የኢሳት 7ኛ አመት በሙኒክ ጀርመን በተሳካ ሁኔታ ተከበረ

ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢሳት አለማቀፍ የድጋፍ ኮሚቴ የበላይ መሪነት እና በሙኒክ የኢሳት ቤተሰቦች የተዘጋጀው የኢሳት 7ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አዘጋጆች ገልጸዋል። በእለቱ የክብር እንግዳ ሆነው የቀረቡት ከአሜሪካ የቢቢኤን ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድና የኢሳት ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ነበሩ። ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ፣ ባለፉት 25 አመታት የህወሃትን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አራት ም/ፕሬዚደንቶቹን ከሃላፊነት አነሳ

ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካሉት አምስት ምክትል ፕሬዚደንቶች አራቱን ማክሰኞ ሚያዚያ 24 ፥ 2009 ጀምሮ ከሃላፊነት አነሳ። አቶ ታደሰ ሃቲያ የክሬዲት (ብድር) ማኔጅመንት ምክትል ፕሬዚደንት፣ አቶ ተካ ይብራህ፣ የኮርፖሬት አገልግሎት፣ አልማዝ ጥላሁን የፋይናንስና ባንኪንግ ማኔጅመንት እንዲሁም አቶ ደረጀ አውግቸው የድጋፍ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚደንቱ ከሃላፊነታቸው የተነሱ ባለስልጣናት መሆናቸውን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ከስልጣናቸው በተነሱ ምክትል ፕሬዚደንቶች ምክትል ...

Read More »

የውጭ ምንዛሪ እጥረት በድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያደረሰ ነው ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተከሰተው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በትልልቅ ድርጅቶች ላይም ከፍተኛ ተፅዕኖ ማምጣቱ ተገለጸ። በዚህም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ባጋጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ አጠቃላይ ገቢው ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች በ1.5 ቢሊዮን ብር መቀነሱን አስታወቀ። ይኸውም መንግስታዊ ተቋም በዘጠኝ ወራቶች ውስጥ 14.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰባሰብ ቢያቅድም በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት 11.8 ቢሊዮን ብር አካባቢ ብቻ ማግኘቱን ...

Read More »

የአቶ አሰፋ ጫቦ ቀብር የሰነ-ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ታወቀ

ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) የአቶ አሰፋ ጫቦ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን አርብ በአዲስ አበባ ቅድስ ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ታወቀ። አስከሬኑ ማክሰኞ ከዳላስ አሜሪካ የተነሳ ሲሆን፣ ሃሙስ ከሰዓት አዲስ አበባ እንደሚደርስም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል። ሚያዚያ 5 ቀን 2009 አም በ73 አመታቸው በዩ ኤስ አሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ዳለስ ከተማ ያረፉት አቶ አሰፋ ጫቦ፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 21 ፥ 2009 በዳለስ ቅዱስ ...

Read More »

በሳውዲ አረቢያ ህጋዊ ፈቃድ የላችሁም ተብለው እንዲወጡ ከተጠየቁት መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተነገረ

ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ ፈቃድ የላቸውም በሚል በ90 ቀናት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በማድረግ ላይ ካሉት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተገለጠ። የሳውዲ መንግስት ባለፈው ወር ተግባራዊ ባደረገው በዚሁ አዲስ መመሪያ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው ይወጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከ300 ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ማይግራንትስ ራይትስ (Migrants’ Rights) የተሰኘ አለም ...

Read More »

ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ የሃገር ገጽታ ሊያበላሽ ይችላል በሚል ችላ መባሉ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እያደረሰ ያለው ጉዳት የሃገሪቱን ገጽታ ሊያበላሽ ይችላል በሚል በመንግስት ችላ ተብሎ ቆይቷል የሚል ትችት በመቅረብ ላይ መሆኑን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ማከሰኞ ዘገበ። በስልጣን ላይ ያለው ገዥው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያ ዳግም ወደ ድርቅና ረሃብ አደጋ ተመልሳለች መባልን እንደማይፈልግ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስነብቧል። ይሁንና፣ ድርቁ በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል እያደደረሰ ያለው ጉዳት ...

Read More »

ከፊ ሚነራል የተባለ ኩባንያ በኦሮሚያ አድርሷል በተባለ የአካባቢ ተፅዕኖ ካሳ እንዲከፍል ጥያቄ ቀረበበት

ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ወርቅ ለማውጣት በዝግጅት ላይ የሚገኘው የብሪታኒያ ከፊ ሚነራል ኩባንያ ከአመታት በፊት በክልሉ አድርሷል በተባለ የአካባቢ ተፅዕኖ የ12 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ጉዳት ጥያቄ ቀረበበት። ኩባንያው በምዕራብ ወለጋ አካባቢ ቱሉ ቆቢ በተባለ ስፍራ ወርቅ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ሲሆን፣ ይህንን ፕሮጄክት ከመረከቡ በፊት በአካባቢው በተመሳሳይ እንቅስቃሴ በቆየበት ከ1998 እስከ 2006 አም በስፍራው አካባቢያዊ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ...

Read More »

ባለፈው ሳምንት በጎንደር በፈነዳው ቦምብ አንድ የውጭ አገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009) የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ ደርሶ በነበረው የእጅ ቦምብ ፍንዳታ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን ሰኞ ይፋ አድርጓል። ይሁንና የብሪታኒያ መንግስት ጉዳት የደረሰበትን የውጭ ዜጋ ማንነት ከመግለጽ የተቆጠበ ሲሆን ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባሰራጨው የጉዞ ማሳሰቢያ አመልክቷል። ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ የእንግዶች ማረፊያ ሆቴል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ አስመልክቶ ኢሳት ...

Read More »

የአርጆ ዴዴሳ ስኳር ፋብሪካ በሸንኮራ እጥረት ተከትሎ ምርቱን አቋረጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009) የአርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ያጋጠመውን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት እጥረት ተከትሎ ምርቱን ሙሉ ለሙሉ አቋረጠ። ከ2007 አም ጀምሮ ስራውን በከፊል የጀመረው ፋብሪካው ችግሩን ለመቅረፍ በግንባታው ላይ ከሚገኝ ግድብ ውሃን በመጥለፍ የሸንኮራ አገዳ ለማምረት ቢሞከርም በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ጥረቱ ሳይሳካ መቅረቱን የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ካባ መርጋ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ለዚሁ ፋብሪካ አገልግሎት አንዲሰጥ የታሰበ ...

Read More »

ቅዳሜ በባህር ዳር ከተማ በፈንዳ ቦምብ አንድ ሲቪል ሲገደል ሶስት የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት መቁሰላቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009) ቅዳሜ ባህርዳር በፈነዳው ቦምብ አንድ ሲቪል ሲገደል አንድ ኢንስፔክተርን ጨምሮ ሶስት የልዩ ሃይል ፖሊሶች መቁሰላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ዳሸን ቢራ በአዲስ ስያሜ “ባላገሩ” በሚል ራሱን ለማስተዋወቅ በጠራው የሙዚቃ ኮንሰርት አካባቢ በፈነዳው ቦምብ የሙዚቃ ኮንሰርቱ መቋረጡም ታውቋል። ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ እስራቱ ይበልጥ በባጃጅ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ላይ ያተኮረ እንደሆነም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የባጃጅ ...

Read More »