ሚያዝያ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር እና ጎንደር ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች እንደገለጹት የዝነኛው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ “ኢትዮጵያ” የሚለው አዲሱ የሙዚቃ ስራው በመኪኖች ላይ እየተዞረ እንዳይሸጥ ተከልክሏል። ነጋዴዎቹ “በአዲስ አበባ እንጅ በዚህ አካባቢ እንድትሸጡ ፈቃድ አልተሰጣችሁም” ከተባሉ በሁዋላ የማከፋፈል ፈቃድ ሲጠይቁ ከአንዱ መስሪያ ቤት ወደ ሌላው በማመላለስ ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል። የቅስቀሳ ስራ ለመስራት በቀን ...
Read More »በጂንካ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተመሰረተው ክስ ውድቅ ተደረገ
ሚያዝያ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዞኑ ደህንነት ሃላፊ አቶ አልአዛር ቶይሳ ፍላጎት ከ4 ወር በላይ የታሰሩት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ ኦህዲኅ/ ም/ል ሊቀመንበር መምህር ዓለማዬሁ መኮንን በ3000 /ሦስት ሺህ) ብር ዋስ 07/07/2009 ዓ.ም. ከተፈቱ በሁዋላ፣ ያቀረቡት ክስ መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ ከወንጀሉ ነጻ ተብለዋል ፡፡ ‹‹ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ‹‹ የጥቁር መልበስ ድንበር ተሻግሮ ...
Read More »የአቶ አሰፋ ጨቦ የቀብር ስነ ስርአት በአዲስ አበባ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ።
ሚያዝያ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለረጅም አመታት በስደት የኖሩት አቶ አሰፋ ጨቦ በቅርቡ ባሳተሙት የትዝታ ፈለግ መፅሀፋቸው ህልም ባየሁ ቁጥር የሚታየኝ ጋሞ እና ኢትዮጵያ ናቸው ቢሉም ባደረባቸው ህመም ሳቢያ የናፈቋትን አገራቸውን ሳያዩ ከሳምንት በፊት በአሜሪካ ህይወታቸው አልፏል። የአቶ አሰፋ የቀብር ስነ ስርአት በርካታ ህዝብና ወዳጆቻቸው በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል። ታዋቂው ፖለቲከኛ፣ ጸሃፊና የህግ ...
Read More »በአወዛጋቢ ሁኔታ የተገደለው የኢትዮጵያ የቡና ደጋፊ ዘነበ በላይ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
ሚያዝያ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከወር በፊት ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉትን የእግር ኳስ ጫወታ ለመከታተል ወደ አዋሳ ያቀናው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ዘነበ በላይ ከጫወታው በኋላ አድራሻው ጠፍቷል። የዘነበ በላይን አድራሻ ለማግኘት የቡና ደጋፊዎች እና ቤተሰቦቹ የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደረጉም ጥረታቸው ሳይሰምር ቀርቷል። እስካሁንም አሟሟቱን አስመልክቶ ግልጽ የሆነ የሚታወቅ ነገር ማግኘት አልተቻለም። ግድያው በማን ...
Read More »ሰሜን ኮሪያ የአገሪቱን መሪ ኪም ጆን ኡንን በባዮ-ኬሚካል ንጥረ ነገር በመመረዝ ለመግደል የታቀደው ሴራ መክሸፉ ገለጸች
ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009) የግድያ ሴራውን አስመልክቶ የሰሜን ኮሪያ የመንግስት ዜና አገልግሎት ድርጅት እንደገለጸው፣ በሰሜን ኮሪያ በህቡዕ የሚሰራ አሸባሪ ሃይል ከአሜሪካው የስለላ ድርጅት (CIA)ና ከደቡብ ኮሪያ የጸጥታ አገልግሎት (IS) ጋር በመተባበር ጥቃቱን ለመፈጸም አቅደው እንደነበር ገልጿል። የሰሜን ኮሪያ የዜና አገልግሎቱ በታላቁ መሪ ማለትም ኪም ጆን ኡንን ላይ ታቅዶ ስለነበረው የመግደል ሙከራ የሰጠው ምንም አይነት ተጨባጭ መረጃ ባይኖርም፣ ሴራው በቅርብ ...
