አቶ ከበደ ተሰራ በኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ምህረት መለቀቃቸው ተነገረ ።

  (ኢሳት ዜና ሐምሌ- 6/2009)    በአርራጣ ብድርና በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተከሰው የ 25 አመት እስር ፍርደኛ የነበሩት አቶ ከበደ ተሰራ በኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ምህረት መለቀቃቸው ተነግሯል። አቶ ከበደ ተሰራ በአንድ ወቅት በአራጣ አበዳሪነታቸው የ አለም ባንክ (ወርልድ ባንክ) የሚል ቅጽል ስም በህብረተሰቡ ወቶላቸው  እንደነበር ይታውቃል። በፐሬዝደን ሙላቱ ምህረት የተደረገላቸው ኣቶ ከበደ ተሰራ 8 ዓመታት ከታሰሩ በኋላ 17 ዓመታት ...

Read More »

አቶ በቀለ ገርባ የተከሰሱበት የሽብር ክስ ወደ  ወንጀል ክስ እንዲቀየር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።

(ኢሳት ዜና ሐምሌ-6/2009) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የተከሰሱበትን የሽብር ክስ ወደ ተራ ወንጀለኝት እንዲቀየር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ። ፍርድ ቤቱ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት 22 የተቃዋሚ የፖለቲካ መረጃዎችና አባላት 17ቱ እንዲከላከሉ የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፎባቸዋል። 5 ተጠርጣሪዎች ደግሞ በነጻ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ውስኗል ። ፍርድ ቤቱ በቀጥታ በሽብር ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው ተከሰው ከነበሩት መካከል ጎርሜሳ አያና፣ ...

Read More »

የአምቦ ነጋዴዎች ተቃውሞ ሲያካሂዱ ዋሉ

ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ የግብር መክፈያ ቦታዎችም በአቤቱታ አቅራቢዎች እየተጨናነቁ ነው የእለታዊ ገቢ ግብር አሰራርን በመቃወም በአምቦ ከተማ ዛሬ ተቃውሞ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ አንድ የፌደራል ፖሊስ መኪና ሲቃጠል ፣ አንድ አውቶቡስና ሌሎች የመስሪያ ቤት መኪኖችም ተሰባብረዋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ 11 ሰአት ድረስ በከተማዋ ተኩስ ይሰማ ነበር። ወደ ...

Read More »

የአቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ ተበየነ

ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ሃሙስ ሀምሌ 6/2009 ዓም በዋለው ችሎት በኦፌኮው ም/ል ሊ/መንበር በአቶ በቀለ ገርባ ላይ የቀረበውን የሽብር ወንጀል ክስ በመቀየር ፣ በወንጀለኛ ህጉ አንቀፅ 257 ሀ ስር የተደነገገውን ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት ስር የተጠቀሰውን እንዲከላከሉ በይኗል። በጉርሜሳ አያና መዝገብ ከተከሰሱት መካካል ከ ተራ ቁጥር አንድ ...

Read More »

ወጣት ታዲዮስ በየነ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ታዲዮስ በምርጫ 97 ወቅት በቅንጅት ውስጥ ታቅፎ አዲስ አበባ ወጣቶችን በማደረጀትና በመምራት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በወቅቱ ካሰራቸው ወጣት የቅንጅ አመራሮች መካከል አንዱ ነበር። ወጣት ታዲዮስ በእስር ቤት ውስጥ ለ2 አመታት ያክል ታስሮ ከተፈታ በሁዋላ ወደ አውስትራሊያ ተሰዶ ፣ በነጻነት ትግሉ ውስጥ አስተዋጽኦ ሲያካሂድ ቆይቷል። በጓደኞቹ ...

Read More »

ከጋምቤላ እርሻ ስራ ጋር በተያያዘ ታግደው የነበሩት የትግራይ ባለሀብቶች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተደረገ

  (ሐምሌ -5/2009)በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ስር የተቋቋመው አጥኚ ቡድን ውላቸው እንዲቋረጥ ካደረጋቸው በጋምቤላ እርሻ ኢንቨስትመንት ከተሰማሩት ባላሃብቶች ውስጥ ቅሬታ ካቀረቡት 98 በመቶ ወደ ስራ መወሰኑ ነው የተገለጸው። በጋምቤላ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶችን እንቅስቃሴ ለማጥናት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ስር የተቋቋመው አጥኚ ቡድን ለተራዘመ ወራት ጥናት በማካሄድ የተሰጣቸውን የባንክ ብድር ለሌላ ተግባር ያዋሉ፣ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ያልገቡ ፣መሬቱን ለሶስተኛ ወገን ...

