የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት የቤት ግንባታ ተቋራጮች ገንዘባችንን ተቀማን ይላሉ

ሰኔ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተንዳሆ ቤቶች ልማት ግንባታ ምዕራፍ ሁለት ታሳተፊ ስራ ተቋራጮች ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓም ለተወካዮች ምክር ቤት፣ ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ለአቶ አህመድ አብተው በጻፉት ደብዳቤ ከ200 በላይ የስራ ተቋራጮች ለግንባታ ያወጡት ገንዘብ እንዲመለስላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ላሉ ባለስልጣናት ደብዳቤዎችን ቢጽፉም መልስ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ጠቅሰዋል። “254 ስራ ...

Read More »

የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግምባር / ጋህዴአግ/ የኦህዴድን የግዛት ማስፋፋት ጥያቄን እንደሚያወግዝ አስታወቀ

ኢሳት ዜና ሰኔ 29 2009    የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ / ከጋምቤላ ክልል ጋር በተያያዘ እያካሄደ ያለውን  ማስፋፋት ጥያቄ እንደሚያወግዝ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግምባር / ጋህዴአግ / ባወጣው መግለጫ አስታወቀ ። በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞም ሆነ የጋምቤላ ህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ የግዛት መስፋፋት አለመሆኑን  ጋህዴአግ  ገልጿል ። የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግንባር /ጋህዴአግ/ በመግለጫው እንዳለው ህውሃት መራሹ ገዢ ግምባር ...

Read More »

በአዲስ አበባ ጎርፍ ባስከተለው ዶፍ ዝናብ 5 ሰዎች ሞቱ

ኢሳት ዜና ሰኔ 29, 2009 በአዲስ  አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት ከፍተኛ ጎርፍ ባስከተለው ዶፍ ዝናብ 5 ሰዎች መሞታቸውን የአደጋ መከላከል ባለስልጣናት አስታወቁ ። በከተማዋ በስተደቡብ ጫፍ ላይ አንድን ወንዝ በመሻገር ላይ የነበሩ 4 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ መከላከል ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ንጋቱ ማሞ መግለጻቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል ። የቱርኩ የዜና ወኪል አናዱሉ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው እስከሁን የሁለት ...

Read More »

ዩኤንድፒ የአፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ተናኘወርቅ ጌቱ የጓደግኛቸውን ልጅ ካለውድድር ቀጠሩ

ኢሳት ዜና – ሰኔ 29, 2009   የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አማካሪ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ሴት ልጅ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ( ዩኤንድፒ ) በአባቷ እገዛ ያለውድድር እንድትቀጠር መደረጉን አንድ አለም አቀፍ የፕሬስ ተቋም አጋለጠ ። ኢንተር ሲቲ ፕሬስ የተሰኘውና በተባበሩት መንግስታት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚሰራው የሚድያ ተቋም እንዳለው የአምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚታየውን የትጥቅ ትግል ተንተርሶ እርሻ አለመታሩሱን ታጋዮች ተናገሩ

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርበኞች ግንቦት7 ስር ታቅፈው እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹት ታጋዮቹ ፣ ህወሃት ለአንድ አርበኛ ታጋይ 400 ያክል ወታደሮችን አሰልፎ ታጋዮቹን ለመፈለግ በሚያደርገው ዘመቻ አርሶአደሩ እየተያዘ እስር ቤት በመወርወሩ እርሻ አልታረሰም። “ አንድ ሰኔ የነቀለውን 10 ሰኔ አይተካውም “ የሚሉት ታጋዩ፣ “ከማረሻ ውጭ ምን አለን? ማረሻ ከተሰቀለ፣ ቀንበር ከተሰቀለ፣ ጅራፍ ከተሰቀለ ከዚህ ...

Read More »

የኩራዝ አንድ የስኳር ፕሮጀክት ምርት ጀመረ ተብሎ መዘገቡን ሰራተኞች አስተባባሉ ።ማኔጂመንቱና ሜቴክ እየተወዛገቡ ነው።

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት በአማራጭነት ያቋቋመው የቴሌቪዥን ጣቢያ ፣ ኢኤንኤን /ENN/ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ “ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በአካባቢው ነዋሪዎች ‘ፋብሪካው ሥራ የሚጀምረው በምጽዓት/በፍርድ ቀን ነው፣ ወይም የፋብሪካውን ሥራ መጀመር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው (ሜቴክም አያውቀውም)’ ሲባል የነበረው የኦሞ-ኩራዝ 1 የስኳር ፋብሪካ ምርት ጀመሮ ፤ በቀን 650 ቶን ስኳር እንደሚያመርት ፣ ...

Read More »

በአዲስ አበባ በደረሰ የጎርፍ አደጋ አምስት ሰዎች ሞቱ። የአባትና ልጅ አስከሬን እስካሁን አልተገኘም።

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በተከታታይ የጣለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በአዲስ አበባ አምስት የከተማዋ ነዋሪዎች መሞታቸውን የአደጋ ሰራተኞች አስታወቁ። የአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከያ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳሉት ”በመዲናዋ ደቡባዊ አዋሳኝ ላይ የሚገኝውን ወንዝ ለመሻገር በሚሞክሩበት ወቅት አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል።” በተጨማሪም በቦሌ ጃክሮስ ...

Read More »

በበቆጂ ከተማ የውሃ እጥረት ነዋሪዎችን አማረረ

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርሲ ዞን የምትገኘው የበቆጂ ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ሙሉ ለሙሉ በማጣታቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን አስታውቀዋል። በከተማዋ የነበረው ጥንታዊ የውሃ መስመር አገልግሎት መስጠት ካቆመ ረዥም ጊዜያት ሆኖታል። የከተማዋ መስተዳድርም ሆነ የውሃ ልማት ድርጅቱ የነዋሪዎችን የውሃ ችግር ለመፍታት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታይም። አንድ የአካቢው ነዋሪ ”እኛ የምንኖረው ኑሮ ኑሮ ...

Read More »

የአልሸባብ ታጣቂዎች በኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት አደረሱ

 ሰኔ 28/2009 የአልሸባብ ታጣቂዎች ረቡእ ጠዋት በኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሶስት ፖሊሶች ሲገደሉ ስድስት ቆስለዋል ። ላሙ በተባለች ሃገሪቱን ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስን መንደር በሚገኝ የኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ብዛት ያላቸው የአካባቢው ሰዎች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል ። ሰባት የሚሆኑ የፖሊስ አባላትም የደረሱበት አልታወቀም ። ውጊያው ለ10 ሰአታት መካሄዱን ያመለከተው የቢቢሲ ዘገባ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬድዮ የተመሰረተበት 7ኛ ግምት በቴነሲ ግዛት ናሽቪል ከተማ ተከበረ

 ሰኔ 28/2009 የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬድዮ የተመሰረተበት 7ኛ ግምት በቴነሲ ግዛት ናሽቪል ከተማ ተከበረ ። በከተማዋ የሚገኙ የኢሳት ደጋፌዎች በተገኙበትና በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደው መድረክ ኢሳትንና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ውይይትም ተካሂዷል ። የናሽቪል  የኢሳት ኮሚቴ ባዘጋጀውና ቅዳሜ ጁላይ 2/20/17 በተካሄደው ዝግጅት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንዲሁም ኮሜዲያን ክበበው ገዳ የተገኙ ሲሆን ከአጎራባቿ ከተማ ሜንፈስ የመጡ የኢሳት ደጋፊዎችና በዝግጅቱ ...

Read More »