አሜሪካና እንግሊዝ ከመካከለኛ ምስራቅና አፍሪካ ሃገራት የሚጓዙ መንገደኞች ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ይዘው እንዳይጓዙ እገዳን አስቀመጡ

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) አሜሪካ ከስምንት የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ሃገራት ወደ ሃገሪቱ የሚጓዙ መንገደኞች ከማክሰኞ ጀምሮ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ጨምሮ ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችንን አብረ ይዘው እንዳይጓዙ እገዳን አስመቀምጠች። ከሽብር ጥቃት ስጋት ጋር በተገናኘ የተወሰደው ነው የተባለው ይኸው እገዳ በግብፅ፣ ኩዌት፣ ኳታር፣ ሞሮኮ፣ ዮርዳኖስ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ እና በተባበሩት አረብ ኤመሬት የሚገኙ 10 አየር ማረፊያ ጣቢያዎች ላይ ተግባራዊ መደረጉ ታውቋል። የአሜሪካና የጸጥታ አካላት ...

Read More »

በቴኔሲ ናሽቪል ከተማ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሆቴልን የገደለ ተጠርጣሪ ለመያዝ ፍለጋው ተጠናክሮ ቀጥሏል

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) የአሜሪካ ፖሊሶች በሳምንቱ መገባደጃ ዕሁድ በዚህ በአሜሪካ የቴኔሲ ግዛት ናሽቪል ከተማ ኢትዮጵያዊ ባለሆቴሉን የገደለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ለሶስተኛ ቀን ፍለጋ አጠናክረው መቀጠላቸውን ገለጡ። የ41 አመቱ ኢትዮጵያዊ አቶ ግጠም ደምሴ  አይቤክስ የተባለውን የምግብ ቤቱን ቅዳሜ ምሽት ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ ድርጅቱን ዘግቶ በመውጣት ላይ እንዳለ ፊቱን የሸፈነ ግለሰብ በተደጋጋሚ የተኩስ ዕርምጃን በመውሰድ ግድያ መፈጸሙን የግዛቲቱ ፖሊስ አስታውቋል። የናሽቢል ...

Read More »

ከሳውድ አረቢያ ይገኛል የተባለው ገንዘብ በመቅረቱ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ተባብሷል

መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአስመጪነት የተሰማሩ ባለሃብቶች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራ መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ ቢደርሱም እንዲሁም በርካታ ፋብሪካዎችም የመለዋወጫ እቃዎችን ማስመጣት እየተሳናቸው ሰራተኞችን መቀነስ ቢጀመሩም፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ይቀርፋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ከሳውድ አረቢያ የሚገኘው ብድር እስካሁን ሊገኝ ባለመቻሉ፣ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል። የሳውዲ መንግስት በአጭር ጊዜ ብድር እስከ 1 ቢሊዮር ዶላር እንደሚያቀርብ ተስፋ ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ዞን የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ተሰማራ

መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን የካይሳ እና አካባቢው ነዋሪዎች የወረዳ ይገባኛል ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ በወረዳው እና በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ነግሷል። የነዋሪዎቹን ሕጋዊ ጥያቄዎች ሕጋዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ እስራት እና አፈና በማድረግ ወታደራዊ ሃይል እንዲሰፍር ተደርጓል። በሳላማጎ፣ በና ጸማ እና ሃመር ወረዳዎች ሽፍታዎች አሉ በሚል ምክንያት በአርብቶ አደሮች ላይ ኦፕሬሽን በሚል ዘመቻ ከፍተኛ ...

Read More »

በቂልንጦ እስር ቤት ለወራት ክስ ሳይመሰረትባቸው የቆዩ እስረኞች የረሃብ አድማ ጀመሩ

መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት 19 ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትባቸው በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ነው። እስረኞቹ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ የእስር ቤቱን አመራር ቢጠይቁም፣ እስካሁን መልስ አላገኙም። እስረኞቹ ከሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ የረሃብ አድማ በማድረግ ላይ ናቸው። እውቁ ፖለቲከኛ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በቂልጦ የረሃብ አድማ ...

