በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው አደጋ በአካባቢው በመገንባት ላይ ባለ በባዮ-ጋዝ ፕሮጄክት ምክንያት መሆኑ ተገለጸ 

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለ65 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው አደጋ በአካባቢው በመገንባት ላይ ያለ የባዮጋዝ ፕሮጄክት ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ። በከተማዋ አስተዳደር በመካሄድ ላይ ላለው ለዚሁ ግንባታ መሬቱን ለማስተካከል ሲከናወኑ የቆዩ ስራዎች በቆሻሻ ክምሩ ላይ ጭነት ማሳደሩንና ለአደጋው መንስዔ መሆኑን ሮይተርስ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። አቶ ብርሃኑ ደግፌ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪና ...

Read More »

በጎንደር ከተማ በእግር ኳስ ደጋፊዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት ተነስቶ ጨዋታው ተቋርጦ ነበር ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) እሁድ በጎንደር ከተማ በኢትዮጵያ ቡናና በፋሲል ከነማ መካከል የተካሄደ የእግር ኳስ ጨዋታ በደጋፊዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት በማስነሳት ጨዋታው ለጥቂት ጊዜያት እንዲቋረጥ ማድረጉን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታው በጎንደር ከተማ ስታዲየም በመካሄድ ላይ እንዳለ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የተለያዩ መፈክሮችን ማሰማት በጀመሩ ጊዜ በድርጊቱ ቅሬታ የተሰማቸው የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ዕርምጃ ለመውሰድ ሙከራ አድርገው እንደነበር ታውቋል። ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት ለኢትዮጵያና ሌሎች አገራት ሲሰጥ የቆየው የገንዘብ ድጋፍ ብክነት አሳይቷል ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ለኢትዮጵያና ሁለት የአፍሪካ ሃገራት ለአማራጭ የሃይል አቅርቦት ፕሮጄክቶች ሲሰጥ የቆየው በመቶ ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ “ብክነት” አስከትሏል የሚል ጥያቄን አስነሳ። ሃገሪቱ ለዚሁ ፕሮጄክት ከስምንት አመት በፊት ወደ ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ የሚጠጋ ገንዘብ ብትመድብም በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እንዲሁም በማሊ የሃይል አማራጭን ተግባራዊ ለማደረግ የተከናወኑ ስራዎች ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ታይቶባቸዋል የሚል ጥያቄ ማስነሳቱን ቴሌግራፍ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት መቅረፍ አልቻለም ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) በቅርቡ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመር አገልግሎት የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር መፍታት ሳይችል መቅረቱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ዘገበ። በከፍተኛ የውጭ ብድር የተገነባው የባቡር አገልግሎት የከተዋን ነዋሪዎች ፍላጎት ማሟላት ባለመቻሉ ምክንያት ተጠቃሚዎች ፊታቸውን ወደ መለስተኛ አውቶቡስ የታክሲ አገልግሎት እያዞሩ መሆኑን የዜና አውታሩ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። ...

Read More »

የሃዘን መግለጫ

ቅዳሜ መጋቢት 2, 2009 አም በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ የመላው የኢሳት ቤተሰብ የተሰማው ሃዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን። በትንሹ ከ60 በላይ ኢትዮጵያውያን ያለቁበትና አሁንም የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ የሚገኘውን ይህን አደጋ በተመለከተ ኢሳት የሶስት ቀና ሃዘን እንዲሆን ወስኗል። ከማክሰኞ መጋቢት 5 ጀምሮ እስከ ሃሙስ መጋቢት 7 2009 በሚቆየው የሃዘን ቀን በኢሳት ማናቸውም ሙዚቃዎች የማይተላለፉ ሲሆን፣ ፕሮግራሞቹ  በሃዘን መግለጫዎች ይታጀባሉ። ...

Read More »

በህዝባዊ ወያነ ኃርነት ትግራይ-ህወኃት መሪነት በጋምቤላ የተቀናጀ ጭፍጨፋ እየተደረገ ነው ተባለ

መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጋምቤላ ኒሎቴ አንድነት ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ጋምቤላ ውስጥበታጠቁ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች እንዲሁም የንዌርና ሙርሌ ጎሳ በሆኑ የግመል አርቢዎች አማካይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት እየተፈጸመ እነደሆነ በመጥቀስ ድርጊቱን አጥብቆአውግዟል። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር መጋቢት 1 ቀን 2017 አመተ ምህረት ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የታጠቁየሙርሌ ሚሊሻዎች ድንበር አሳብረው በመግባት በኦቱዎል መንደር በጆር ቀበሌ ስምንት ሰዎችን ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና የተከሰስኩት ወንጀል ፈጽሜ ሳይሆን ለአገሬና ለህዝብ በመታገሌ መሆኑንየኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ

መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር መረራ ጉዲና የዋስትና መብት መከልከላቸውን አስመልክቶ እየተፈጸመባቸው ያለውን የመብት ጥሰቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ እዲያውቅላቸው ከእስር ቤት ደብዳቤ ልከዋል። የተከሰስኩት ምንም ዓይነት ሕገወጥ ወንጀል ፈጸሜ ሳይሆን ለዘመናት ለአገሬና ለህዝብበመታገሌ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ ብለዋል። ከእነ ጀነራል መንግስቱ ነዋይ እና ጄኔራል ታደሰ ብሩ ዘመን ጀምሮ ከአንድ ትውልድ በላይ ገዳዮችና ሟቾች፣ ታሳሪዎች እና አሳሪዎች፣ በበዙበት ...

Read More »

የአዲስ አበባ ታክሲ አሸከርካሪዎች ፍትህ አጣን ይላሉ

መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ህዳር ወር የስራ ማቆም አድማ መተው የነበሩት የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ከአድማው በሁዋላ ችግራቸው እንደሚፈታላቸው ተነግሯቸው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም በችግር እየተሰቃዩ መሆኑን ገልጸዋል። “መድረሻ አጥተናል፣ መቆሚያችንን ለሰላም ባስ ለሚባለው ለቀን ወጥተናል። የሰቀቀን ኑሮ ነው የምንኖረው” የሚሉት አሽክርካሪዎች ዳኝነት ጠፍቷል በማለት ምሬታቸውን ገልጸዋል። ኢህአዴግ የጥፋት ሪከርድ ምዝገባ ተወግዷል ቢልም የገንዘብ ቅጣቱ ጨምሮ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን ጎንደር ጥቃት ፈጽሞ እስረኞችን አስለቀቀ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሃይሎች በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ ችንፋዝ  በገና ሲራሬ ከተማ ሰርገው በመግባት በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስለቀቁ። ታጋዮቹ ትናንት የካቲት 30: 2009 አም ምሽት ከ4 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት በከተማ ባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ገድለዋል። የተወሰኑ የከተማዋ ታጣቂዎች ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ድጋፍ በመስጠት በህወሃት ኢህአዴግ ወታድሮች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ከፊሎችም ...

Read More »

አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት ታቋርጥ ሲሉ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009) ዩ ኤስ አሜሪካ ከጨቋኙ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነቷን ታቋርጥ ሲሉ የአሜሪካ ምክር  ቤት አባል ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ ጥሪ ሲያቀርቡ ሌላው የምክር ቤት አባል ኮንግረስ ማን ዳና ሮራባከር  ዩ ኤስ አሜሪካ አናሳዎችን ብቻ ከሚወክለው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር የነበራት ግንኙነት ስህተት መሆኑን ተቀብላ ለሁለቱ ሃገራት ጥቅም የኢትዮጵያን ህዝብ መሰረት ያደረገ ግንኙነት እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ...

Read More »