ኢትዮጵያ የአህያ ሥጋ ወደ ውጪ መላክ ጀመረች

መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዲስ አበባ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ ወይም ደብረዘይት የተገነባው የአህያ ማረጃ መጠናቀቁንና ሥራ መጀመሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ የአህያ ሥጋ ለውጪ ገበያ ማቅረብ መጀመሯን ሳምንታዊው አዲስ ፎርቹን ዘግቧል። እንደ መገናኛ ብዙሀን ሪፖርት ሻንዶንግ ዶንግ የተሰኘው የአህዮች ማረጃ ቄራ ግንባታ 80 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል። ኩባንያው የአህያውን ሥጋ የሚልከው ወደ ቬትናም ...

Read More »

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ልታስገባ መሆኗል አሳወቀች።

መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መዲናይቱን አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ የአኢትዮጵያ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች በኤሌክትሪክ ብርሀን እጦት በተቸገሩበት በአሁኑ ወቅት ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ 400 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ልታስገባ መሆኗን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ እንዳሉት ሀገራቸው 57 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ በመጠባበቂያነት ቢኖራትም የኃይል ማመንጫ ግድቦቿ ያሉባቸው አካባቢዎች በድርቁ ምክንያት በመቀነሳቸው ከፍተኛ የኃይል እጥረት አጋጥሟቸዋል። ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ለሚታወቁት ሃገራት ለስለላ የሚረዱ ቁሳቁሶችንና የጦር መሳሪያዎችን እንደሚያቀርብ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ለሚታወቁት ሃገራት ለስለላ የሚረዱ ቁሳቁሶችንና የጦር መሳሪያዎችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አንድ አለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ። ሃገሪቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለሳውዲ አረቢያ፣ ባህሬንና፣ የቤንዙዌላ መንግስታት የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሲያቀርብ መቆየቱን በመገናኛና በማህበረሰብ መብት መከበር ዙሪያ የሚሰራው ግሎባል ቮይስ የተለያዩ አካላትን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። መቀመጫውን በኔዘርላንድ አምስተርዳም ከተማ ...

Read More »

በኩዌት አንዲት ኢትዮጵያዊት ከሰባተኛ ፎቅ ላይ ስትወድቅ የሚያሳይ ቪዲዮ የቀረጸች አሰሪን በቁጥጥር ስር በማዋል ፖሊስ ምርመራ ጀመረ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2009) የኩዌት ፖሊስ አንዲት ኢትዮጵያዊት ከሰባተኛ ፎቅ ላይ ልትወድቅ ስትል የሚያሳይ ቪዲዮ የቀረጸች አሰሪን በቁጥጥር ስር በማዋል ድርጊቱን በመመርመር ላይ መሆኑን አርብ አስታወቁ። ኢትዮጵያዊቷ ከፎቁ በመስኮት ከመውደቋ በፊት “ያዙዝ” የሚል የዕርዳታ ጥሪን በተደጋጋሚ ብታሰማም አሰሪዋ ኢትዮጵያዊቷን ከመታደግ ይልቅ ሰብዓዊነት ባልተሞላበት መንገድ ፀያፍ ቃላቶችን ስትጠቀም የሚያሳይ ቪዲዮ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። ይኸው በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች በመሰራጨት ...

Read More »

የመኢአድ ፕሬዚደንት አቶ ማሙሸት አማረ ከነወንድማቸው ጋር በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2009) የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚደንት አቶ ማሙሸት አማረ ከወንድማቸው ጋር በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ታወቀ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት አቶ ማሙሸት ከወራት በፊት ከደረሰባቸው የጤና እክል ተከትሎ ጸበል በመከታተል ላይ እንደነበሩ ገልጸዋል። የአቶ ማሙሸት አማረ ወንድም የሆኑት አቶ ግዛቸው አማረ፣ ለወንድማቸው ስንቅ ለማቀበል በሄዱ ጊዜ በአንድ ላይ በኮማንድ ፖስት አባላት ታፍነው መወሰደዳቸውን ለመረዳት ...