Read More »

በቅርቡ ከእስር የተለቀቁት አቶ አለማየሁ መኮንን ስለ እስር ቤት ቆይታቸው ተናገሩ

መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት /ኦህዲኅ/ ሊቀመንበር አቶ ዓለማየሁ መኮንን፣ የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ አጠቃላይ 11 አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ታግተው ከተያዙበት ሕዳር 5 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ከአራት ወራት በላይ በእስር ሲሰቃዩ ቆይተው መጋቢት 7 ቀን 2009 ዓ.ም ከትግል አጋሮቻቸው ጋር በዋስ ተፈተዋል። በእስር ቤት ውስጥ ምንም ዓይነት ምግብ እንደማይቀርብላቸውና ለብቻቸው እንዲታሰሩ ...

Read More »

በሰሜን ኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች የሚፈጸመው ጥቃት ቀጥሎአል

መጋቢት ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት7 ሰሞኑን በተከታታይ ካደረጋቸው ጥቃቶች መካከል አንዱ የሆነ ጥቃት በደንቢያ ከተማ ባለፈው ቅዳሜ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈጽሟል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ጥቃቱን ተከትሎ ከተማዋ እንደገና በወታደሮች የተወረረች ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ጥቃት ፈጻሚዎችን አጋልጡ እየተባሉ ክፉኛ ተደብድበዋል። በጯሂት ከተማ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎም እንዲሁ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሟል። በደንቢያ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመው ጥቃት ...

Read More »

ብአዴን ሚስጢሮች የሚወጡት ለፓርቲው ህልውና የሚያስቡ ከፍተኛ አመራሮች በመጥፋታቸው ነው አለ

መጋቢት ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን ሚስጢሮቹ የሚባክኑት እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን እንዲጨምር ያደረገው ከፍተኛ አመራሩ በድርጀቱ ላይ እምነት እያጣ በመምጣቱ ነው ሲሉ የብአዴንና የህወሃት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ብአዴን ቅዳሜ ባካሄደው ስብሰባ ፣ ከብአዴን መሪዎች አቶ አለምነው መኮንን፣ ከህወሃት ደግሞ አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ በስልክ የተሳተፉ ሲሆን፣ ህወሃት የብአዴን ከፍተኛው አመራር እንዲሁም የክልሉ ሚዲያ እና ጋዜጠኞች ...

Read More »

የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የቲማቲም ኩባንያ በአገሪቱ የሚታየውን የቲማቲም እጥረት ተከትሎ ከፍተኛ ሽያጭ እያካሄደ ነው

መጋቢት ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና አሁን ለአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት የሚወዳደሩት የህወሃቱ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ እና በአርሲ ዞኖች ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ገዝተው የቲማቲም እርሻ እያኬዱ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች የታየውን የቲማቲም እጥረት ተከትሎ፣ ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ነው። በአዲስ አበባ ...

Read More »

በአዳማ ከተማ የውሃ እጥረት እና የመብራት መቆራረጥ ተባብሶ ቀጥሏል

መጋቢት ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዳማ ከተማ እና አካባቢዋ የውሃ እጥረት እና የመብራት መቆራረጥ ችግር ተባብሶ በመቀጠሉ ነዋሪዎቹ ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን አስታወቁ። አገልግሎት ይሰጥ የነበረው የቀድሞው የውሃ ማጣሪያ ከከተማዋ ስፋት እና ሕዝብ ብዛት ጋር ተመጣጣኝ አለመሆኑን ተከትሎ የውሃ አቅርቦቱ ላይ መስተጓጎል ያስከተለ ከመሆኑን በተጨማሪ የከተማዋ አስተዳደር ንጹሕ ውሃ ለተጠቃሚዎች ለማዳረስ ምንም ዓይነት እርምጃዎችን ሲወስድ አልታየም። የኦሮሚያ ...

Read More »