ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ አንዳንድ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለኦህዴድ ማጠናከሪያ በሚል ለአመታት ያለፈቃዳቸው ከደሞዛቸው የሚቆረጠው ገንዘብ እንዲቆም ጥያቄ አቅርበዋል። በክልሉ ውስጥ የሚኖር የየትኛውም ብሄር ተወላጅ ከደሞዙ 5 በመቶ ለኦህዴድ በግዴታ ይከፍላል። በጅማ ዞን በሚገኙት ሰቃ፣ ደዶ እና ጎማ ወረዳዎች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ከእንግዲህ ክፍያ አንከፍልም በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፣ ከእንግዲህ ደሞዛችን በግድ የሚቆረጥ ከሆነ ...
Read More »ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ 11 ሚሊዮን ሕዝብ ለርሃብ ተጋላጭ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ አገራት በተከሰተ ድርቅ 11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ በተባበበሩት መንስግታት ድርጅት የሕጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ እና የዓለም የምግብ ድርጅት በጋራ አስታውቀዋል። ድርቁ በደቡብ ሱዳን ከ100 ሺ በላይ ነዋሪዎችን ሲያጠቃ፣ ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው። በደቡብ ሱዳን ከድርቁ በተጨማሪ የእርስበርስ ጦርነቱ በነዋሪዎቹ ...
Read More »የብሪታኒያ ኩባንያ በአፋር ክልል ወርቅ ለማውጣት የደረሰው ስምምነት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ተጓትቶብኛል አለ
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ የማዕድን ኩባንያ በአፋር ክልል ወርቅን ለማውጣት የደረሰው ስምምነት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት መጓተቱን ማክሰኞ ገለጸ። ከፊ ሚነራል የተባለው ይኸው ኩባንያ፣ ባለፈው አመት የወርቅ ቁፋሮን በክልሉ የቱሉ ካፒ ፕሮጄክት ለመጀመር ከመንግስት ጋር ስምምነት የደረሰ ሲሆን፣ ፕሮጄክቱ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት እንደሚፈልግ ከኩባንያው የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ይሁንና ኩባንያው ስራውን ለመጀመር ...
Read More »በወላይታ ዞን አረካ የሚገኝ አንድ የገበያ ቦታ መቃጠሉ ተነገረ
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ አረካ የሚገኝ አንድ የገበያ ቦታ መቃጠሉ ተነገረ። የቃጠሎው ምክንያት በውል ባይታወቅም በህዝቡ ውስጥ ከንግድና ከአስተዳደር በደል የመነጨ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የገበያ ቦታው እና በዚያው የነበሩ ሱቆች በደህዴን ካድሬዎች እና በአቶ ሃይለማሪያም ደጋፊዎች የተያዙ ነበሩ። በዚሁ ሳቢያ ወጣቶች የስራ ዕድል ባላገኙበት ሁኔታ ጥቂቶች ተጠቃሚ መሆናቸው በህዝቡ ...
Read More »የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች LC ለመክፈት 100 % ገንዘብ በባንክ እንዲያስቀምጡ ተጠየቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) የብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) ለመክፈት ያስቀመጠውን የ30 በመቶ መጠን ወደ 100 ፐርሰንት ከፍ አደረገ። ባንኩ የወሰደውን ይህንኑ ዕርምጃ ተከትሎ አስመጪ ነጋዴዎች በግል ባንክ ያስቀመጡትን ገንዘብ በማውጣት ወደ ብሄራዊ ባንክ ለማስገባት መገደዳቸውን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በበኩላቸው ዕርምጃው የግል ባንኮች የገንዘብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው በማድረግ ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስጋት አሳድሮብኛል ሲል የአውሮፓ ህብረት ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተገናኘ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለእስር መዳረጉና እስራቱ አሁንም ድረስ መቀጠሉ ስጋት አሳድሮብኛል ሲል ማክሰኞ ገለጸ። ሃሳቡን የመግለጽ መብት እንዲከበር ህብረቱ አሳስቧል። ህብረቱ በሃገሪቱ ባሉ የሰብዓዊ መብት አያያዞችና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር በአውሮፓ ህብረት ልዩ የሰብዓዊ መብቶች መልዕክተኛ በሆኑ ስታርቮስ ላምብሪኒደስ የተመራ የልዑካን ቡድን ባለፈው ሳምንት ...
Read More »ባለፈው አመት በተለያዩ ሃገራት ከ3 ሺ በላይ ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈጸመባቸው
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) ባለፈው የፈረንጆች አመት 2016 ቻይናን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከ 3ሺ በሚበልጡ ላይ የሞት ቅጣት መፈጸማቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማክስኞ ይፋ አደረገ። ቻይና በአለማችን ካሉ ሃገራት የሞት ቅጣቱን በብዛት በመፈጸም በግንባር ቀደምትነት የተቀመጠች ሲሆን፣ ኢራን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና ፓኪስታን ከሁለት እስከ አምስተኛ ደረጃ ይዘዋል። ባለፈው የፈረንጆች አመት ከ3ሺ በላይ ሰዎች ላይ ተፈጻሚ ከሆነው ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 ተጨማሪ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈጸሙን የሚገልጸው አርበኞች ግንቦት7 ፣ መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓም ከሱዳን ተነስቶ ወደ ጎንደር በማቅናት ላይ የነበረ የሱዳን ታርጋ ያለው መኪና ላይ በፈጸመው ጥቃት የመኪናውን ከፊል አካል ማቃጠሉን ገልጿል። ጥቃቱ የተፈጸመው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ካለበት አካባቢ ነው። እንዲሁም ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓም አምባጊዮርጊስ አካባቢ የአገዛዙ ሰላይ ...
Read More »በይርጋለም ከተማ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ ከ15 በላይ የፋይናንስና የማዘጋጃ ሰራተኞች በሙስና በሚል ተሰብስበው ታስረዋል። እርምጃው የተወሰደው በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ነው። የድርጅተ ሰራተኞች እንደገለጹት በሙስና የተዘፈቁት ዋናዎቹ አመራሮች ሆነው እያለ እነሱን ወደ ሌሎች ቦታዎች በማዛወር፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ተራ ሰራተኞች ይዘው አስረዋል። እስሩን ተከትሎ በሰራተኞች ዘንድ አለመረጋጋት መፈጠሩን ሰራተኞች ተናግረዋል። ...
Read More »ኦብነግ ከሶማሊ ልዩ ሃይልና ከመከላከያ ጋር መዋጋቱ ተዘገበ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦጋዴን ኒውስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሁለት ቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊት በሚደገፈው የሶማሊ ልዩ ሃይልና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት መካከል በደጋሃቡር አውራጃ፣ በብርቆት ወረዳ ልዩ ስሙ ሊዲለይ በሚባል ስፍራ ላይ በተደረገ ውጊያ 3 አዛዦችን ጨምሮ 17 ወታደሮች መገደላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። 21 ቁስለኛ ወታደሮች ደግሞ በአየር ወደ ጅግጅጋ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን እማኞች እንደገለጹለት ...
Read More »