በአዲስ አበባ ቆሻሻ መድፊያ ቦታ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው።

መጋቢት ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሸ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው አደጋ ሟቾች ቁጥር ከ90 በላይ የደረሰ ሲሆን፣ አሁንም በርካታ ዜጎች ከተቀበሩበት አፈር አልወጡም። ዛሬ ማክሰኞ ከ40ያላነሱ ሰዎች ተገኝተዋል። ከተገኙት አስከሬኖች መካከል ከወለደች 3 ወሩዋ የሆነችው አራስ እና የልጇ እንዲሁም ሁለት ቁራን በመቅራት ላይ የነበሩ ታዳጊዎች ይገኝበታል። ወላጆችም ዛሬም አካባቢውን ከበው ሲያለቅሱ ውለዋል። በጭንቀት ...

Read More »

ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የአውራሪስ ቀንድ ከኢትዮጵያ ወደ ታይላንድ ሊገባ ሲል ተያዘ

መጋቢት ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግምታቸው ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ 21 የአውራሪስ ቀንድ በሕገወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ታይላንድ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የታይላንድ ባለስልጣናት አስታወቁ። ባለፈው ዓርብ መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ወደ ታይላንድ ከገባ አውሮፕላን ውስጥ ክብደታቸው 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ በቦርሳዎች የተጫኑ ከተለመዱት የአውራሪስ ቀንዶች ለየት ያሉ እና ትላልቆች የአውራሪስ ቀንዶችን በታይላንድ አየር ማረፊያ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከቀናት በፊት ከደረሰው አደጋ የተረፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ ተጓትቷል ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀናት በፊት ከደረሰው አደጋ የተረፉ በርካታ ሰዎች የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ ተጓትቷል በማለት ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ። ቅሬታ አቅራቢዎቹ አሁንም ድረስ ከፍራሹ ሊወጡ ያልቻሉ ሰዎች መኖራቸውንና ፍለጋው ከተጠበቀው በላይ መጓተት ማሳየቱን እንደገለጹ ቪኦኤ የእንግሊዝኛው ክፍል ቅሬታ አቅራቢዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። “በአግባቡ የሚረዳን አካል ባለመኖሩ እራሳችን የቁፋሮ ስራ እያከናወንን ...

Read More »

በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ከሶስት ሺ በላይ መኖሪያ ቤቶች ለመልሶ ማልማት ፕሮጄክት ሊፈርሱ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥2009) ክፍለ ከተማው የመኖሪያ ቤቶቹን ለማፍረስ በቅርቡ የተዋወቀው 10ኛው የከተማዋ የተሻሻለ የማስተር ፕላን በከተማው አስተዳደር መጽደቁን እየተጠበቀ የሚገኝ ሲሆን፣ እንዲፈርሱ የተወሰነባቸው 3ሺ 221 መኖሪያ ቤቶች ከ12 አመት በፊት የተገነቡ መሆናቸውን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶች ከ20 አመት በፊት የተገነቡ መሆናቸው ታውቋል። የየካ ክፍለ ከተማ እንዲፈርሱ በተወሰነባቸው አካባቢዎች የከተማ አስተዳደር የመልሶ ማልማት ፕሮጄክቶችን ለማካሄድ እቅድ እንዳለው ...

Read More »

በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተፈጠረው አደጋ የሟቾች ቁጥር 72 መድረሱ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥2009) በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተፈጠረው አደጋ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ማክሰኞ ምሽት ድረስ ቁጥሩ 72 መድረሱ ተገለጸ። በአካባቢው በሚደረገው ፍለጋ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ሊሄድ እንደሚችል የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው። ከአደጋው የተረፉ ሰዎች በቆሻሻ ክምሩ አቅራቢያ ወደ 300 የሚደርሱ ሰዎች ይኖሩ እንደነበር ይገልጸዋል። ይሁንና የነዋሪዎቹ ትክክለኛ ቁጥሩ በአግባቡ ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለተከሰተው የህይወት መጥፋት አደጋ የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ ነው አለ

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ60 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ለሆነው አደጋ የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ መንግስት በርካታ ሰዎች በቆሻሻ ክምር አጠገብ ለብዙ ጊዜያት ሲኖሩ ዝም ብሎ መመልከቱንና አደጋው ቀድሞ ሲወሰድ በሚችል የጥንቃቄ እርምጃ መከላከል ይቻል እንደነበር ገልጿል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለባዮ-ፊዩል የሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት ...

