“ብአዴንንና ህወሃትን፣ ህወሃትንና ኦህዴድን ለማጋጨት ፀረ-ሰላም ሃይሎች የጠነሰሱትን ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ አግዘናቸዋል” ሲሉ አንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ተናገሩ

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ ብአዴን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካና ርእዮተአለም ብልሽት አጋጥሞታል። በ40 እና 50 አመታት ጊዜ ውስጥ የበለጸገ አገር የሚፈጥር መስመር ሆኖ እያለ፣ ይህንን መስመር በብቃት ባለማወቃችን ምክንያት ይህን መስመር እየተከላከልነው አይደለም” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ በእኛ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ብልሽት ምክንያት ከመስመራችን በተጻጻሪ ለቆሙ ሃይሎች አቅም ሆነን እንታያለን ሲሉ በተሃድሶ ስብሰባ ላይ ምሬታቸውን ...

Read More »

ዲፕሎማቶች የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይሳካል ብለው እንደማያምኑ ፋይናንሻል ታይምስ ዘገበ

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው የቢዝነስ ጋዜጣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ ይዞት በወጣው ጽሁፍ እንዳተተው ምንም እንኳ ቻይና መራሹ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የስራ እድል በመፍጠር በአገሪቱ ውስጥ የሚታየውን የስራ አጥ ቁጥር ትክክለኛ አካሄድ መስሎ ቢታይም፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ ዲፕሎማቶች አጠቃላይ የኢኮኖሚ እቅዱ ይሳካል የሚል እምነት የላቸውም። ዲፕሎማቶቹ ከሚጠቅሷቸው ምክንያቶች መካከል የፋይናንስ አገልግሎቱ ፣ ...

Read More »

በባህርዳር አየር ማረፊያ ላይ የተያዘውን ተቀጣጣይ ፈንጅ ተከትሎ በጥርጣሬ ሰዎች እየተያዙ ነው

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተያዙት ሰዎች መካከል አንደኛው ግለሰብ፣ እቃውን እንዳደርስ አንድ ሰው ላከኝ እንጅ ፈንጅ ይሁን አይሁን አላውቅም ብሎ የተናገረ ሲሆን፣ ከጎንደር መላኩንም ገልጿል። ፈንጁን ሰጥቶታል የተባለውን ሰው ለመያዝ፣ ከግለሰቡ ጋር መርመሪዎች ወደ ጎንደር ሊወስዱት ማሰባቸውን የኢሳት የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። አንድ የአየር መንገድ ሰራተኛም በቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮች ገልጸዋል።

Read More »

በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ሲሰቃዩ የነበሩ 120 ሶማሊያዊያን እስረኞች ተለቀቁ

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን ዓሊ ከይሬ ለ29ኛው አፍሪካ ሕብረት ስብሰባ በመጡበት በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ 120 ሶማሊያዊያን እስረኞችን ሰኞ እለት አስለቁ። ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ”ሁለታችንም መንግስታት በደረስንበት የጋራ ስምምነት አማካኝነት 120 ሶማሊያዊያን ዜጎቻችንን ከእስር ተፈተዋል።” በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ አሁንም ድረስ ስላሉት ሶማሊያዊያን ...

Read More »

የአፍሪካ ህብረት 29ኛው የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሰኞ ተጀመረ

የአፍሪካ ህብረት 29ኛው የመሪዎች ጉባኤ የአህጉራዊውን ተቋም የፋይናንስ ምንጭ በራሱ ለመሸፈን በሚያስችሉና አሰራሩን ለማጎልበት በሚያበቁ ጉዳዮች ለመምከር በአዲስ አበባ ሰኞ ተጀመረ ። ህብረቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባኤ በአህጉሪቱ የጸጥታና የሰላም ጉዳዮች ላይም እንደሚመክር ዘገባዎች አመልክተዋል ። የአፍሪካ ህብረት እስካሁን በነበረው ሁኔታ ወጪዎቹ የሚደጎሙት ከአውሮፓ ህብረትና ከተለያዩ እርዳታ ሰጪዎች በሚለገሰው ገንዘብ ነው ። ከዚህ በተጨማሪም የህብረቱ  ሃገራት የሚያዋጡት የአባልነት መዋጮ ገንዘብም ...

