ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) የሱዳን መንግስት በቀይ ባህር ላይ በሚገኘው የሃይላብ ግዛት ላይ ያነሳውን የይገባኛል ጥያቄ ተከትሎ ግብፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቃውሞ አቀረበች። ግብፅና ሱዳን በአዲስ መልኩ የገቡበት ይኸው የድንበር ይዞታ ውዝግቡ በአባይ ግድብ ላይ በመካሄድ ላይ ባለው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን ያሳድራል ተብሎ ተሰግቷል። የሱዳን መንግስት በግዛቱ ላይ ያነሳውን የይገባኛ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ይፈታል ያለውን አዲስ ሃሳብ ...
Read More »ኢሳት የ7ኛ አመት ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በሲልቨርስፕሪንግ የተሳካ ገቢ ማሰባሰቢያ አካሄዱን አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን (ኢሳት) የ7ኛ አመት ምስረታን በማድረግ በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ የተካሄደው የገቢ ማሳሰቢያ የተሳካ እንደነበር አስተባባሪዎች ገለጹ። የዋሽንግተን ዲሲ የኢሳት ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ያዘጋጀው የ7ኛ አመት የምስረታ በዓል በድምቀት መከበሩን ለማወቅ ተችሏል። በስነ-ስርዓቱ ታዋቂዎቹ ድምጻውያን ሻምበል በላይነህ እና ደሳለኝ መልኩ ኮሜዲያን ወንደወሰን ( ዶክሌ) ታዳሚዎችን ሲያዝናኑት አምሽተዋል። የኢሳት 7ኛ አመት የምስረታና የገቢ ማሰባሰቢ ...
Read More »ብሪታኒያዊው ዴቪድ ናባሮ የአለም ጤና ድርጅት ሆነው የመመረጥ እድላቸው አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) በተያዘው ወር የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊን ለመምራት በሚደረገው የአባል ሃገራት ምርጫ ብሪታኒያዊው ተወዳዳሪ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ መሰረት የመመረጥ እድላቸው አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ። ብሪታኒያ በአባልነት ያለችበት የጸጥታው ምክር ቤት ደንብ መሰረት ሃገሪቱ ለአለም ጤና ድርጅት ሃላፊን ከመወከል እንደሚከለክላት ብሪኪንግ ታይም የተሰኘ የጤና መጽሄት ሰኞ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረበው ዘገባ አመልክቷል። ይኸው አለም አቀፍ ድንጋጌ ከሶስቱ የመጨረሻ ...
Read More »ከፊ ሚነራል ከቱሉ ቆቢ ፕሮጄክት የሚወጣውን የወርቅ ሃብት የሚያስተዳደር አካል ከመንግስት ጋር መቋቋሙን አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል የወርቅ ማውጣት ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ከፊ ሚነራል ኩባንያ በቱሉ ቆቢ ፕሮጄክት የሚወጣውን የወርቅ ሃብት የሚያስተዳደር አካል ከመንግስት ጋር ማቋቁሙን ሰኞ አስታወቀ። በአካባቢው የሚወጣውን ከፍተኛ የወርቅ ሃብት ለማስተዳደር በሁለቱ ወገኖች በተደረሰ አዲስ ስምምነት መንግስት 25 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው የተደረገ ሲሆን፣ ቀሪው 75 በመቶ ደግሞ የከፊ ሚነራል እንዲሆን ተወስኗል። መንግስት 25 በመቶ ድርሻን ...
Read More »በአፋርና አማራ ድንበሮች በተነሳ ግጭት ከ 15 በላይ ሰዎች ቆሰሉ
ሚያዝያ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በአዳር ወረዳ ከባቲ 15 ኪ ሜ ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ ላይ ከድንበር ይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት ከ15 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ግጭቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት በአካባቢው የነበሩ የአጋዚ ወታደሮች ሁኔታውን ለማብረድ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማሳየታቸው ነዋሪዎችን ግራ አጋብቶአል ። እንደ ወረዳው ነዋሪዎች ገለጻ በአካባቢው ከዛሬ ...
