ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2009) የህወሃት/ኢህአዴግ አማጺያን ወደ አዲስ አበባ እየገፉ በመጡበት ወቅት የመንግስት መቀመጫ ከአዲስ አበባ ለማንሳትና ወደ ደቡብ ወይንም ምስራቅ ለመውሰድ ክርክር መደረጉን ተገለጸ። በቀድሞ የኢትዮጵያ መንግስትና በአማጺያን መካከል የተደረገው ድርድርም በአሜሪካ ጣልቃገብነት እንደከሸፈ ይፋ ሆኗል። ይህ የተጋለጠው በለንደን በተካሄደው ድርድር የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን በመምራት በሂደቱ ተዋናይ በነበሩት በጠ/ሚኒስተር ተስፋዬ ዲንቃ መጽሃፍ ላይ ነው። በዚህ ሳምንት ለንባብ የበቃውና ...
Read More »በአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ 500 ሺ ስደተኞች በሱዳን እንደሚገኙ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ
ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2009) አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ወደ 500ሺ አካባቢ የሚጠጉ የኤርትራና የሶማሊያ ስደተኞች በሱዳን እንደሚገኙ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ። ሰሞኑን ሱዳን በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ፈጽማዋለች የተባለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ተከትሎ ለሃገሪቱ የሚሰጠውን የስደተኞች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቋርጥ የተጠየቀው ህብረቱ ለሃገሪቱ እስካሁን ድረስ የለቀቀው ድጋፍ አለመኖሩን ገልጿል። የሱዳን የድንበር ተቆጣጣሪ ሃይሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ ወደ ሃገሪቱ ድንበርን እያቋረጡ የሚገቡ ...
Read More »በጋምቤላ ክልል በሰፋፊ የእርሻ ልማት ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሃብቶች በባንክ የተቀመጠ 7.5 ሚሊዮን ብር ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል ለሰፋፊ የእርሻ ልማት ስራ ሲሰጥ በቆየው ብድር በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ የደረሰበት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ ባለሃብቶች በትንሹ 7.5 ሚሊዮን ብር ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አዲስ መመሪያን ተግባራዊ አደረገ። ባንኩ ባለፉት ጥቂት አመታት በጋምቤላ ክልል ሲሰጥ በቆየው ብድር በርካታ ባለሃብቶች በተመሳሳይ መሬት ላይ ተደራራቢ ብድርን በመውሰድ ለብድር የተሰጠ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ የገባበት ...
Read More »በአዲስ አበባ አንድ ጣሊያናዊን የገደሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ነው ተባለ
ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2009) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በጥይት የተገደለ ጣሊያናዊ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገለጸ። ስሙ ያልተገለጸው የ32 አመት ጣሊያናዊ የካቲት 18 ምሽት በከተማዋ ቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ የምሽት ክበብ በመዝናናት ላይ እንዳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉን በስፍራው የነበሩ እማኞች ለሃገር ውስጥ መገናኛ ተቋማት አስረድተዋል። ሟች ከጓደኞቹ ጋር ...
Read More »በአማራ ክልል ጎንደርና ባህርዳር “ኮማንድ ፖስት” ተጨማሪ ተጽዕኖ እያደረሰ መሆኑ ተነገረ
ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2009) በአማራ ክልል ከተቀጣጠለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወዲህ በከፍተኛ ልዩ ጥበቃ ውስጥ የሚገኙ የጎንደርና የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች በኮማንድ ፖስቱ ተጨማሪ ተጽዕኖ እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በዚሁም የባህርዳር ከነማና የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ዝርዝር ለኮማንድ ፖስቱ መመሪያ ተላልፏል። በሌላ በኩል በወህኒ ቤት የሚገኙ እስረኞችን በአማራ ክልል ቴሌቪዥን መቅረጽ ተጀምሯል። በሃምሌ 2008 ዓም መጀመሪያ በጎንደር የተነሳውና ...
Read More »ታጋይ ጎቤ መልኬ መስዋቱ ታወቀ
የካቲት ፳፪ ( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የነጻነት አርበኛው ታጋይ ጎቤ መልኬ ከሃምሌ 5 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝን በመሳሪያ ሲፋለም ቆይቶ፣ መሰዋቱን ምንጮች ገልጸዋል። በጀግንነቱ የብዙ ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ የገዛው የ70 አመቱ ታጋይ ጎቤ፣ በእሱ የሚመራው ሃይል ከህዳር 16 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ በገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ በተዳጋጋሚ ሲያደርስ በነበረው ጥቃት ከፍተኛ ...
Read More »በአርባምንጭ በተፈጠረው ግጭት 2 ህጻናትና አንድ ጎልማሳ ተገደሉ
የካቲት ፳፪ ( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ የካቲት 19፣ 2009 ዓም አርባምንጭ ከተማ ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በአርባምንጭ ከነማ ቡድኖች መካከል የተደረገውን የእግር ኳስ ጨዋታ ተከትሎ፣ በፖሊስና በህዝብ መካከል በተፈጠረው ግጭት 2 ህጻናትና አንድ ጎልማሳ ተገድለዋል። የአይን እማኖች እንዳሉት ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባማንጭን 4 ለ1 እየመራ በነበረበት ወቅት፣ በመጨረሻው ሰአት ላይ አንድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ...
Read More »ባለፈው ዓመት የወጣውና የባጃጅና ታክሲ አሽከርካሪዎችን ለስራ ማቆም አድማ አነሳስቶ የነበረው የትራንስፖርት ህግ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ በመሆኑ በባህርዳር ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረ ተነገረ፡፡
የካቲት ፳፪ ( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በአማራ ክልል የከተማ ታክሲዎችና ባጃጆች ላይ የወጣውና ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳት ከሶስት ቀን በላይ የስራማቆም አድማ በማድረግ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ተደርጎ የነበረው ህግ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን በመጀመሩ ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ ታክሲዎችና ባጃጆች ሰሞኑን በተጀመረው በአንድ ምድብ ብቻ እንዲሰሩና ወደ የትኛውም የከተማዋ አካባቢ ለግል ጉዳይም ሆነ ...
Read More »በሞዛምቢክ 36 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ
የካቲት ፳፪ ( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ ሞዛምቢክ የአውራጃ አስተዳደር በህገ ወጥመንገድ ወደ ሞዛምቢክ ገብተዋል ያላቸውን 36 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብ ቀው መያዛቸውን የፖሊስ ቃል አቀባይ ዘካርያ ናኩቴ ለአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። በእስር ላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ እንደሚሞከርም አክለው ተናገረዋል። ...
Read More »ኢህአዴግ አባላቱን ሳይቀር እየሰበሰበ በማሰር ላይ ነው
የካቲት ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የኢህአዴግ አባላት ሳይቀር የጦር መሳሪያ ሽጣችሁዋል በሚል እየታሰሩ ነው። በሚሊሺያ ስም ያስታጠቃቸውን አባሎቹን ሳይቀር እያሰረ የሚገኘው አገዛዙ፣ በአካባቢው የተሰማሩት ወታደሮች የነጻነት ሃይሎችን ትደግፋላችሁ በሚል በጅምላ እየቀጡዋቸው ነው። አፈናው መሮት ለትግል ጫካ የገባ አንድ ታጋይ እንደገለጸው፣ በአሁኑ ሰአት አገዛዙን በክርክር ማሳመን ስለማይቻል፣ ህዝቡ አንድ ነገር ...
Read More »