Read More »

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ዝግጅት በሲያትል ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ

34ኛ አመት ያስቆጠረው የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን ዠግጅት እሁድ July 2, 20172 በዋሽንግተን ሲያትል ሬንተን ስቴድየም ብዙ ሺህ ተመልካቶች በተገኙበት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መጀመሩን በስፍራው የተገኘው የኢሳት ጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ዘግቧል። በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ለ34ኛ ጊዜ በአሜሪካ ሲያትል ያዘጋጀው አመታዊ ስነ-ስርአት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ታዳሚ ተገኝቶበታል። የኢትዮጵያ ባህልና ወግ የተንጸባረቀበት ስነ-ስርአቱ የተከበረው በሬንተን ስቴድየም ከመሆኑ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የሚያቀርባቸው ሪፖርቶች በሃሰት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ተገለጸ

የኢህአዴግ ፓርላማ የመንግስት ልማት ድርጅት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)  የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀራረቡ  ያልሰራውን እንደሰራ አድርጎ ሰለሆነ የተሳሳተ መረጃ እንደመስጠት ተደርጎ ሊቆጠር እንደሚገባ ተናግረዋል ። የፓርላማው ተወካዮች እንደገለጹት ሜቴክ ከአቅሙ በላይ የሆኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመረከብ ለተራዘሙ አመታት በመንጓተቱ ፤ የሃገሪቱ የፋይናንስ ስርአትን ባልተከተለ ሁኔታ ገንዘብ ማባከኑ፤ የፕሮጀክት ባለቤቶች ከሆኑ መንግስታዊ ተቋማት ጋር ጤናማ ግንኙነት መፍጠር ...

Read More »

የኢትዮጵያ የሙስሊም ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላትን ጨምሮ 12 ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ጅዳ መታሰራቸው ተነገረ

ከታሰሩት መካከል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን እና ኡስታዝ ከማል ሸምሱ ይገኙበታል። 12ቱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በምን ምክንያት እንደታሰሩ ባይታወቅም የሳውዲ አረቢያ የደህንነትና የፖሊስ አባላት በትብብር ተቀናጅተው በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል። በሳውዲ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያን በዋስ ለማስፈታት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።  ለዋስትናም አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር መጠየቁ ተነግሯል ። የጀርመን ድምጽ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ እዳ ከ575 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ

በውጭ ምንዛሪ ቀውስ የሚታወሰው የህዉሃት/ኤህአዴግ አገዛዝ በ2009 አ.ም አመታዊ የውጭ ወለድ ክፍያው ከ3 ቢሊዮን ብር ወደ 10 ቢሊዮን ብር እንዲሁም አመታዊ የመንግስት የውጭ እዳ ክፍያ ከ14 ቢሊዮን ብር ወደ 25 ቢሊዮን ብር አድጓል። በዚህ ምክንያት ችግሩ የህዉሃት መራሹ መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ እየከተተው እንደሆነ ተገልጿል። ከፊሉን የውጭ እዳ ለማቃለል ከወጭ ንግድ ከሚገኘው የውጭ ምንዛሪ እሸፍናለሁ በማለት ቢገልጽም በየአመቱ ከውጭ ንግድ የሚገኘው ...

Read More »

ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተጣለው ግብር በመላ አገሪቱ ችግር እየፈጠረ ነው።

ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እዳ አለባቸው የሚባሉ ነጋዴዎች በባንክ ያስመቀጡትን ገንዘባቸውን እንዳያወጡ እገዳ እየተጣለባቸው መሆኑን ነጋዴዎች ገልጸዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለው ገዢው ፓርቲ፣ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጣነ ግብር እንዲከፍሉ በማድረጉ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ነጋዴዎች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው። “ የሌለንን ገቢ እንዳለን አድርጎ የሚጣለው ግብር” በኑሮአችን ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው የሚሉት ...

Read More »