መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋዮቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ መጋቢት 25 ለ 26 ሌሊት ከ 7፡00 እስከ 9፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰራቫ ጣና በለስ መስኖ ፕሮጀክት ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ መሽጎ በነበርው የህውሐት መከላከያሰራዊት ላይ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት በወሰዱት እርምጃ ሁለት የገዥው ፓርቲ ወታደሮችን እና ሁለት የመከላከያ ሾፌሮችን ሲገድሉ በስድስት ወታደሮች ላይ ከባድ የመቁሰል ...
Read More »ኢህአዴግ “የመገናኛ ብዙሀንን አኮላሽቻቸዋለሁ” ሲል በግምገማው ማመኑ ተገለፀ፡፡
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሀትና የኢህአዴግ ከፍተኛ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አባይ ጸሐየ ከመገናኛ ብዙሐን አመራር እና ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዩች ጋር በነበረው ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር “መገናኛ ብዙሐንፀረ ህዝብ እና የልማት እንቅፋት እንዲሆኑአኮላሽተናቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ ችግር ከፓርቲዎች ጋር በሚደረግ ድርድርና ከግለሰቦች ጋር በመካከር አይሰተካከልም ያሉት የህወሃት አመራሩ አቶ አባይ ፤ “ብዙሐን መገናኛዎች እና ምክር ...
Read More »ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠው ታሪካዊው የጋምቤላ የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል ጽላት መዘረፉን ሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ።
መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በጋምቤላ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ታሪካዊውየሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ጽላት ማነታቸው በማይታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ምእመናን ገልጸዋል። የደብሩ ካህናት በበኩላቸው ከየካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም ቀን ጀምሮ ታቦቱ ከመንበሩ አለመኖሩን አሳውቀዋል፡፡ በ1941 ዓ.ም. በቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ሀይለስላሴ እንደተሰራ የሚነገርለት ይህ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ታቦቱ በቅርስነት ተይዞ ጥበቃ ሊደረግለት ...
Read More »መንግስት ለአባይ ግድብ ግንባታ በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ የነበረው እቅድ ችግር እንዳጋጠመው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 25 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመገንባት ባለው የአባይ ግድብ ግንባታ በተለይ በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ የነበረው እቅድ ችግር እንዳጋጠመው ገለጸ። 6.5 ሚሊዮን ዶላር ለአሜሪካ መንግስት ለመክፈልና የተመሰረተበትን ክስ ለማቋረጥ መወሰኑንም አስታውቋል። ባለፈው አመት ሰኔ ወር የአሜሪካው ሴኪውሪቴስ ኤንድ ኤክስቼንጅ (American Securities and Exchange Commission) ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካን ህግ በጣሰ መልኩ የቦንድ ሽያጭ አካሄዷል ሲል ...
Read More »በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሚገኙ 38 እስረኞች ላይ የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታ እንዲመረመር ተወሰነ
ኢሳት (መጋቢት 25 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 38 ተከሳሾች በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ የቆዩት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አቤቱታ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ። የልብ ስፔሻሊስቱን ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ 38ቱ ተከሳሾች ባለፈው አመት በነሃሴ ወር በእስር ቤቱ ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተደራራቢ ክስ ስር የሚገኙ ሲሆን፣ አቤቱታ አቅራቢዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ከተፈጸመባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መካከል የምርመራ ...
Read More »ከዋልድባ ገዳም ተቃውሞ ጋር በተገናኘ 39 የገዳሙ መነኩሴዎች መታሰራቸው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 25 ፥ 2009) በቅርቡ ለእስር የተዳረጉት የዋልድባ ገዳም መነኩሴ አባ ገብረየሱስ ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት መወሰዳቸውንና የስቃይ ሰለባ ይሆናሉ የሚል ስጋት እንዳደረበት የዋልድባን እንታደግ ማህበር ሰኞ አስታወቀ። በአጠቃላይ 39 የዋልድባ ገዳም መነኩሴዎች መታሰራቸውንም መረዳት ተችሏል። አባ ገብረየሱስ የዋልድባ ገዳሙ ለልማት መነካት የለበትም በማለት ሲያሰሙ የቆዩትን ተቃትሞ ተከትሎ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ ከሁለት ወር በፊት ታፍነው መወሰዳቸውን ...
Read More »በጎንደር ከተማ አንድ ሆቴል ውስጥ ጥቃት ተፈጽሞ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
ኢሳት (መጋቢት 25 ፥ 2009) በጎንደር ከተማ ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል ላይ ቅዳሜ ምሽት የቦምብ ጥቃት ደረሰ። ጥቃቱ የተፈጸመበት ባለሶስት ኮከብ ሆቴል በአብዛኛው የወታደራዊ አዛዥ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያርፉበት እንደኾነ እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ማራኪ ተብሎ በሚታወቀው የጎንደር ዩኒቨርስቲ አካባቢ በሚገኘው በዚሁ ሆቴል የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል። ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም። በዚሁ በፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል ...
Read More »የህወኃትና ኢህአዴግ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አባይ ጸሀዬ የመንግስትንና የፓርላማውን አሠራር አጠንክረው ነቀፉ።
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እምነት ያጣንበት ሚኒስትር ዳግም እየተሾመ ነው ያሉት አቶ አባይ፤ የመንግስት አሠራር ካልተቀየረ ይች ሀገር በእሳት ትቃጠላለች ሲሊ አስጠንቅቀዋል። ኢሳት በደረሰው የድምጽ መረጃ ላይ በፓርላማው የተለመደ የደቦና የጥድፊያ አሰራር ትችት የሰነዘሩት አቶ አባይ፤ ሹመትና በጀት ያለብስለትና ያለ እምነት በጥድፊያና በዘመቻ እየጸደቀ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ችግር ማስከተሉን ጠቁመዋል። ቋሚ ኮሚቲው ከአስፈጻሚው የመጣውን ማጽደቅ ...
Read More »ትናንት ምሽት በጎንደር ከተማ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች ከስፍራው ባደረሱን መረጃ የትናንት ምሽቱ ከፍተኛ ፍንዳታ ከሰሞኑ በከተማዋ ለሦስተኛ ጊዜ የደረሰ ፍንዳታ ነው። በከተማዋ ማዕከል ላይ በሚገኘው በፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል ትናንት ምሽት በተፈጸመው የቦምብ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ኣስካሁን የሞተ ሰው ስለመኖሩ አልተነገረም። አካባቢውን ባናወጠው በዚህ ፍንዳታ የፍሎሪዳ ሆቴል መስኮቶች መሰባበራቸውንና በሌሎችም የሆቲሉ ንብረቶች ላይ ጉዳት ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን ማራዘሙ ሕዝባዊ ቁጣውን አያቆመውም ሲል የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ አስታወቀ
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት ማራዘሙን ለዓለምአቀፉ ማህበረስብ ማስታወቁ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ሊያስቆመው አይችልም ሲል የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ መግለጫ አወጣ። ሚሊዮኖችን ከነባር ይዞታ ያፈነቀለውን የመሬት ቅርምት በመቃወም እና በአገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በማውገዝ በሰላማዊ መንገድ ገዥው መንግስትን ሲቃወሙ የነበሩትን የአማራ እና ኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ...
Read More »