቲት 16 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈዋል ተብለው በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ሃሙስ የተለያዩ የወንጀል ክሶች በይፋ ተመሰረተባቸው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተግባራዊነትን የሚከታተለው ወታደራዊ ዕዝ ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ ጉብኝታቸው በተመለሱ ጊዜ አዋጁን ጥሰዋል በሚል ለእስር ተዳርገው መቆየታቸው የሚታወስ ነው። የዚህኑ ምርመራ መጠናቀቅ ተከትሎ አቃቤ ህግ ህገ-መንግስቱን በሃይል ለመናድ በሚሉና የተለያዩ ወንጀል ክሶች መመስረቱን አዲስ ስታንዳርድ ...

Read More »

ኢትዮጵያ መጠነ-ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከተፈጸሙባቸው ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 16 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆች 2016 አም በአለም መጠነ-ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከተፈጸሙባቸው ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርት ገለጸ። በሃገሪቱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ለአንድ አመት ያህል ጊዜ የዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተስተናገዱበት ወቅት ሆኖ መመዝገቡን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የ2016 አም ሪፖርቱን አስመልክቶ ባወጣው የሰብዓዊ መብት ቅኝቱ አስፍሯል። በዚሁ ...

Read More »

ለህዝብና ቤቶች ቆጠራ 180ሺ ዲጂታል ታብሌቶች (ዘመናዊ የእጅ ኮሚውተሮችን) ግዢ እንዲፈጸም ተወሰነ

ኢሳት (የካቲት 16 ፥ 2009) በቀጣዩ አመት በኢትዮጵያ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መንግስት 180ሺ ዲጂታል ታብሌቶች (ዘመናዊ የእጅ ኮሚውተሮችን) ግዢ እንዲፈጸም ወሰነ። ዋና ዋና ከተሞችን ጨምሮ በአብዛኛው በገጠር የሃገሪቱ አካባቢዎች ለሚካሄደው ለዚሁ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ የእጅ ኮምፒውተሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊዎች ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ዘማናዊ ያእጅ ኮምፒውተሮቹን ግዢ ለመፈጸም መንግስት በሚሊዮን ...

Read More »