ግንቦት ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረሪ ክልል በገጠር አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሞ አገር ሽማግሌዎች ለኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት በጻፉት የአቤቱታ ድብዳቤ በሃረሪ ክልል ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም፣ ከፖለቲካና ከኢኮኖሚ ጉዳዮች ውጭ በመሆናችን አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ወደ ኦሮምያ ክልል እንድንጠቃለል እንጠይቃለን ብለዋል። ከ99 በመቶ በላይ የሚሆኑ በክልሉ የሚገኙ የንግድ ቤቶች እና ቦታዎች የተያዙት ...
Read More »ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በፌስቡክ ጽሁፎቹ በሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ
ግንቦት ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዞ ከዓመት በላይ በእስር ሲሰቃይ የቆየው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ዮናታን ተስፋዬ በቀረበበት የሽብር ክስ ጥፋተኛ ተብሎአል። በፌስ ቡክ እና ትዊተር ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገጾች ላይ በሚጽፋቸው ጽሁፎች ምክንያት ለእስር የተዳረገው ዮናታን ተስፋዬ የፀረ ሽብር አዋጁን 652/2001 አንቀፅ 6ን ተላልፈሃል በሚል የጥፋተኝነት ፍርድ ...
Read More »በአማራ ክልል ዕምነት አልተጣለባቸውም የተባሉ የፖሊስ አመራሮች ከሃላፊነትና ከደረጃቸው ዝቅ ተደረጉ
ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) በአማራ ክልል ከተካሄደው የጸጥታና ደህንነት ግምገማ ጋር በተያያዘ በህወሃት ዕምነት አልተጣለባቸውም የተባሉ የፖሊስ አመራሮች ከሃላፊነትና ከደረጃቸው ዝቅ ተደረጉ። ከክልሉ የፖሊስ አመራሮች ከስራ የተሰናበቱም ይገኙበታል። በባህርዳርና በጎንደር ከተፈጸሙት የቦምብ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ የአካባቢው ጸጥታ አልተቆጣጠራችሁም የተባሉት የክልሉ ፖሊስ አባላት ስም ዝርዝር ኢሳት ደርሶታል። የአማራ ክልል አመራር አባላት ከስራ ደራጃቸው ዝቅ የተደረጉትና የተባረሩት የትምክህት አስተሳሰብ ሰለባ ናችሁ ...
Read More »ዶ/ር ቴዎድሮስ የኮሌራ በሽታ እንዳይታወቅ ደብቀዋል ተብለው በአለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ክስ ቀረበባቸው
ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) ኢትዮጵያን በመወከል ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩ ጊዜ በሃገራቸው የተከሰቱ ሶስት የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታዎች ለህዝብ እንዳይታወቅ አድርገዋል የሚል ቅሬታ በአለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ቀረበባቸው። የጤና ድርጅቱ አባል ሃገራት የመጨረሻ እጩ ሆነው ከቀረቡ ሶስት ተፎካካሪዎች መካከል አንዱን ለመምረጥ የሳምንት ዕድሜ በቀራቸው ጊዜ ዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የቀረበው ...
Read More »የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባላት ላይ ሊሰጥ የነበረው ብይን ለሁለተኛ ጊዜ ተራዘመ
ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሌሎች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባላት ላይ ሲሰጥ የነበረን የመጀመሪያ ዙር ብይን ለሁለተኛ ጊዜ አራዘመ። ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ይከላከሉ ወይም በነጻ ይሰናበቱ የሚል ብይን ሰኞ ያስተላልፋል ተብሎ ቢጠበቅም ለግንቦት መጨረሻ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ዘግቧል። አቃቤ ህግ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ አቀርበዋለሁ ያለው ...
Read More »የግብፅ መንግስት የአባይ ወንዝን አጠቃቀም በተመለከተ በዩጋንዳ ምክክር እንዲካሄድ ጥያቄ አቀረበ
ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) የግብፅ መንግስት በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከሰባት አመት በፊት አቅርቦ የነበረው ሃሳብ በዩጋንዳ ዳግም ምክክር እንዲካሄደበት ጥያቄን አቀረበ። ግብፅ ያቀረበችውን ይህንኑ ጥያቄ ተከትሎ የዩጋንዳው ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በናይል ምክር ቤት አባላት ዘንድ በፕሬዚደንቶች ደረጃ በቀጣዩ ሳምንት ምክክር እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል። ይሁንና ኢትዮጵያ በግብፅ የቀረበውን ሃሳብ በአግባቡ ለመመልከት ጊዜ ያስፈልገኛል በማለት የውይይቱ ቀን እንዲፈጸም ጥያቄ ...
Read More »180ሺ የእጅ ኮምፒውተሮች (ታብሌቶች) እንዲገቡ የተካሄደው የግዢ ጨረታ ውዝግብ ማስነሳቱ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) መንግስት ለቀጣዩ አመት በሃገሪቱ ለሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ 180ሺ የእጅ ኮምፒውተሮች (ታብሌቶች) እንዲገቡ ያካሄደው የግዢ ጨረታ ውዝግብ ማስነሳቱ ተገለጸ። የመንግስት ግዢዎችና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሌኖቮ የተሰኘውን የቻይና ኩባንያ በተለያዩ መንገዶች በመገምገም ለጨረታው ተሳታፊ እንዳይሆን ቢወሰንም የኤጀንሲው የቅሬታ ሰሚ ቦርድ ግን ውሳኒው እንዲቀለበስ ማድረጉ ይታወሳል። አንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረግበታል የተባለው የኮምፒውተሮች ግዢ ከሌሎች አምስት ኩባንያዎች ...
Read More »በባህርዳር የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ የፖሊስ አመራሮች ከሃላፊነት ተነሱ
ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ የደረሰውን ተደጋጋሚ የቦንብ ጥቃት መንስኤና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለመያዝ ባለመቻላቸው የተገመገሙት የባህርዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ውበቱ አለን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ፖሊሶች ከደረጃ ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል። በተባረሩ አዛዦች ቦታ የሚተኩት አዲሶቹ አዛዦች፣ ነባሩ አመራር ሊደርስበት ያልቻለውን ህዋስ አጥንተው እንዲደርሱበት ልዩ ትእዛዝ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ...
Read More »ከ40 በላይ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ጎንደር አቅጣጫ ማምራታቸው ታወቀ
ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚደረገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ ሲሆን፣ ዛሬም ከ40 በላይ ወታደሮችን የጫኑ ኦራል ተሽከርካሪዎች በወልድያ አድርገው ወደ ጎንደር አቅጣጫ አምርተዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተሽከርከሪዎች ወታደሮችን ወደ ሰሜን ሲያጓጉዙ ሰንብተዋል። በቅርቡ በርካታ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮች ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ የገቡ ...
Read More »በአዲስ አበባ ቆሻሻ መድፊያ ቦታ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ የተሰበሰበው ገንዘብ እስካሁን አለመከፋፈሉ በተፈናቃዮች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል።
ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው የቆሻሻ መድፊያ ላይ በደረሰው ናዳ በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና መፈናቀላቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያን የእርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለተጎጂዎች ቢሰጡም፣ የባንክ ሂሳቡን የሚቆጣጠረው ገዢው ፓርቲ ገንዘቡን ለተጎጂዎች ባለማከፋፈሉ ማዘናቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናግረዋል። በቅርቡ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ለተጎጂዎች የሚሰጣቸውን የኮንዶሚኒየም ቤት እና ቦታ ቢያስታወቁም፣ እስካሁን ድረስ ቃል ...
Read More »