ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ሕገወጥ ስደተኞች ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ የውጭ አገር ዜጎች አገርቷን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። የተለያዩ አገራት በኤንባሲዎቻቸውና በቆንስላዎች አማካኝነት ከቀረጥ ነጻ እቃዎቻቸውን እንዲያስገቡ ለዜጎቻቸው እገዛ እያደረጉ ነው። ፈቃደኛ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ግን ወደ ኤንባሲዎቸው በመሄድ ለመመለስ ቢጠይቁም የጉዞ ሰነዶችን በአፍጣኝ ለማግኘት ተቸግረዋል። ...
Read More »የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች አሰግድ ተስፋዬ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በልዩ የእግር ኳስ ክህሎቱ በመላው ኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ አድናቂዎች ተወዳጁ አሰግድ ተስፋዬ ቅዳሜ ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በድንገት መታጠቢያ ቤት ውስጥ በመውደቁ ሕይወቱ አልፏል። አሰግድ ተስፋዬ በ1962 ዓ.ም በድሬደዋ ከተማ ደቻቱ ውስጥ ተወልዶ በ47 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ዓመለ ሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ለድሬደዋ ጨርቃጨርቅ፣ መድህን ድርጅት፣ ...
Read More »አሜሪካ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የአለም ሙቀትን ለመቀነስ ከተደረሰው ስምምነት መውጣቷን ይፋ አደረገች
ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሃገራቸው ከሁለት አመት በፊት በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የአለም ሙቀትን ለመቀነስ ከተደረሰው ስምምነት መውጣቷን ይፋ አደረጉ። የፓሪስ ስምምነት በመባል የሚታወቀው ይኸው አለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነት በ187 ሃገራት መካከል ተቀባይነትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን፣ ዕርምጃውም የአለም ሙቀትን በሁለት ዲግሪ ሴንቲግሬድ ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ታውቋል። ይሁንና በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት የፓሪሱን ስምምነት ውድቅ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተው ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ተጠየቀ
ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) በቀጣዩ ሳምንት ጠቅላላ ጉባዔውን የሚያካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ውሳኔዎች እንዲያስተላልፍ አለም አቀፍ የሰብዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥያቄን በድጋሚ አቀረቡ። ሂማን ራይትስ ዎች፣ ፍሪደም ሃውስ ኢንተርናሽናል፣ ፌዴሬሽን ፎር ሂማን ራይትስ የተሰኙና ሌሎች ተቋማት ምክር ቤቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ውሳኔ እንዲተላለፍ ጠይቀዋል። ከቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ ለ15 ...
Read More »ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ከሌለባቸው ከመጨረሻዎቹ ሃገራት ተርታ መመደቧ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ከሌለባቸው የመጨረሻዎቹ አምስት ሃገራት ተርታ እንደምትመደብ ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ የተባለ አለም አቀፍ ተቋም ገለጸ። ተቋሙ የ2017 ጥናታዊ ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጸው ኢትዮጵያ ከ161 ሃገሮች ጋር ስትነጻጸር የሰላምና መረጋጋት እጦትን በተመለከተ 134 ደረጃ ላይ ትገኛለች። በጥናቱ መሰረት ኢትዮጵያ ሰላሟን እያጣቸው የመጣችው በሃገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ነው። በሃገሪቱ በከፊል በብሄር ...
Read More »የእርዳታ ምግብ አቅርቦት እጥረትን ተከትሎ 700ሺ ሰዎች ድጋፍ ሳያገኙ መቅረታቸው ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የእርዳታ ምግብ አቅርቦት እጥረትን ተከትሎ በግንቦት ወር እርዳታ ማግኘት የነበረባቸው 700 ሺ አካባቢ ሰዎች ያለምንም ድጋፍ መቅረታቸው ተገልጿል። በዚሁ የምግብ እጥረት ዙሪያ መግለጫን ያወጣው የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ወደ አራት ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በከፍተኛ የምግብ ችግር ውስጥ መሆናቸው አስታውቀዋል። ይሁንና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪው በቂ ምላሽ ባለመስጠቱ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ...
Read More »የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ 175 ት/ቤቶች መዘጋታቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ እየተባባሰ ያለውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ 175 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውንና ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በአፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች በዚሁ የድርቅ አደጋ ክፉኛ መጎዳታቸውን በድጋሚ ያወሳው ድርጅቱ በምግብ እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ህጻናት ተማሪዎች በመበራከታቸው ትምህርት ቤቶቹ ሊዘጉ መቻላቸውን ገልጿል። ከአደጋው ...
Read More »በግንቦት 20 በአል ሰበብ በተጠራው የመኮንኖች ስብሰባ ላይ የተነሱት ጥያቄዎች የመከላከያ አዛዦችን አሳስቧቸዋል።
ግንቦት ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንቦት 20 በአልን ምክንያት በማድረግ ለመከላከያ አባላት ገለጻ በተደረገበት ወቅት የጦር መኮንኖች ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎችና የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች ከዚህ በፊት ያልተለመዱና ያልታዩ በመሆኑ፣ ወታደራዊ አዛዦችን አሳስቧል። በቅርቡም በመካለከያ ውስጥ አዲስ ጥልቅ ተሃድሶ ሊጠራ እንደሚችል ምንጮች ተናግረዋል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ የመከላከያ መኮንኖች ግንቦት20ን በማስመልከት አገሪቱ ስለምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ተደርጎላቸው ...
Read More »በሳውድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሬታቸውን እየገለጹ ነው
ግንቦት ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በሳውድ አረቢያ ለአመታት በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የቆዩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በቂ አገልግሎት እየሰጠን አይደለም ብለዋል። ለተመላሽ ኢትዮጵያውያን የትራንስፖርት አገልግሎት ከማመቻቸት አንስቶ እቃዎቻቸውን ከቀረጽ ነጻ የሚያስገቡበት ሁኔታ እንደሚመቻችላቸው በመንግሰት መገናኛ ብዙሃን ሲገለጽ ሰንብቷል። የተለያዩ የኢህአዴግ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ ከዚህ ቀደም በተመለሱት ዜጎች ...
Read More »ኢንተርኔት መዘጋቱን ተከትሎ የመንግስትና የፓርቲ የመገናኛ ብዙሃን ሳይቀሩ ዜናዎችን ማውጣት አቆሙ
ግንቦት ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ የተዘጋውን የኢንትርኔት አገልግሎት ተከትሎ የውጩን ማህበረሰብ ስለአገሪቱና ስለመንግስቱ መልካም ገጽታ እንዲኖረው በሚል ዘገባዎችን የሚያቀርቡ የመንግስት ሚዲያዎች፣ የፓርቲ ሚዲያዎችና በፌስቡክ፣ በቲውተርና በድረገጻቸው የገዢውን ፓርቲ አወንታዊ ገጽታ ሲያቀርቡ የነበሩ ሁሉ እንቅስቃሴ አቁመዋል። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ከሆኑት መካከል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ የኢንተርኔት ገጻቸው የተዘጋ ...
Read More »