የአረካ ገበያ ተቃጠለ

ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ በሆነችው አረካ ከተማ የሚገኘው የገባያ ማእከል በመቃጠሉ ከፍተኛ ንብረት ወድሟል። አብዛኞቹ ሱቆች በአቶ ሃይለማርያም የቅርብ ዘመዶችና በደኢህዴን አባላት የተያዙ እንደነበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ የእሳቱ መንስኤም የአስተዳደር በደልንና ሙስናን ከመወጋት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግምታቸውን ይገልጻሉ። የዚህ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የአስተዳደር በደል የሚፈጸምባቸው ሲሆን፣ በተለይ ወጣቶች ...

Read More »

በአማራ ክልል ካሉ ትምህርት ቤቶች 87 ከመቶ የሚደርሱት ከደረጃ በታች ናቸው ተባለ

ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቆርቋሪ እያጣ ነው ተብሎአል። መሠረታዊ የግብዓት እጥረት መኖር ፣ የመምህራን ድጋፍ ማነስ፣ የወላጆች ክትትልና ድጋፍ አለመኖር፣የተማሪዎች የመማር ፍላጎትን ከመቀነስ አልፎ 87 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች እንዲሆኑ ምክንያቶች መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መገምገሙን ገለጸ፡፡ ብዙዎቹ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ተማሪዎች ተነሳሽነት ...

Read More »

የጀግናው ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ የቀብር ስነስርዓት በቅድስተ-ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ተፈጸመ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) የሌተናል ጄነራል ጃጋማ ኬሎ የቀብር ስነስርዓት ትናንት ዕሁድ በቅድስተ-ስላሴ ቤ/ክርስቲያን በርካታ ሰዎች በተገኙበት ተፈጸመ። በጣሊያን የወረራ ጦር ጊዜ ባደረጓቸው ትግሎች በርካታ ድሎች መጎናጸፋቸው የሚነገርላቸው ሌተናል ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ ባደረባቸው ህመም ሳቢያ የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ በ96 አመታቸው ባለፈው አርብ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። እሁድ በተከናወነው የቀብር ስነ-ስርዓት የቤተሰብ አባላት እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ አርበኞች ...

Read More »

በወህኒ ቤት ሰቆቃ እየፈጸሙ ያሉት የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) የኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ከ90 በመቶ በላይ በትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር መውደቁን፣ በወህኒ ቤቱ ሰቆቃ የሚፈጽሙት በተመሳሳይ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ገለጸ። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረውና ከአንድ አመት በላይ በወህኒ ቤት ያሳለፈው አቶ ሃብታሙ አያሌው ይህንኑ የተናገረው በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በተዘጋጀ መድረክ ላይ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። በቨርጂኒያ አርሊንግተን ከተማ ሼራተን ሆቴል ዕሁድ ...

Read More »

በሰሜን ተራሮች የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎችን ከፓርኩ ለማስወጣት የተጀመረው ዘመቻ ውዝግብ ቀሰቀሰ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) በህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎችን ከፓርኩ ለማስወጣት የጀመረው ዘመቻ ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ አለመግባባት ቀሰቀሰ። በዚሁ ብሄራዊ ፓርክ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች በፓርኩ ውስጥ ለሚገኙ ብርቅዬ የዱር አራዊት ቁጥር መመናመን ምክንያት ሆነዋል በሚል አገዛዝ ከሶስት አመት በፊት ነዋሪዎችን የማስወጣት ሂደት መጀመሩ ይታወሳል። በመጀመሪያ ዙር ከተካሄደው በዚሁ ዘመቻ ...

Read More »

በጋምቤላ ክልል የታፈኑትን ህጻናት ለማስመለስ በቂ ትኩረት አልተሰጠም ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) ከጋምቤላ ክልል በቅርቡ ታፍነው የተወሰዱት ህጻናትን ለማስመለስ መንግስት በቂ ትኩረት አልሰጠም ሲሉ በጋምቤላ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት መከበር ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ገለጹ። የኢትዮጵያ መንግስት ታፍነው የተወሰዱ ከ40 በላይ ህጻናትን ለማስለቀቅ ቃል ቢገባም፣ እስካሁን ድረስ የተመለሱ አለመኖራቸውንና ጥቃቱ በነዋሪው ዘንድ ስጋትን ማሳደሩን የደቡብ ሱዳን የዜና አገልግሎት ነዋሪዎችንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላትን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። ባለፈው ...

Read More »

የማላዊ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸው 56 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) የማላዊ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ 56 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰኞ ገለጸ። በየወሩ በሃገሪቱ ለእስር የሚዳረጉ ስደተኞች ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑንና ድርጊቱ አሳሳቢ መሆኑን የማላዊ ኢሚግሬሽን ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። 56ቱ ኢትዮጵያውያን ካሮንጋ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ መዳረሻቸው ወደ አልታወቀ ቦታ በጭነት ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እንዳሉ በጸጥታ ሃይሎች መያዛቸውን ማላዊ 24 የተሰኘ ...

Read More »

በግብፅ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 44 ሲሞቱ ከ 100 በላይ መቁሰላቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) በግብፅ በሁለት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች ላይ ዕሁድ በተፈጸመው የቦንብ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 44 መድረሱንና ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በቤተ-ክርስቲያኖቹ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ የግብፅ ፕሬዚደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጉዳዩን በአግባቡ እንደሚይዙት ገልጸዋል። ከተለያዩ የአለም አቀፍ ሃገራትና ተቋማት እየቀረበ ያለውን ውግዘት ተከትሎ ግብፅ የሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ እንዲታወጅ ...

Read More »

በቆላድባ አንድ ወታደር የ14 ዓመት ልጃገረድ መድፈሩን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን አሰማ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው የሚታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ከተላኩት ወታደሮች መካከል አንዱ የሆነው ለጊዜው ስሙ ያልታወቀው ወታደር፣ እሁድ ሚያዚያ 1 ፣ ከጓደኛው ጋር በመሆን አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ በጉልበት ወስዶ ደፍሯታል። ታዳጊዋ ደም እየፈሰሳት ለአካባቢው ሰዎች መናገሩዋን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን እያሰማ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርቷል። ሰቀልት ክፍል ወይም ቀበሌ ዜሮ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነቸው ...

Read More »

በምስራቅ ጉጂ በረሃብና በበሽታ ህጻናት እያለቁ ነው ተባለ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ጉጂ ዞን ቆላ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ድርቅ መግባቱንና ይህንን ተከትሎም ወረርሽኝ በመከሰቱ የበርካታ ህጻናት ህይወት እያለፈ ነው ። በተለይ በዞኑ በሚገኙ 6 ወረዳዎች የሚላስ የሚቀመስ የለም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ህጻናት በተቅማጥና ትውከት እያለቁ ነው ይላሉ። በሃራቀሎ፣ ሉባን፣ ሰባ ቦሩ እና ደዋ ቀበሌ የሚኖሩ ነዋሪዎች የሚደርስላቸው ...

Read More »