Read More »

መንግስት በአዲስ አበባ ፈለገ-ዮርዳኖስ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ቦታ ሳይሰጣቸው የመኖሪያ ቤቶቻቸው ማፍረስ መጀመሩ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 11 በተለምዶ ፈለገ-ዮርዳኖች ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ አማራጭና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ለረጅም ጊዜ የኖሩበትን የመኖሪያ አካባቢ ማፍረስ መጀመሩን አስታወቁ። ሜክሲኮ ተብሎ ከሚጠራ አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው ዋና መንገድ ዙሪያ የሚገኙ እነዚሁ ነዋሪዎች አካባቢው ለልማት ይፈለጋል ተብለው በሃይል እንዲለቁ በመደረግ ላይ መሆኑን ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የከተማ አስተዳደሩ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዲሱ አስተዳደርና በጋምቤላ የሚገኙ ኢንቨስተሮች ውዝግብ ቀጥሏል

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2009) በ5 ቢሊዮን ብር ብክነት የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ልማት ባንክና አዲሱ አስተዳደር በጋምቤላ ከሚገኙ ኢንቨስተሮች ጋር የጀመሩት ውዝግብ ቀጥሏል። የቀድሞ የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ ባህረን የተኩት አቶ ጌታሁን ናና በጋምቤላ እርሻ ኢንቨስትመንት ላይ በተሰማሩ የትግራይ ተወላጆች ወቀሳ የቀረበባቸው ሲሆን፣ የኢሳትን ወሬ እየሰማችሁ ተሽመድምዳችኋል በማለት ለደርግና ለግንቦት 7 ኮሎኔሎች ማበደር ፈልጋችሁ ነው ወይ ሲሉ ጠየቁ። ባለፈው ቅዳሜ የኢትዮጵያ ...

Read More »

ከ30 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች በመኪና አደጋ አለቁ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት አንድ ኦራል ተሽከርካሪ ከ30 በላይ ወታደሮችን አሳፍሮ ከመተማ ወደ ቋራ ወረዳ በመጓዝ ላይ እያለ ለምለም ተራራ ላይ ሲደርስ በመገልበጡ ሁሉም ወታደሮች አልቀዋል። ምንጮች አሰቃቂ ሲሉ በጠሩት በዚህ አደጋ የአንድም ወታደር ህይወት ሊትርፍ አለመቻሉን ተናግረው፤ በከፍተኛ ሁኔታ የተቃጠሉና አካላቸው የተለያዩ ወታደሮች አስከሬን እየተለቀመ ተወስዷል። አደጋው በምን ...

Read More »

በቡሌ ሆራ ወረዳ 12 ሰዎች ተይዘው ታሰሩ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በቡሌሆራ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ጥቃት ይደርስብናል በሚል ተሸሽገው የቆዩ 12 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሰዎቹ የተያዙት ከዚህ በሁዋላ ምንም እንደማይደርስባቸው በአገር ሽማግሌዎች ማረጋገጫ ከተሰጣቸው በሁዋላ ነው። በአሁኑ ሰአት የአካባቢው ህዝብ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጮች፣ በርካታ ሰዎች አካባቢውን ጥለው እየሸሹ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ...

Read More »

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የሲቪል ሰርቪስ የምዘና ሂደት መከነ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደኢህዴግ ከፍተኛ ካድሬ በሆኑት አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ለመተግበር እየሞከረ ያለው የመሠረታዊ የሥራ ሒደት (BPR) እና የውጤት ተኮር ሥርዓት (Balanced Score Card/BSC) ምዘና መምከኑን ምንጮች ገልጹ። የምዘና ዕቅዱ በሰራተኞች ተቀባይነት አጥቶ ቢከሽፍም፣ የኢህአዴግ አገዛዝ ግን ዕቅዱን ለማስፈጸም በሚል ዛሬም ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ነው። የሚኒስቴሩ ምንጮች ...

Read More »