Read More »የአቶ አሰፋ ጫቦ የቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2009) የታዋቂው የህግ ባልሙያ፣ ፖለቲከኛና ጸሃፊ አቶ አሰፋ ጫቦ የቀብር ስነስርዓት ሚያዚያ 2009 አም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ። ለ25 አመታት በአሜሪካ ስደት ላይ የነበሩት አቶ አሰፋ ጫቦ በሚኖሩበት ዳለስ ቴክሳስ ግዛት በ75 አመታቸው በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። አቶ አሰፋ ጫቦ የኢትዮጵያ ጭቁን አብዮታዊ ትብብር (ኢጭአት) ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር በመሆን በደርግ ጊዜ የታወቁ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአሜሪካ ያለክፍያ የመውለድ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የአሜሪካ ኤምባሲ ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ለጉብኝት በሚል ወደ አሜሪካ በመሄድ ያለምንም ክፍያ የመውለድ አገልግሎት ማግኘታቸው ስጋት እንዳሳደረበት ገለጸ። ኤምባሲው ለአየር መንገዱ ባቀረበው አቤቱቷ ወደ አሜሪካ በተለያዩ ጊዜያት ተጉዘው ማንኛውንም ህክምና ያደረጉ ሰራተኞችን በተመለከተ ሪፖርት እንዲያደርጉለት ጥያቄ ማቅረቡን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ኤምባሲው ለእረፍት በሚል ወደ ሃገሪቱ ሄደው የመውለድ እና የተለያዩ አገልግሎት ያገኙ ...
Read More »የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከሶስት ወር ያነሰ የገቢ ሸቀጦችን ወጪ ብቻ ለመሸፈን የሚያስችል መሆኑ ተመለከተ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2009) የብሄራዊ ባንክ የሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከሶስት ወር ያነሰ የገቢ ሸቀጦችን ወጪ ብቻ ለመሸፈን የሚያስችል መሆኑን የባንኩ አረጋገጠ። በአስመጪ ንግድ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ ነጋዴዎች ሃገሪቱ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ የውጭ ምንዛሪን ለማግኘት በአማካኝ እስከ ስድስት ወር ወረፋን እንደሚጠብቁ ሲገልፁ ቆይተዋል። በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ለፓርላማ የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርትን ረቡዕ ያቀረቡት የባንኩ ዋና ...
Read More »በባህርዳር ከፍንዳታ ጋር በተየያዘ በጥርጣሬ በተያዙ ሰዎች ላይ የቴሌቪዥን ቀረጻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009) ባለፈው ቅዳሜ በባህርዳር ከተከሰተው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ በጥርጣሬ በተያዙ ሰዎች ላይ የቴሌቪዥን ቀረጻ በመካሄድ ላይ መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገልጹ። የገዢው ፓርቲ ምርት የሆነውን ባላገሩ ቢራ ለማስተዋወቅ በተጠራ የሙዚቃ ኮንሰርት አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ ፕሮግራሙ መቋረጡ ይታወሳል። በጥርጣሪ በተያዙት ግለሰቦች ላይ ማክሰኞ የተጀመረው ቀረጻ በአማራ ክልል ቴሌቪዥን አማካኝነት እየተፈጸመ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ይህንን ሂደት በበላይነት የሚመሩት የማነ ...
Read More »አሜሪካ ለአለም አቀፍ ድጋፍ በምትሰጠው የገንዘብ ድጎማ ላይ ያስተላለፈችው የበጀት ቅነሳ፣ ኢትዮጵያ ዋነኛ ተጎጂ ማድረጉ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009) አሜሪካ በቅርቡ ለአለም አቀፍ ድጋፍ በምትሰጠው የገንዘብ ድጎማ ላይ ያስተላለፈችው የበጀት ቅነሳ፣ ኢትዮጵያ ዋነኛ ተጎጂ ማድረጉ ተገለጸ። ለኢትዮጵያና ኡጋንዳ የሚሰጠው ድጋፍ እንደሚቀንስም ተመልክቷል። ሃገሪቱ በተያዘው ሳምንት ባቀረበችው የ2017/2018 በጀት እቅድ በአለም አቀፍ የእርዳታ ላይ የ31 በመቶ አካባቢ ቅናሽ ማድረጓን ዘኢስት አፍሪካን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። በዚሁ የአሜሪካ ዕርምጃ ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ከአፍሪካ ዋነኛ ተጎጂ መሆናቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ ...
Read More »