Read More »በስዊዘርላንድ የህወኃት አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው የጠሩት ስብሰባ ተቃውሞ ገጠመው
ሚያዝያ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አምባሳደሩ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለመወያዬት በሚል ነበር በመኖሪያ ቤታቸው የህወኃት- ኢህአዴግ አባላት የሆኑ ሰዎችን በምስጢር ስብሰባ የጠሩት። ስለ ጥሪው የሰሙ በስዊዘርላንድ የሚገኙ ሀገር ውዳድ ኢትዮጵያውያን “የሀገራችን ጉዳይ እኛንም ያገባናል” በማለት በቀጥታ ስብሰባው ወደተጠራበት ወደ አምባሳደሩ ቤት ሰተት ብለው ይገባሉ። ሁኔታው ስጋትና ጭንቀት ያሳደረባቸው የስብሰባው አስተባባሪዎች ልክ እንደ ጸጉረ ...
Read More »የደህንነቱ መ/ቤት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ማሴሩ ተሰማ
ሚያዝያ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ወራት ውስጥ በጎንደርና በባህር ዳር ከአገዛዙ ጋር ቅርበት ባላቸው አካላት ላይ ያነጣጠሩ ተከታታይ ፍንዳታዎች ሲደርሱ ቆይተዋል። በጎንደር ከተማ በጥቂት ወራት ውስጥ ከአስር በላይ ፍንዳታዎች የተፈፀሙ ሲሆን፤ በእንግዶች ማረፊያ ሆቴል ላይ በደረሰ ፍንዳታ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች እንደተጎዱ በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል። እንዲሁ በባህር ዳርም ጃሽን ቢራ ...
Read More »የዶክተር አዲስ ዓለማዬሁን ሐውልት የመረቁት ሚኒስትር በቦታው የነበሩትን ታዳሚዎችን አሳዘኑ።
ሚያዝያ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፍቅር እስከመቃብርን ጨምሮ በርካታ ረዣዥምና ዘመን ተሻጋሪ ልቦለድ መጽሐፍትን ላበረከቱት ለታዋቂው ኢትዮጵያዊ ደራሲ ለክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማዬሁ በደብረማርቆስ ከተማ የተገነባውን ሐውልት የመረቁት የባህል ሚኒስትሯ ወረቀታቸው ጠፍቷቸው ንግግራቸውን ማቋረጣቸው ተሰማ። ቅዳሜ ዕለት ሚያዚያ 28 ቀን 2009 ዓመተምህረት በተደረገው የመታሰቢያ ሐውልት ምርቃት ሥነ ስር ዓት ላይ የክብር እንግዳና ተናጋሪ የነበሩት ሚኒስትሯ ...
Read More »76ኛው የድል በአል ተከብሮ ዋለ
ሚያዝያ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ይዘው ለመግዛት ባህር አቋርጠው የመጡትን የፋሽሽት ጣሊያን ወታደሮች፣ በአምስት አመት የአርበኝነት ተጋድሎ በማንበርከክ የኢትዮጵያን ነጻነት መልሰው እጃቸው ውስጥ ያስገቡበት፣ 76ኛው የድል በዓል በመላው ኢትዮጵያ ተከብሯል። አትዮጵያውያን አርበኞች በጎብዝ አለቆች እንዲሁም በጊዜው በነበሩ መሳፍንት እየተመሩ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተደራጅቶ የመጣውንና መላ ኢትዮጵያን ወሮ ለመያዝ አልሞ የመጣውን ...
Read More »በደንቢያ የተጠራው ስብሰባ ተቃውሞ ገጠመው
ሚያዝያ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ ተቃውሞዎችን ስታስተናገድ በከረመችው ደንቢያ፣ የተጠራው ስብሰባ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ እንደቀረበበትና ስብሰባው ተቋርጦ እንደነበር ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የወረዳው አስተዳደር ዘይት እናከፋፍላለን በማለት ህዝቡ በስብሰባው ላይ እንዲገኝ ያደረገ ቢሆንም፣ የዘይት ችግር የሚለው አጀንዳ ተለውጦ ስለሰላም እና ስለጸጥታ ንግግር በሚደረግበት ወቅት፣ ህዝቡ “ ዘይት ብላችሁ ነው የጠራችሁን፣ አሁን የምታወሩን ...
Read More »