ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጀመሪያው ዙር የታተመው 500 ሺህ ኮፒ በቂ ላይሆን ይችላል የሚል ሥጋት በማሳደሩና በበርካታ አፍሪካ ሀገሮች ካሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተጨማሪ ጥያቄ በመቅረቡ ሁለተኛ ዙር ሕትመት መቀጠሉን አስተባባሪዎቹ አስረድተዋል። አልበሙ ከወጣበት ማክሰኞ ከቀኑ 6 ፡00 ሰዓት ጀምሮ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው ሕዝብ ወደ ሲዲ መደብሮች በመትመሙ አከፋፋዮችና ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ለህዝብ ...
Read More »በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃገራችን ካለችበት አደገኛ የሆነ የጥፋት አዘቅት ውስጥ እንድትወጣም ሆነ ፤የስርዓት ለውጥም መምጣት የሚቻለው እያንዳንዱ ዜጋ በተደራጀ መልኩ ሲታገል ፤ድርጅቶችም ሳይጠላለፉ በመመካከር ስራዎችን በጋራ መስራት ሲችሉ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል። የትብብር መድረኩ በጀርመን አካባቢ የሚጠሩ ማናቸውም ሰላማዊ ሰልፎችና የተቃዋሚ እንቅስቃሴዎች በታቻለ መጠን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በጋራ እንዲዘጋጁ፣ በአካባቢው የሚካሄዱ ...
Read More »በሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሁለቱ ሃገራት ሰራዊቶች መስፈራቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል በድንበር ዙሪያ ቁጥጥርን ለማጠናከር የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ የሁለቱ ሃገራት ሰራዊቶች በአዋሳኝ ድንበር ዙሪያ መስፈራቸውን የሱዳን ባለስልጣናት ረቡዕ አስታወቁ። የሁለቱ ሃገራት ተወካዮች ባለፈው ወር በባህር ዳር ከተማ ባካሄዱት የድንበር ውይይት በአካባቢው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የአደንዛዥ ዕፅን ይቆጣጠራል የተባለ የጋራ ሰራዊት እንዲሰፍር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። የዚህኑ የመግባቢያ ሰነድ መፈረም ተከትሎ የኢትዮጵያና ...
Read More »ከ300 ሺ በላይ ህጻናት አስከፊ የምግብ እጥረት ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ዩኒሴፍ ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በአራት ክልሎች እየተባባሰ ባለው የድርቅ አደጋ ዕድሚያቸው ከአምስት አመት በታች የሆነ ከ300 ሺ በላይ ህጻናት በአስከፊ የምግብ እጥረት ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግስት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ገለጸ። የአለም ባንክ በበኩሉ ተደጋጋሚ የድርቅ አደጋ እያጋጠማት ያለው ኢትዮጵያ አደጋውን በዘላቂነት መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ማተኮር እንዳለበት አሳስስቧል። አዲስ ተከስቶ ባለው በዚሁ የድርቅ አደጋ በኦሮሚያ፣ አፋር፣ ...
Read More »የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብዱላሂ ከኢትዮጵያ ጋር ተፈጥሯል በተባለው አለመተማመን ዙሪያ ለመምከር አዲስ አበባ ገቡ
ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009) የሶማሊያው አዲስ ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብዱላሂ ከኢትዮጵያ ጋር ተፈጥሯል በተባለው አለመተማመን ዙሪያ ለመምከር ረቡዕ በአዲስ አበባ ጉብኝት ማድረግ መጀመራቸውን ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል የሃገሪቱ ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ ረቡዕ ዘገበ። ፕሬዚደንት አብዱላሂ ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው በፊት በአምስት ሃገራት ጉዞ ያደረጉ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ አስፈላጊም እጅግ አስቸጋሪም ነው ሲሉ የአፍሪካ ቀንድ የታሪክ ምሁር የሆኑት ጀራልድ ፕሩኒየር ለራዲዮ ጣቢያው ...
Read More »የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአለም ሃገራት ለመገናና ብዙሃን ነጻነት መከበር ቁርጠኝነታቸው እንዲያሳዩ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተለያዩ አለም አቀፍ አካላት የአለም ሃገራት ለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት መከበር ቁርተኝነታቸውን በተግባር እንዲያሳዩ አሳሰቡ። በየአመቱ ሚያዚያ 25 ፥ የሚከበረውን የአለም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀንን አስመልክቶ መልዕክትን ያስተላለፉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ የአለም ሃገራት መረጃዎችና ዜጎች በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ማዋከብና ማስፈራራት በአስቸኳይ ማቆም ...
Read More »በባህርዳር የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች ታሰሩ
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደረሰበትን ህዝባዊ ማዕቀብ መቋቋም የተነሳነው በህወሃት/ብአዴን የሚተዳደረው ዳሸን ቢራ ስሙን ባላገሩ ቢራ በሚል ቀይሮ ባህርዳር ላይ ያዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት፣ ፍንዳታ መካሄዱን ተከትሎ ፖሊሶች በድንጋጤ በመተኮሳቸው የ2 ሰዎች ካለፈ በሁዋላ፣ ከፍተኛ ብስጭትና ሽንፈት የደረሰበት ገዢው ፓርቲ፣ “ይህን ያክል ጥበቃ ተመድቦ ፣ ይህን ያክል ወታደር ጥበቃ እያደረገ እንዴት ቦንብ ሊገባ ...
Read More »ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮች ወደ አገር ገቡ
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ 24 ቀን 2009 ዓም ጠዋት በርካታ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ሾፌሮች ገልጸዋል። በጅቡቲ ወደብ 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮች የተራገፉ መሆኑን የሚገልጹት የአይን እማኞች፣ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑትን ታንኮች የጫኑ ሎቤድ መኪኖች ወደ ደብረዘይት ተንቀሳቅሰዋል። ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መራባቸው በተነገረ በሳምንት በእርዳታ ...
Read More »የእንግሊዝ መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ለደህንነት ሲባል መጎብኘት የሌለባቸውን ቦታዎች ይፋ አደረገ
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእንግሊዝ መንግስት የውጭ ጉዳይ እና የጋራ ብልጽግና ጽ/ቤት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ በሚያደርጓቸውን ማንኛውንም ጉዞዎች ለደህነታቸው አስጊ እና አደጋ ሊደርስባቸው ይችላል ያላቸውን አካባቢዎች ለይቶ አሳውቋል። የቱሪስት መስህብ ከሆኑት ደብረዳሞ እና የሃ በስተቀር ከኢትዮ-ኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር አካባቢ በሚገኙት ከአክሱም እስከ አዲግራት ባሉ ዋና መንገዶች ዜጎቹ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል። በሱዳን ...
Read More »በከተሞች ዙሪያ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ተተኪ ቦታ ባለማግኘታቸው እየተንገላቱ መሆኑን ተናገሩ፡፡
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመርአዊ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች እንደገለጹት ፣ በተለያዩ ሰበቦች የእርሻ መሬታቸውን ከተነጠቁ በኋላ፣ ተተኪ የመኖሪያ ቦታ ባለማግኘታቸው ቤተሰቦቻቸው በቤት ኪራይ እየተሰቃዩ ነው። ወይዘሮ ፈንታነሽ አድማሴ በመርዓዊ ዙሪያ በሚገኝ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ከከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚኖሩበት አካባቢና የእርሻ ቦታቸው በመካለሉ አሮጌ ቤታቸውን አድሰው ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ለመኖር ተከልክለዋል፡፡የከተማ ...
Read More »