ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ የአሁኑ ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ሰመጉ) ባወጣው 142ኛ ልዩ መግለጫ፣የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ከመስከረም28 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ከህግ አግባብ ውጭ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ ተደብድበዋል፣ በመደበኛ እስር ቤቶችና ከመደበና እስር ቤቶች ውጭ በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል፣ የደረሱበትም የማይታወቁ በርካታ ናቸው ብሎአል። ሰመጉ ከህግ ...
Read More »የደህንነት ሃይሎች የባህርዳርን ጸጥታ መቆጣጠር ተስኖዋቸዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ የሚገልጹት ነዋሪዎች፣የጥቃቱን ፈጻሚዎች ማንነት ለማወቅ አለመቻሉ ግራ አጋብቷቸዋል፡፡ የክልሉን ደህንነት እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመራው የህውሃት ደህንነት ክፍል ጥቃቶችና አፈናዎችን መመከት አለመቻሉን የከተማዋ ነዋሪኦች ለክልሉ ወኪላችን ገልጸውላታል። ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ የተካሄዱትን ግድያዎችና አፈናዎች መመከት ያልቻለው የደህንነት ኃይሉ፣ ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸሙትን ግለሰቦች መያዝ ...
Read More »የጎርፍ አደጋ በረሃብ የተጎዳውን ህዝብ ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ተመድ አስታወቀ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ ከ3 ሳምንት በፊት በኦሮምያ በምዕራብ ሃረርጌ በሃዊ ጉዲና ወረዳ እና በአርሲ ዞን ሰሩ እና ጮሌ ወረዳዎች የጣለው ዝናብ በርካታ ዜጎችን አፈናቅሏል። በምዕራብ ሃረርጌ ዞን በሃዊ ጉዲና ወረዳ 8 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሲሞቱ 5ቱ ደግሞ ቆስለዋል። 3 ሺ 179 የቀንድ ከብቶች አልቀዋል። በአርሲ ...
Read More »ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም አያናው ከስራ ታገደ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ማስ ሚዲያ ውስጥ ጋዜጠኛ የሆነውና በድፍረት በሚሰነዝራቸው ትችቶች የሚታወቀው ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም አያናው ከስራ መታገዱንና የመንግስትን ስም በማጥፋት ሊከሰስ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም ከስራ መታገደኑን ወደ መስሪያ ቤት ሲገባ መከልከሉን ኢሳት ለማረጋገጥ ችሎአል። ፍቅርማርያም ጥልቅ ተሃድሶ በሚል በአማራ ክልል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለጋዜጠኞች በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ፣ የህወሃትን ...
Read More »በኮሪያ በኢትዮጵያ ኢምባሲ የተጠራዉ የግንቦት 20 በአል ዝግጅት ተቃውሞ ገጠመው
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ3 ቀናት በፊት በአምባሳደር ሽፈራዉ ጃርሶ የሚመራው ኢምባሲ ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት ደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ዉስጥ በሚገኘው ባለ 5 ኮከብ ሎቴ ሆቴል ያዘጋጀው ዝግጅት በአገሪቱ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንዳጋጠው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ኢምባሲው የሚስጥር ጥሪ ወረቀት መላኩንና እንግዳ ሆነው የተገኙት የህወሃት አባላት ብቻ መሆናቸውን የሚገለጹት ኢትዮጵያውያን፣ በግብዣው ...
Read More »ከመቀሌ አቻው ጋር ጨዋታ ያደረገው የባህር ዳር ከነማ ክለብ ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ተፈረደበት
ኢሳት (ግንቦት 17 ፥ 2009) ከመቀሌ አቻው ጋር ሲጫወት በመቀሌ ደጋፊዎች ተደብድቦ ወደ አማራ ክልል የተመለሰው የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጥፋተኛ ተብሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅጣት ተጣለበት። የባህር ዳር ከነማ ክለብ በረኛን ጨምሮ 4 ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ተባርረው በ7ቱ ብቻ ወደ መቀሌ ሄዶ ደጋፊ በሌለበት ዝግ ስታዲየም ጨዋታው ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለው 16 ደቂቃዎች ከመቀሌ አቻው ጋር ውድድር ...
Read More »የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ የአንድ አመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት በየነ
ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰሞኑን የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ የአንድ አመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣር አርብ ሰጠ። ጋዜጠኛው የተላለፈበት የ 18 ወር እስራት ከእስር ቆይታው ጋር የሚቀረረብ በመሆኑ ተከሳሹ አመክሮ ታስቦለት ከእስር ይወጣል የሚል ግምት መኖሩን የህግ አካላት ገልጸዋል። ይሁንና ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስከ አርብ ከሰዓት በኋላ ድረስ ከእስር አለመለቀቁን ለመረዳት ተችሏል። ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለግብርና ዘርፍ ለስራ ማስኬጃ የሚሰጠውን ብድር አቋረጠ
ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2009) በቅርቡ ለግል የልማት ፕሮጄክቶች ሲሰጥ የቆየውን ብድር ያቋረጠው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለግብርና ዘርፍ ለስራ ማስኬጃ የሚሰጠውን ብድር አቋረጠ። ባንኩ የወሰደው ይኸው ተጨማሪ ዕርምጃ በተያዘው የክረምት ወር ብድርን ወስደው በግብርና ምርት ላይ ሲሰማሩ ለነበሩ ባለሃብቶች ያልታሰበ ድንጋጤ ማሳደሩን ካፒታል የተሰኘ የቢዝነስ ጋዜጣ ዘግቧል። የብሄራዊ ባንክ ከቀናት በፊት ተግባራዊ ያደረገው ይኸው መመሪያ የብድር ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ገንዘብ ...
Read More »ከኢሬቻ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ ግጭት አነሳስተዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ክስ ቀረበባቸው
ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2009) ከሳሽ አቃቤ ህግ ባለፈው አመት ከኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት ጋር በተያያዘ ተከስቶ የነበረውን ግጭት አነሳስተዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በሽብር ወንጀል መክሰሱ ታውቋል። ተከሳሾቹ ተፋ መልካ እና ከድር በዳሱ የተባሉ ግለሰቦች ሲሆን፣ በበዓሉ አከባበር ወቅት ከሃገር ሽማግሌዎች ድምፅ ማጉያን በመቀማትና ሁከት በማነሳሳት ለ55 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል ተብለዋል። ከሳሽ አቃቤ ህግ ሁለቱን ተከሳሾች የሽብር ወንጀል ድርጊት ...
Read More »በጎዴ አንድ የአይር ሃይል ባልደረባ በርካታ መኮንኖችን ገድሎ ራሱን ማጥፋቱ ተሰማ
ግንቦት ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር በምትገኘው ጎዴ ከተማ የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባል የሆነው የጎንደር ተወላጅ ወታደር በርካታ መኮንኖችን ገድሎ በመጨረሻም ራሱን አጥፍቷል። ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው በአየር ሃይል የምህንድስና ትምህርት ተምሮ ጎዴ በእግረኛ ወታደርነት መመደቡን ተከትሎ ነው። ምንጮች እንደገለጹት ፣ ወታደሩ ያለምንም ምክንያት ወደ ጎዴ ተወስዶ በእግረኛ ወታደር ...
Read More »