ከፊ ሚነራል የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ስትርሊግን እሴት ታክስ ተመላሽ ከመንግስት መቀበሉን ገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል የወርቅ ማውጣት ስራውን ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ከፊ ሚነራል ኩባንያ የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ (ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ) የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመላሽ ከመንግስት መቀበሉን አርብ አስታወቀ። በለንደን አለም አቀፍ የአክሲዮን ንግድ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው ይኸው ድርጅት የቱሉ ቆጲ  ፕሮጄክቱ ከሌላ ኩባንያ በተረከበ ጊዜ ያለአግባብ የድርጅቱን የቫት ክፍያ እንድፈጸም ተደርጊያለሁ ሲል ከወራት በፊት ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና ግድያዎችን ለመመርመር ጥያቄ ሲያቀርብ የቆየው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ። የኮሚሽኑ ሃላፊ ዘይድ ራድ አል-ሁሴን በቀጣዩ ሳምንት ከሚያዚያ 24 እስከ 26 ፥2009 አም ድረስ በአዲስ አበባ ቆይታ እንደሚኖራቸው ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኮሚሽኑ ሃላፊ ራድ አል-ሁሴን በሃገሪቱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ለአንድ አመት ያህል ...

Read More »

በበለና እና በአማሮ ወረዳዎች መካከል በተነሳ ግጭት የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በደቡብ አካባቢ በሰገን ዞን በአማሮ ወረዳ እና አጎራባች በሆነው በጉጂ ዞን ውስጥ በሚገኘው በላና ወረዳ በተነሳ ግጭት የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው። በአካባቢው የተነሳውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦች ለእንስሳት መኖና ውሃ በማጣታቸው ከአካባቢው አካባቢ መሰደዳቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ግጭት መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ከተጀመረበት ካለፉት 4 ...

Read More »

የይርጋለም መምህራን ለአባይ ቦንድ በግዳጅ እንዲገዙ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በይርጋለም ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለአባይ ግድብ ግንባታ በግዳጅ እንዲያወጡ መጠየቃቸውን ከተቃወሙ በሁዋላ፣ ዛሬ አርብ ደግሞ የይርጋለም መምህራን ለግድቡ እንዲያዋጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ መምህራን ተቃውመውታል። “መምህራኑ እኛ ያለን ዲግሪ ነው፣ ወረቀት ነው፣ ለራሳችን የሚሆን ፍጆታም የለንም” በማለት ተቃውመውታል። የካቢኔ ስብሰባ ላይ “የመንግስት ባለስልጣናትን ልብሳቸውንና ሰውነታቸውን ብታዩት ደረጃውን የጠበቀ ነው፣ ማሰብ ግን ...

Read More »

የተመድ የሰብዓዊ መብት ካውንስል ሃላፊ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ዋና አዛዥ የሆኑት ዘይድ ራድ አል ሁሴኒ በመጪው ሳምንት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ድርጅቱ አስታውቋል። የእሳቸው ጉብኝት ከመካሄዱ አስቀድሞ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ያለቁበት ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበውን ጥያቄ፣ ...

Read More »

በሶማሊያ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የኬንያ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ከመጠን በላይ ሃይል ተጠቅመው ዜጎችን መግደላቸውን ሪፖርቶች አጋለጡ

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬኒያ እና ኢትዮጵያ ወታደሮች አልሸባብን ለማደን በሚል ምክንያት ድንበር አቆራርጠው ወደ ሶማሊያ ግዛት በመግባት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከመጠን በላይ የሆነ የሃይል እርምጃዎችን መውሰዳቸውን በሶማሊያ የተሰማሩ የረድኤት ድርጅቶች ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ባቀረቡት ሪፖርቶች አጋልጠዋል። በሶማሊያ ጌዶ ግዛት ውስጥ ከ2015 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የኬንያ አየር ሃይል፣ አርብቶ አደሮች በተሰማሩባቸው አካባቢዎች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜያት ድንበር ...

Read More »

የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደጎንደር ከተማ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) በጎንደር ከተማ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ አሜሪካ ዜጎቿ ወደ አካባቢው በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ ዕርምጃን እንዲስወዱ ሃሙስ አሳሰበ። በተያዘው ወር ብቻ አራት የእጅ ቦምቦች ጥቃት መድረሱን ያረጋገጠው በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ከሁለት ቀን በፊት በአንድ የቱሪስቶች ማረፊያ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ማስረዳታቸውን ...

Read More »

በህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት የተገደሉት የሟች ቤተሰቦችን ካሳ ለመስጠት ምዝገባ ተጀመረ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) በመንግስት የተቋቋመው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ የወጣውን የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢ የሟች ቤተሰቦችን ካሳ ለማግኘት ተመዝገቡ የሚል እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል። በዚህም የፌዲራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አዛዦችን ከተጠያቂነት ነጻ በማድረግ የአካባቢ ሚሊሺያ ታጣቂዎችና ሃላፊዎችን ለመክሰስ ጠበቃ እንደተቀጠላቸውም ተነግሯቸዋል። ከባህር ዳር ለኢሳት በደረሰው መረጃ መሰረት በሃምሌ 1 ፥ 2008 ብቻ ከመቶ ሰዎች በላይ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ በኢሳት ላይ የተመሰረተውን ክስ የአሌክሳንድሪያ ከተማ ፍ/ቤት ውድቅ አደረገው

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ በኢሳት ላይ የተመሰረተውን ክስ የአሌክሳንድሪያ ከተማ ፍ/ቤት ውድቅ አደረገ። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በገንዘብ ድጋፍ የሚያደርላቸው ግለሰቦችና አካላት በአሜሪካ ፍ/ቤቶች በኢትዮጵያውያን ተቋማት ግለሰቦች ላይ የመሰረቱት ክስ የቀጠለ ቢሆንም፣ እንደተለመደው በዚሁ ሳምንት ውድቅ መደረጉ ያበሳጫቸው አንድ ዲፕሎማት ነኝ ያሉ በአደባባ ዘለፋ ሲያካሄዱ ተደምጠዋል። በኢሳት፣ በኢሳት የቀድሞ ማኔጂንግ ዳይረክተር አቶ ...

Read More »

የህዋ ሳይንስ ምሁር ዶ/ር ለገሰ ወትሮ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) ታዋቂው የህዋ ሳይንስ ምሁር ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ለገሰ ወትሮ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በአስትሮ ፊዚክስ ሙያ የላቀ አስተዋጽዖ ያደረጉት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር በመሆን አገልግለዋል። የተለያዩ የአለም አቀፍ ሽልማቶች ባለቤትም ነበሩ። በኢትዮጵያ የህዋ ሳይንስ እንዲጎለብት የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ቀርጸው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ ማህበርን ከመሰረቱት ምሁራን እና የሙያ ...

Read More »