ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደዘገበው ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች በተለይም በፒያሳ አካባቢ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት የሚታዩ ሲሆን ፣ ምሽት ላይ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው በሚያመሩበት ጊዜ ፍተሻ ያደርጋሉ። አንዳንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ነዋሪዎችን በሚፈትሹበት ወቅት ‘ አይዟችሁ አትፍሩ ታዘን ነው የምንፈትሸው እንደሚሉ” ወኪላችን ገልጿል። የገዢው ፐርቲ የደህንነት አባላት በአሉን ...
Read More »በኢትዮጵያ በረሃብ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ ተቋም ከመጋቢት እስከ ግንቦት ወራት ድረስ የሚጥለው የዝናብ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ20 እስከ 30 ቀናት ዘግይቶ እንደሚጀምር እና የዝናቡም መጠን በአማካኝ ከነበረው አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል በወርሃዊ ሪፖርቱ ገልጿል። በድርቅ ክፉኛ ተጠቂ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የዝናብ ስርጭቱ ከ30 እስከ 40 ቀናት ዘግይቶ ይጥላል ...
Read More »የተመድ የልማት ፕሮግራም ኢትዮጵያን በመጨረሻዎች ደሃ አገራት ደረጃ አስቀመጠ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእየለቱ ብዙ የሚባልለት የኢትዮጵያ ባለሁለት አሃዝ ኢኮኖሚ እድገት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራምን እጅግም አልመሰጠው። ዘንድሮም ድርጅቱ አገሪቱን በአለም እጅግ ድሃ ከሚባሉ አገራት ተራ መድቧታል። ምንም እንኳ ባለፉት 25 ዓመታት መሻሻሎች ቢኖሩም ፣ ኢትዮጵያ በብዙ መስፈርቶች አሁንም እጅግ ዝቅተኛ ሰብአዊ ልማት ( Low Human Development Category) ካላቸው አገራት ተርታ ትመደባለች ያለው ...
Read More »በይርጋለም የታሰሩት የመንግስት ሰራተኞች በእስር እንዲቆዩ ውሳኔ ተላለፈባቸው
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ በአንድ ጊዜ ከ10 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ የሲዳማ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰራተኞች ያቀረቡትን የዋስ መብት ጥያቄ ባለመቀበል ለተጨማሪ 10 ቀናት በእስር ቤት እንዲቆዩ ወስኗል። በግለሰቦቹ ላይ የቀረበው ክስ የበሉትን አበል አላወራረዱም የሚል መሆኑን ችሎቱን የተከታተሉ ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ግን በጅምላ የተደረገው እስር ...
Read More »አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ የሚፈልጉ ወረዳዎች ቁጥር ወደ 364 አሻቀበ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በመባባስ ላይ ባለው አዲስ የድርቅ አደጋ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ የሚፈልጉ ወረዳዎች ቁጥር ወደ 364 ማሻቀቡ ተገለጠ። ሲጠበቅ የነበረው የበልግ ዝናብ በሚፈለገው መጠን ባለመጣሉ ምክንያት 5.6 ሚሊዮን የሆነው የተረጂዎች ቁጥር በቀጣዮቹ ጥቂት ወራቶች እንደሚጨምር የአደጋ መከላከልና አስተዳደር ኮሚሽን ማስታወቁን የቱርኩ ዜና አገልግሎት አናዱሉ ዘግቧል። ከአንድ ወር በፊት በድርቁ የተጎዱ ወረዳዎች ቁጥር ወደ 240 አካባቢ እንደነበር ...
Read More »የስነምግባር ጉድለት ተገኝቶባቸዋል የተባሉ ዳኞች ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ መወሰኑ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2009) የስነ ምግባር ጉድለት ተገኝቶባቸዋል የተባሉ አራት የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞች ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሃሙስ ወሰነ። የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አራቱ ዳኞች ከፍተኛ የስነ-ምግባር ጉድለት ታይቶባቸዋል ሲል ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ለምክር ቤቱ ጥያቄን አቅርቦ እንደነበር ታውቋል። ለመደበኛ ስብሰባ ተሰይሞ የነበረው ምክር ቤቱ ያለምንም ተቃውሞ አራቱ የፌዴራል ዳኞች ከስራቸው እንዲሰናበቱ የመጨረሻ ውሳኔ ማስተላለፏን የአገዛዙ መገናኛ ...
Read More »የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ግጭት ዕልባት አለመሰጠቱ የአፍሪካ ቀንድን መረጋጋት አደጋ ውስጥ ገብቷል ሲል አውሮፓ ህብረት አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2009) ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸው ያለውን የድንበር ግጭት ዕልባት አለመስጠታቸው የአፍሪካ ቀንድን መረጋጋት አደጋ ውስጥ ከቶታል ሲል የአውሮፓ ህብረት ሃሙስ ስጋቱን ገለጠ። የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን የሁለቱ ሃገራት የድንበር ይገባኛል ጥያቄን እልባት ለመስጠት ውሳኔ ያስተላለፈበትን 15ኛ አመት አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው ህብረቱ፣ ጉዳዩን የአህጉራዊ ትብብርና ልማትን ለማጠናከር በተያዘው እንቅስቃሴ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አመልክቷል። በሁለቱ ሃገራት መካከል የተቋቋመው ...
Read More »የኢትዮጵያ ገበሬዎች በአል-ፋሻጋ አካባቢ ዘልቀው ገብተዋል ሲል የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ቅሬታ አቀረበ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ገበሬዎች አጨቃጫቂ በሆነው የአል-ፋሻጋ አካባቢ ወደ ሱዳን ግዛት ዘልቀው ገብተዋል ሲል የሱዳን መከላከያ ሚኒስቴር ሃሙስ ቅሬታን አቀረበ። በዚሁ የድንበር ዙሪያ የሚኖሩ የሁለቱ ሃገራት ዜጎች በዓል-ፋሸጋ ስር የሚገኝ ሰፊ የእርሻ ቦታ ላይ ለአመታት የቆየ የይገባኛል ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። በድንበሩ አዋሳኝ አካባቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የሱዳን የፀጥታ ሃይሎች በተደጋጋሚ ወደ ይዞታቸው እየመጡ መሬቱ ለሱዳን የተሰጠ ...
Read More »ኢህአዴግ “በአገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ በጠባብነትና ትምክተኝነት የተነሳ ነው” ሲል ራሱን ሸንግሎ ተሃድሶውን ማጠናቀቁን አስታወቀ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያና አማራ እንዲሁም በአንዳንድ የደቡብ ክልሎች የታዩትን ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተከትሎ አገሪቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስአዋጅ አውጥቶ በወታደራዊ ሃይል እየገዛት ያለው ኢህአዴግ፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ ብሎ ያስቀመጠውን ጥልቅ ትሃድሶ ሲያጠናቅቅ፣ ለተቃውሞው መነሻ በውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃንን ተጠያቂ አድርጓል። ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶው በድል ተጠናቋል ቢልም ህዝቡ ግን ተሃድሶው የተባለውን ከቁም ነገር አልቆጠረውም። የኢህአዴግ ምክር ቤት ...
Read More »ታጋዮች በበለሳ ወረዳ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሙ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ለኢሳት በላኩት መግለጫ በበለሳ ወረዳ ባጃየ ንኡስ ወረዳ ሚያዚያ 4 ቀን 2009 ዓም ሌሊት ላይ በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ታጋዮቹ ለግማሽ ሰአት ያክል አካባቢውን መቆጣጠራቸውንና ያለምንም ጉዳት ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ጥቃቱን በተመለከተ በገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ መልስ የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ ዘመን በመስተዳድሩ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ...
Read More »