በሜቴክ የሚሰራው የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ከመንግስት ከ4. 4 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ክፍያ ጠየቀ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ5 ዓመታት በፊት ተጀምሮ በ2008 ዓም ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረውና በአሁኑ ሰዓት ከ35 በመቶ ያልበለጠ ግንባታ ያካሄደው እንዲሁም ከተፈጥሮ ውድመት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቅርብበት የቆየው ያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በመጀመሪያ የተያዘለት የ9 ቢሊዮን 600 ሺ ብር በጀት እንደማይበቃው ግንባታውን በሚያካሂደው በመከላከያ ኢንጂነሪንግ በኩል ጥያቄ አቅርቧል። ኩባንያው ተጨማሪ 4 ቢሊዮን ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 ተጨማሪ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ እንደገለጸው ግንቦት 7 ከሌሊቱ 8 ሰአት ከ55 ደቂቃ ላይ ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን በሊቦከምከም ወረዳ በጣራ ገዳም አካባቢ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ጦሩ በተጠቀሰው ቦታ ላይ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ስቃይ ሲፈጽም እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል። የንቅናቄው ታጋዮች ወደ ...

Read More »

ዮናታን ተስፋዬ በፌስቡክ ላይ በመጻፉ በአሸባሪነት መከሰሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮናታን ተስፋዬ መንግስትን በመተቸቱ ብቻ በሽብር ክስ መከሰሱን አውግዟል። ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከቅም በላይ ሃይል መጠቀማቸውን በማህበራዊ ድረገጾች ማውገዙ ሊያስከስሰው አይገባም ብሏል። ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በአንድ ወቅት ...

Read More »

አልሸባብ ሂራን በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ላይ ጥቃት አደረሰ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር አሜሶም ስር በሶማሊያ በተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ላይ አሸባሪው አልሸባብ ጥቃት ፈጸመ። ረቡእ እለት በሂራን ግዛት በሃላጋን ከተማ በሁለቱም መሃከል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። እስካሁን በግጭቱ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ማወቅ አልተቻለም። አልሸባብ በራሱ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ወታደራዊ ቤዝ ...

Read More »

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለአለም ጤና ድርጅት ተመራጭ እንዳይሆኑ ተቃውሞ አቀረቡ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን በአለም ጤና ድርጅት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የድርጅቱ ተመራጭ እንዳይሆኑ ተቃውሞ አቀረቡ። ማክሰኞ ረፋድ ላይ በድርጅቱ ጽ/ቤት የተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ቴዎድሮስ ከገዢው ከኢህአዴግ መንግስት ጋር በሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ያላቸው የቆየ ትስስር ድርጅቱን ለመምራት እንደማያበቃቸው ሲቃወሙ ታይተዋል። በትናንትናው ዕለት ታዋቂ የጤና ባለሙያዎች ዶ/ር ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አገራት ከሚገኙ ደንበኞች ያልተከፈለው የአገልግሎት ክፍያ ለፋይናንስ እጥረት መዳረጉን ገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ከደንበኞቹ ያልተከፈለው የአገልግሎት ክፍያ ለፋይናንስ እጥረት እንደዳረገው ይፋ አደረገ። አየር መንገዱ ለተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መንግስታትና ተቋማት አገልግሎት የሰጠባቸው ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለረጅም ጊዜ ሳይከፈለው መቅረቱን ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል። ይኸው ለረጅም ጊዜ ሳይከፈል የቆየው ክፍያ በድርጅቱ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖን ማሳደሩን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ...

Read More »

የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቶ ዮናታን ተስፋዬ በተመሰረተበት የሽብርተኛ ክስ የጥፋተኝነት ብይን ሰጠ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ዮናታን ተስፋዬ ላይ በተመሰረተበት የሽብርተኛ ክስ የጥፋተኝነት ብይን ማክስኞ ሰጠ። በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ ጽሁፎችን ሲያቀርብ የነበረው ዮናታን በኦሮሚያ ክልል ከተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ከአመት በፊት ለእስር መዳረጉ ይታወሳል። በግንቦት ወር 2008 አም ክሱን የመሰረተው ከሳሽ አቃቤ ህግ ተከሳሹ በማህበራዊ ድረገጾች አመፅ እንዲስፋፋ ...

Read More »

በመቀሌና በባህርዳር ከነማ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ግጭት የባህርዳር ከነማ ጥፋተኛ ሆኖ እንዲቀጣ ውሳኔ ተላለፈ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2009) በመቀሌ ከነማና በባህርዳር አቻው የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ውዝግብና ግጭት የባህርዳር ከነማ ጥፋተኛ ሆኖ እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል የተላለፈው ውሳኔ የፊታችን አርብ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።  ዕርምጃው ፖለቲካው ይዘት ያለው ነው የሚለውን ለመከላከል ከዳኞቹና ከውድድር ኮሚቴ በተገኘ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ውሳኔው መተላለፉን የሚገልጽ ደብዳቤ መዘጋጀም ትመአልክቷል። የእግር ...

Read More »

ደህዴን በትግራይ ክልል በ12 ሚሊዮን ብር ያስገነባው ትምህርት ቤት መመረቁ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2009) የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደህዴን) በትግራይ ክልል በ 12 ሚሊዮን ብር ያስገነባው ህንጻ መመረቁ ተዘገበ።  መንግስታዊው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኤዜአ) እንደዘገበው በአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሚመራው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በትግራይ ክልል አዲገባሮ በተባለ ገጠር ቀበሌ የሰራው 12 ሚሊዮን ብር የወጣበት ትምህርት ቤት ሰኞ ዕለት ተመርቋል። የደቡብ ክልል ለትግራይ ክልል ትምህርት ቤት ለመገንባት 12 ...

Read More »

መከላከያን ጥለው የሚጠፉ ወታደሮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል

ግንቦት ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ በአማራና በኦሮምያ አካባቢዎች የተነሱትን ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተከትሎ፣ ስርዓቱን በተለያየ መንገድ አናገለግልም በማለት እየጠፉ የሚሄዱ ወታደሮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ አዳዲስ ወታደሮችን በፍጥነት ለመመልመልና በተለያዩ መንገድ ከመከላከያ የተሰናበቱትን ተመልሰው እንዲገቡ ጥሪ ለማድረግ ተገዷል። ባለፉት 4 ወራት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች መጥፋታቸው ለመከላከያ ከፍተኛ ...

Read More »