ለነጻነት በሚደረገው ትግል ኢትዮጵያውያን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2009) ለነጻነት በሚደርገው ትግል ኢትዮጵያውያን በአቅማቸውና በሙያቸው አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ። በአራት ድርጅቶች በቅርቡ የተመሰረተው ሃገራዊ ንቅናቄ በዋሽንግተን ዲሲ  ከኢትዮጵያን ጋር ባካሄደው ውይይት በሀገሪቱ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መሰረት ያደረገ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ የአፋር ህዝብ ፓርቲ፣  እና የሲዳማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በጋራ ...

Read More »

በሱዳን የሚኖሩ የሃይማኖት አባትና ሌሎች ስደተኞች ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጡ

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2009) በሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ለእስር ተዳርገው የነበሩ አንድ የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባትና ሌሎች ሰዎች ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጉዳዩን በመከታተል ላይ ያሉ አባላት ለኢሳት አሳታወቁ። የሃይማኖች አባቱ ቄስ ተገኝ በሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው ላለፉት 10 ወራቶች ያህል በእስር ላይ እንደነበሩ የተናገሩት እነዚሁ አካላት በሃገሪቱ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የሃይማኖት አባቱን ጉዳት በመከታተል ላይ እንደነበር ከዜና ክፍላችን ጋር ...

Read More »

በሶማሊያ ከ100 በላይ ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸውን ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 27 ፥ 2009) ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በረሃብ ምክንያት ከ100 በላይ ሰዎች በሶማሊያ መሞታቸውንና የሟቾች ቁጥር እየጨመረ እንደሚካሄድ ስጋት መኖሩን የሃገሪቱ ባለስልጣናት ሰኞ ይፋ አደረጉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ በጎረቤት ሃገራት ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ የከፋ ችግር ከማስከተሉ በፊት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ርብርብ እንዲያደርግ በድጋሚ አሳስቧል። በዚሁ የድርቅ አደጋ ተጠቂ በሆነችው ሶማሊያ ቤይ ተብሎ በሚጠራው ግዛት ...

Read More »

የዞን 9 ጦማሪያን ለ53ኛ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ኢሳት (የካቲት 27 ፥ 2009) አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ይግባኝ ለ52ኛ ጊዜ ፍርድ/ቤት የቀረቡት የዞን 9 ጦማሪያን ውሳኔ ሳያገኙ ለ53ኛ ጊዜ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ታወቀ። ይግባኝ የተጠየቀባቸው ጦማሪያን በፍቃዱ ሃይሉ፣ ናትናዔል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እንዲሁም ሶሊያና ሽመልስ (በሌለችበት) ተለዋጭ ቀጠሮ ለመጋቢት 11, 2009 ተሰጥቷቸዋል። ዓቃቤ ህግ የተከሳሾቹን ከእስር መፈታት በመቃወም ያቀረበው ይግባኝ ዕልባት ሳያገኝ ለ53ኛ ጊዜ በቀጠሮ ሲሸጋገር ከጦማሪያን አንዱ ...

Read More »

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ77 ግለሰቦች ላይ ክስ መሰረተባቸው

ኢሳት (የካቲት 27 ፥ 2009) የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ እንዳይሆንና ነዳጅ ከጎረቤት ወደ ሃገር ውስጥ እንዳይገባ አድርገዋል የተባሉ 77 ግለሰቦች ክስ እንደተመሰረተባቸው አስታወቀ። ከተከሳሾቹ መካከል 12ቱ ኤርትራውያን ናቸው የተባሉ ሲሆን፣ ግለሰቦቹ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆኑ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋት ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በክሱ ማመልከቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ተከሳሾቹ ከጥር 2 ቀን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረገጣን የገመገመው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊ ሪፖርት ይፋ ሆነ

ኢሳት (የካቲት 27 ፥ 2009) የኢትዮጵያን የ2016 አም አጠቃላይ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ የገመገመው አመታዊ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (State Department) ሪፖርት ይፋ ሆነ። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2016 ዓም የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከልክ ያለፈ ሃይል እንደጠተቀሙ የገለጸው ይኸው ሪፖርት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ መገደላቸውና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን አመልክቷል። ሪፖርቱ፣ የህዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞዎች የተደረጉት በአብዛኛው በኦሮሚያና አማራ ክልሎች መሆናቸውና፣ ይህኑም ...

Read More »

በጎንደር ከተማ የከንቲባው መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ

ኢሳት (የካቲት 27 ፥ 2009) በጎንደር ከተማ ከንቲባ መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ። ጥቃቱን የፈጸመው አካል ማንነት አልታወቀም። በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች በጥርጣሪ ተሰብሰብው ታስረዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን የጎንደር ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ተቀባ ተባባል መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ቅዳሜ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በጥቃቱ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን አመልክተዋል። ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ...

Read More »

በከንቲባው ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በጎንደር የሚደረገው ፍተሻ ተጠናክሮ ቀጥሎአል

የካቲት ፳፯ ( ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጎንደር ከተማ ያለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባባል መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ አባላት የአካባቢውን ህዝብ ሲያዋክቡ መሰንበታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ጥቃቱ በግለሰቡ ላይ ያደረሰው ጉዳት ይኑር አይኑር የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ጥቃቱ እንደተሰማ አካባቢው በወታደሮች ታጥሮ የጥቃቱን ...

Read More »

በጂንካ የሙስሊም አመራሮች ታሰሩ

የካቲት ፳፯ ( ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ሦስት የሙስሊም አባቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ እስካሁን ምክንያቱ ባልተገለጸላቸው ሁኔታ በጂንካ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ፡፡ አባቶችን ለመያዝ በዞኑ ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ ቤታቸውን የፈተሸው ቡድን ከሃይማኖታዊ ስነስርዓት ውጭ በሆነ ሁኔታ መስገጃቸውን በጫማቸው በመርገጥ ፣ የህጻናት የመማሪያ ደብተሮች ሳይቀር በማገላበጥና የቤት ዕቃዎችን በመበታተን ...

Read More »

በዶ/ር መረራ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ ኢሳትና ኦኤምኤን ላይ የተመሰረተው ክስ ለችሎት ማሰማት ተጀመረ

ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2009) ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰሞኑን በዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም በኢሳትና በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ላይ የመሰረተውን ክስ ሃሙስ ለችሎት ማሰማት ጀመረ። ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት መቅረብ ያልቻሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና በችሎት የተገኙ ሲሆን፣ የቀረበባቸውን ሽብርተኛ ቡድን መደገፍ ኣንዲሁም በማነሳሳት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከፋይ በመሆን የሽብር ወንጀል ክስ እንደተነበበላቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዶ/ር መረራ ...

Read More »