ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል የሚፈጽሙትን ጥቃት ለመከላከል በአካባቢው እንደሰፈረ መንግስት ቢገልጽም፣ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከቀናት በፊት በሶስት ወረዳዎች አዲስ ጥቃት ፈጸሙ። ቁጥራቸው ያልታወቀው የጎሳ ታጣቂዎች መጋቢት 25 እና ሚያዚያ 1 ቀን 2009 አም የኢትዮጵያ ድንበርን በመዝለቅ በጎድ ጆርና ዲማ ወረዳዎች ጥቃት ማድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ መምሪያ አስታውቋል። ...
Read More »የደህንነት ሰራተኛው ለኢሳት ሚስጢራዊ መረጃ ሰጥተሃል በሚል ታስሮ እየተሰቃየ ነው
ሚያዝያ ፲ (አሥር) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ኢጄንሲ (ኢንሳ) ውስጥ የደህንነት ሰራተኛ የሆነው ጸጋየ ተክሉ የተባለ ግለሰብ ለኢሳት መረጃ ታቀብላለህ በሚል በቂሊንጦ እስር ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል። ጸጋዬ በ2003 ዓም በመረጃ መረብ ውስጥ በሚሰራበት ወቅት ከኢሳት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የድርጅቱን ሚስጢር ለኢሳት ሰጥቷል የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን፣ በማስረጃነትም ኢሳት ከሌላ ግለሰብ ጋር ያደረገውና የራሱ ...
Read More »በኦሮምያና አማራ ክልሎች የተፈጸመው ጭፍጨፋ እንዲጣራ የቀረበውን ጥያቄ ኢህአዴግ ውድቅ አደረገው
ሚያዝያ ፲ (አሥር) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች ተነስቶ የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች ያደረሱትን ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገኖች ለማጣራት ያቀረቡትን ጥያቄ ኢህአዴግ ውድቅ አድርጎታል። ቢቢሲ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጠቅሶ እንደዘገበው በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችም ሆነ በመንግስታት የቀረበውን ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ የማቋቋም ሃሳብ በአገዛዙ በኩል ተቀባይነት አላገኘም። አቶ ...
Read More »አርሶአደሮች በደረሰኝ እየተጭበረበሩ ነው ተባለ
ሚያዝያ ፲ (አሥር) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት የቁም ከብት በሚሸጡ አርሶአደሮች ላይ ያወጣው ተጨማሪ ክፍያ አርሶአደሮችን ለብዝበዛ እየዳረገ መሆኑን ገዳቱ የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ቀደም ብሎ በአንድ የቁም ከብት 3 ብር ይከፈልበት የነበረው ክፍያ ወደ 10 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አርሶአደሮች ቢቃወሙትም ሰሚ አላገኙም። ባለፈው ሳምንት በጉራጌ አካባቢ ገንዘቡን የሚሰበስቡ ሰዎች ከአርሶአደሮች በከብት 15 ብር እየተቀበሉ፣ ደረሰኙ ...
Read More »በፒያሳ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ከመኖሪያ ቀያቸው ሊነሱ መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚኖሩ 10ሺ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ከመኖሪያ ቀያቸው ሊነሱ መሆኑ ተገለጸ። ከተቆረቆረ ረጅም ጊዜ እንደሆነ በሚነገርለት በዚሁ አካባቢ በርካታ በቅርስነት መፍረስ የሌለባቸው ህንጻዎች ያሉ ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና የታሪክ ምሁራን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል። አካባቢውን በቀጣዮቹ ስድስት ወራቶች ሙሉ ለሙሉ ለማፍረስ ሃላፊነት የተሰጠው ...
Read More »ከህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ 669 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2009) በኦሮሚያክ አማራና የደቡብ ክልሎች ሲካሄድ ከቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ 669 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማክሰኞ ገለጸ። በጉዳዩ ዙሪያ ያካሄደውን ምርመራ አስመልክቶ ሪፖርቱን ለፓርላማ ያቀረበው ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በቢሾቱ ከተማ ከእሬቻ በዓል አከባባር ጋር በተገናኘ የደረሰውን የሞት አደጋ ጨምሮ በተለያዩ ዞኖች የተፈጸሙ ግድያዎችን አቅርቧል። በኦሮሚያ ክልል 15 ዞኖች እና 91 ከተሞች በአማራ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የተመድና የአውሮፓ ህብረት በአገሪቱ የተፈጸሙ ግድያዎችን ለማጣራት ያቀረበውን ጥያቄ እንደማይቀበል አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ምክንያት የሆነውን ግድያ ለማጣራት ያቀረቡትን ጥያቄ እንደማይቀበል በይፋ ምላሽ ሰጠ። ሁለቱ አለም አቀፍ ተቋማት ባለፈው አመት በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሃይል ዕርምጃ በመውሰድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ሲገልጹ ቆየተዋል። ይኸው የጸጥታ ሃይሎች ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል ...
Read More »የአህያ ቄራ ለመዝጋት የተወሰደውን ዕርምጃ በመቃወም የቻይናውን ኩባንያ ጉዳዩን ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2009) የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚገኘውን የአህያ ቄራ ለመዝጋት የወሰደውን ዕርምጃ በመቃወም የቻይናውን ኩባንያ ጉዳዩን ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው ማክሰኞ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የፋብሪካው መዘጋትን በተመለከተ እስካሁን ድረስ የሰጠው ምላሽ ባይኖርም የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የአህያ ማረጃ ቄራው እንዲዘጋ መወሰኑ ተገልጿል። ይሁንና የከተማው የአስተዳደር ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም የቄራው ባለቤት የሆነው የቻይናው ሻንዶንግ ዶንግ ኩባንያ ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አንድ ኢትዮጵያዊን ያቃጠሉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 9 ፥ 2009) የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አንድ ኢትዮጵያዊ በገዛ ሱቁ ውስጥ በእሳት ተቃጥሎ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ሰኞ አስታወቀ። አሰቃቂ የተባለው ይኸው የወንጀል ድርጊቱ በምስራቃዊ የኬፕ ግዛት ስር በምትገኘው የምስራቅ ለንደን ከተማ አቅራቢያ ቅዳሜ ምሽት ላይ መፈጸሙን የደቡብ አፍሪካ የማሰራጫ ኮርፖሬሽን (SABC) ዘግቧል። ፖሊስ ድርጊቱ በምን ምክንያት ሊፈጸም እንደቻለ መረጃ አለመገኘቱን ገልጾ፣ የአካባቢው ...
Read More »የታንዛኒያ ፖሊስ በህገወጥ ገብተዋል የተባሉ 66 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 9 ፥ 2009) የታንዛኒያ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገ-ወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ 66 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ። ስደተኛ ኢትዮጵያውያኑ በአንድ ተሽከርካሪ ሆነው በመጓጓዝ ላይ እንዳሉ ከነዋሪዎች በደረሰ ጥቆማ በጸጥታ አባላት ሊያዙ መቻላቸውን ዘ-ሲቲዝን የተሰኘ የታንዛኒያ ጋዜጣ ሰኞ ዘግቧል። የሃገሪቱ የኢሚግሬሽን መምሪያ በበኩሉ በተለያዩ ጊዜያው ወደ ታንዛኒያ በህገ-ወጥ የሚገቡ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አስታውቀዋል። የምቤያ ...
Read More »