Read More »

በጣና ሐይቅ ላይ ኑሯቸውን መሰረት ያደረጉ ከ3 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አደጋ ላይ ወድቀዋል።

  (ሐምሌ– 5/2009)ከ50 ሺህ ሔክታር በላይ የሚሆነውን የጣና ሐይቅ በመሸፈን አደጋ የጋረጠው የእንቦጭ አረም የባህር ዳር ከተማን ጨምሮ በምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብና ሰሜን ጎንደር ዞኖች የሚገኙ ህይወታቸውን ብርጣና ሐይቅ ከሚገኝ የምስኖ እና አሳ ምርት ያደረጉ ዜጎች ላይ መውደቃቸውን መረጃዎች አመላክተዋል። በተለይም የጣና ሐይቅ በሚያዋስናቸው ሰሜን ጎንደር፣ ጎርጎራ፣ አቼራ፣ ደንቢያ፣ ደንቢትና ማክሰኝት አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በተስፋፋው አረም ምክንያት የአሳ ምርቱ በእለት ተእለት ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ግጭት አገርሽቶ በሺ  የሚቆጠሩ ወደ ኢትዮጵያ ፈለሱ

  (ሐምሌ- 5/2009)በደቡብ ሱዳን በላይኛው ናይል ፓርክ ግዛት በደቡብ ሱዳን መንግስት ኃይሎችና በተቀናቃኙ የቀድሞው ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቸር ወታደሮች መካከል ግጭት በማገርሸቱ በሺ የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያ ፈልሰዋል። ሬዲዮ ታማዙጅ እንደዘገበው ወደ 5,000 የሚጠጉ ደቡብ ሱዳናውያን ግጭቱን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ሲሆን በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ልዑክ ዴቪድ ሺረር ግጭቱ በአገሪቱ ሰላም ለምስፈን የሚደረገውን ጥረት እንደሚያስተጓጉል ተናግረዋል። በዚሁ በሪክ ...

Read More »

ወያኔ ሀርነት ትግራይ የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማነሳት ጭንቅ ውስጥ ገብቷል

(ኢሳት-ሐምሌ 5/2009) በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ /ሕወሃት/ የሚመራው አገዛዝ ባለፈው አመት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው አመጽ ዳግም ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል የገባበት ውጥረት አሁንም እንደተባባሰ መሆኑን ነው የኢሳት ምንጮች እየገለጹ ያሉት። ለዚህ ደግሞ በአማራ፣ በኦሮሚያና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ ቀጥሏል ወያኔ ሃርነት ትግራይ እመራዋልሁ ከሚለው ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ቢቀርቡልትም በሰላማዊ መንገድ መልስ ከመስጠት ይልቅ የሀይል እርምጃ መውሰድን አማራጭ ...

Read More »

ቻይና በጅቡቲ ወደብ የጦር ሰፈሯን ገነባች 

  (ኢሳት ሐምሌ 5/2009)የቻይና የባህር ሀይል የአፍሪካ ትንሿ ሀገር በመባል በምትታወቀው ጅቡቲ የጦር ሰፈሩን ከመመስርቱ በፊት እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 በአካባቢው ጉብኝት አድርጎ ነበር። የቻይና ጦር ሰራዊትን የያዘችው መርከብ በአካባቢው ጉብኝት ስታደርግም ቤጂንግ ከሀገር ውጭ ለምትገነባው የጦር ሰፈር መሰረት የጣለችበት ወቅት እንደነበር ነው ዥንዋ በዘገባው ያመለከተው። የጦር ሰፈሯን በጀቡቲ ያደረገችው ቻይና የባህር ሃይሏ ተልእኮ በዋናነት የሰላም ማስከበርንና የሰብአዊ እርዳታን በአፍሪካና በምእራብ ...

Read More »