Read More »

አንድ የእንግሊዝ ኩባንያ ከአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን ለማምረት ፈቃድ ተሰጠው

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥2009) መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገ አንድ የፖታሽ የማዕድን አምራች ኩባንያ በአፋር ክልል ለቀጣዮቹ 20 አመታት የማዕድን ሃብቱን ለማምረት የሚያስችለው ፈቃድ በኢትዮጵያ መንግስት እንደተሰጠው ማክሰኞ ይፋ አደረገ። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን እንዲያገኝ ተደርጓል በተባለው በዚሁ ልዩ ፈቃድ ሲርከም (Circum) የተሰኘው ኩባንያ በብቸኝነት በአፋር ክልል በዳናክል አካባቢ ከአራት እስከ ዘጠኝ ቢሊዮን ቶን የሚጠጋ ፖታሽ ማዕድን ማምረት እንዲያችለው ማይኒንግ ዊክሊይ የተሰኘ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የቆሻሻ መጣያ ሰፈር በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው

መጋቢት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮልፌ ቀራንዩ ወረዳ 01 በተለምዶ ቆሸ ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በተፈጠረው የቆሻሻ ክምር መደርመስ የሟቾች ቁጥር ከ50 በላይ የደረሰ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም እንደጠፉ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። አብዛኞቹ ሟቾች ሴቶችና ህጻናት ሲሆን፣ አስከሬን የመፈለጉ ስራ ቀጥሏል። አስከሬን ሲያወጡ የነበሩ ወጣቶች እንደገለጹት ቁራን ሲቀሩ የነበሩ ህጻናት እንዲሁም፣ ከወለደች 3 ቀናት የሆናት ...

Read More »

ኦህዴድ ከሶማሊ ድንበር ጋር በሚዋሰኑ ወረዳዎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የሶማሊ ክልልን ተጠያቂ አደረገ

መጋቢት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮምያ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በጻፉት ጽሁፍ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ስር ባሉ ቁምቢ፣ጭናክሰን፣ ሚደጋ ቶላ፣ጉርሱም፣መዩ ሙሉቄ እና ባቢሌ ወረዳዎች፤ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የሚገኘዉ የጉምቢ ቦርዶዴ ወረዳ፣ በባሌ ዞን የሚገኙት ዳዌ ሰረር፣ሰዌና፣ መደ ወላቡ እና ራይቱ ወረዳዎች፣በጉጂ ዞን ጉሚ ኢደሎና ሊበን ወረዳዎች በቦረና ዞን የሚገኘዉ ሞያሌ ወረዳ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አውስተው፣ ...

Read More »

የህውሃት የበላይነት አለ ያሉ በብአዴን አመራር ስብሰባ ላይ በልዩነት የወጡ አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ

መጋቢት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ የብአዴን ውይይት እና የካቢኔ አመራር ስብሰባ ላይ “ የህወሃት የበላይነት አለ” በማለት በልዩነት የወጡ የክልል አመራሮች ከስልጣን ተባረዋል። የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ም/ኃላፊ አቶ ቹቹ እና የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ የሻምበል በውይይቱ ላይ “ ህወሃት አገሪቱን በበላይነት እየመራት ነው፣ ሌሎች ፓርቲዎች ያላቸው ኃላፊነት በእጅጉ የወረደ ነው” የሚል ሃሳብ በማንሳት ...

Read More »