ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ አባላት ለኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጹት፣ ኢህአዴግን በመሰረቱት አራት ድርጅቶች መካከል ያለው መናበብ፣ ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ በመዳከሙ፣ አቅጣጫ ሰጥቶ የሚመራ አካል እየጠፋ ነው። በኢህአዴግ ታሪክ የአባላቱ መንፈስ በዚህ ደረጃ የወደቀበትን ጊዜ አናስታውስም የሚሉት አባሎቹ፣ ማእከላዊነት የሚባል ነገር በመጥፋቱ ሁሉም በራሱ የመሰለውን ውሳኔ እየሰጠ ነው ይላሉ። “አለመግባባቱ፣ ...
Read More »አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናን ምክንያት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ተቋረጠ
ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ ለሚጀመረው ፈተና ከማክሰኞ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቁዋረጡ በማህበራዊ ድረገጾች ተጠቃሚዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጥሯል። ቁጥራቸው 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በተጨማሪም 288 ሽህ የ12ኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መሰናዶ ብሄራዊ ፈተናውን በቀጣይ ሳምንት እንደሚወስዱ ሪፖርቶች አመላክተዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት ለ12 ሰዓታት ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ከትናንት ...
Read More »ሱዳን የግብጽ የግብርና እና የእንሣት ተዋጽኦ ምርቶች ወደ አገሯ እንዳይገቡ እገዳ ጣለች
ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱዳን መንግስት የካቢኔ አባላት የግብጽ የግብርና እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች ወደ አገራቸው እንዳይገባ ማገዳቸውን የሱዳን መንግስት ልሳን የሆነው ሱና የዜና አውታር ማክሰኞ እለት ዘገቧል። ካቢኔው አክሎም በቀጥታ ከጎረቤት ግብጽ በኩል ወደ ሱዳን የሚገቡ ማንኛውንም ምርቶች እንዳያስገቡ ለግል ባለሃብቶችም ማሳሰቢያ ሰጥቷል። በሱዳን እና በግብጽ መሃከል የተነሳው ውጥረት ከጊዜ ወደ ...
Read More »ለተረጂዎች ሲሰጥ የነበረ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ከሰኔ ወር ጀምሮ ሊያልቅ እንደሚችል ተመድ አሳሰበ
ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ተጋልጠው የሚገኙ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀጣዩ ሰኔ ወር ጀምሮ የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ሊያልቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪው የሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆን የእርዳታ አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን ድርጅቱ የድርቁን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ገልጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና መንግስት ...
Read More »ከ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ
ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) በመላው ኢትዮጵያ ረቡዕ መሰጠት ከጀመረው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ በሃገሪቱ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ። ብሄራዊ ፈተናው ተሰርቆ ሊሰራጭ እንደሚችል ስጋት መኖሩ ለአገልግሎቱ መቋረጥ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ኳርትዝ አፍሪካ የተሰኘ መጽሄት የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ረቡዕ ዘግቧል። በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ችግሩ ረቡዕ ድረስ የዘለቀ መሆኑን በመግለፅ ላይ ...
Read More »የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ነጻነት እንዲኖራቸው ፕሮፌሰር አድማሱ ጸጋዬ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ስርዓት ነጻነት እንዲኖረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር አድማጹ ጸጋዬ ጥሪ አቀረቡ። የመንግስት የፋይናንስ ህግ ማዕቀፎችም የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፋፋት እንቅፋት መሆናቸውን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መግለጻቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዩኒቨርስቲው በራሱ እቅድ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት በሚያከናውናቸው ፕሮግራሞች የሚሰበሰበው የውስጥ ገቢ ቢኖረውም የመንግስት የፋይናንስ ስርዓት ግን ዩኒቨርስቲው ...
Read More »የመን ወደ መፈራረስ እያመራች መሆኑን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የመን ሙሉ ለሙሉ ወደ መፈራረስ እያመራች መሆኗን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ሃገሪቱ ያጋጠማት የረሃብ አደጋና ዕልባት ማግኘት ያልቻለው የዕርስ በርስ ጦርነት የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና የመንግስታዊ ተቋማት መፈራረስ አደጋ እንዲጋረጥባቸው ማድረጉን የድርጅቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ሃላፊዎች ይፋ ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የየመን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ሪፖርተን ያቀረቡት የማስተባሪያ ...
Read More »በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ቀውስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ 11 አለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቋማት የተመድ ሰብዓዊ መብት ምክርቤትን ጠየቁ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ቀውስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አለም አቀፍ ተቋማት ጠየቁ። በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ 11 ድርጅቶች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ በጋራ ያቀረቡትን ጥያቄ ከምክር ቤቱ እንዲያስገቡ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። ፍሪደም ሃውስ፣ ኢንተርናሽናል ሰርቪስ ፎር ሂውማን ራይትስ፣ ሪፖርተርስ ...
Read More »የህወሃት መሪዎች የትግራይ ተወላጅ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በሃላፊነት እንዲሰራ ድጋፍ እንደማያደርጉ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣኑን የያዙት የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት መሪዎች የትግራይ ተወላጅ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በሃላፊነት እንዲሰራ ድጋፍ እንደማያደርጉ አንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ገለጹ። በአፍሪካ ልማት ባንክ እስከ ምክትል ፕሬዚደንትነት ለ15 አመታት ያገለገሉት አንጋፋው ኢትዮጵያዊ አቶ ተካልኝ ገዳሙ “Republican on the Throne” በተባለውና ከአመታት በፊት ለንባብ ባቀረቡት መጽሃፋቸው እንደገለጹት ለአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚደንትነት ሳይወዳደሩ የቀሩት ...
Read More »አንድ የአሜሪካ ወታደራዊ ኩባንያ አውሮፕላን በሶማሊያ ሞቃዲሾ ተከሰከሰ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) ንብረትነቱ የአንድ የአሜሪካ ወታደራዊ ኩባንያ የሆነ አውሮፕላን በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ከተማ በሚገኘው የኤዴን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ መከስከሱን ባለስልጣናት አስታወቁ። መነሻውን ከዩንጋንዳ አድርጓል የተባለው ይኸው ወታደራዊ አውሮፕላን አራት የምዕራባውያን ሃገራት ዜጎችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን፣ በመንገደኞች ላይ ጉዳት አለመድረሱን የቻይናው ዜና አገልግሎት ሺንሁአ ማክሰኞ ዘግቧል። ባንክሮፍት የሚባል ኩባንያ ንብረት የሆነው ወታደራዊ አውሮፕላኑ በአውሮፕላን ማረፊያው ለማረፍ ...
Read More »