(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 10/2009) ከግብር ጫናና ትመና ጋር ተያይዞ እንደገና ያገረሸው ተቃውሞ በርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎችን እያዳረሰ ይገኛል። በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ በተለያዩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኦሮሚያ ተጨማሪ ወታደሮችን እየላከ መሆኑ ተነግሯል። በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው አምጽ በአምቦ ጀምሮ ጊንጪና ጀልዱ እንዲሁም ወሊሶና ቡራዩን አዳርሷል። በሻሸምኔ፣በኮፈሌና አርሲም ተመሳሳይ ሕዝባዊ ተቃዋሚዎች መኖራቸው ነው የተነገረው። በጊንጪ የስራ ማቆም አድማ ሙሉ በሙሉ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።የንግድ ቤቶች፣ሱቆችና ሆቴሎች ተዘግተዋል። ...
Read More »ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም አረፉ።
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 10/2009) አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም በ93 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ስርአተ ቀብራቸው ሐምሌ 11/2009 በጉርድ ሾላ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ተነግሯል። አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥንን በመምራትና የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና በሬዲዮ እንዲሁም በቴሌቪዥን በጋዜጠኝነት ሙያ ሲሰሩ በሙያው ዘመናዊ ትምህርት ከተማሩ የቀድሞ ጋዜጠኞች አንጋፋ እንደነበሩ የህይወት ...
Read More »ባህታዊ አባ ብርሃኑ ካልተፈቱ ህዝባዊ ተቃውሞ ይቀጥላል ተባለ።
(ኢሳት ዜና — ሐምሌ 10/2009) በደብረታቦር በሕዋሃት/ኢህአዲግ አገዛዝ የታሰሩት ባህታዊ አባ ብርሃኑ ካልተፈቱ ሕዝባዊ ተቃውሞአቸውን ለመቀጠል የከተማዋ ነዋሪዎች ተስማሙ። የከተማዋ ከንቲባ የሕዝቡን ቁጣ በመፍራት ባህታዊው አባ ብርሃኑ ሐምሌ 12/2009 ባላቸው ቀጠሮ መሰረት ከእስር እንደሚፈቱ ማረጋግጫ ቢሰጡም የአካባቢው ነዋሪዎች የጀመሩትን ተቃውሞ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። በደብረታቦር በኢየሱስ ደብር ቅጥር ግቢ ተራራማ ቦታ ላይ የቴሌቪዥን ታወር ነው በሚል ሲካሄድ የነበረው ግንባታም በሕዝብ ተቃውሞ እንዲቆም ...
Read More »በአርባምንጭ አንድ ህንጻ ተደርምሶ 4 ሰዎች ሞቱ።
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 10/2009) በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በሚገኘው አርባ ምንጭ ከተማ አንድ ባልሁለት ፎቅ ህንጻ ተደርምሶ 4 ሰዎች ሞቱ። 11 ሰዎች ደግሞ ቆስልዋል በተደረመሰው ሕንጻ ፍርስራሽ ስር ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መቀበራቸውንም ዥንዋ በዘገባው አመልክቷል። የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኢዞ ኢማጎ የሕንጻው ባለቤት ደረጃውን ያልጠበቅ የህንጻ ግንባታ አካሂደዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። በህንጻው ስር የተቀበሩት ሰዎች ስላሉበት ሁኔታና ሰዎቹን ለማዳን ...
Read More »አዲስ አበባ መስተዳድር ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ለብክነት ተዳርጓል
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 10/2009)የአዲስ አበባ መስተዳድር ምክር ቤት ሰሞኑን ጉባኤውን አካሂዷል’።የከተማዋ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2008 በጀት ዓመት ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አቅርቧል። ሪፖርቱ እንዳመለከተውም ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ያለ አግባብ ባክኗል።– 500 ሚሊየን የሚሆን የህዝብና የመንግስት ገንዘብ ደግሞ በወቅቱ መሰብሰብ አልተቻልም። ከዚህም ሌላ በወቅቱ ያልተወራረደ 200 ሚሊዮን ብር፣ ለማን እንደተከፈለ ማስረጃ የሌለው 257 ሚሊዮን ብር እንዲሁም አዋጅና መመሪያን ሳይከተል ለውሎ ...
Read More »በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የስራ ማቆም አድማ በመደረግ ላይ ነው
ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእለታዊ ገቢን ተንተርሶ የተጣለውን ግብር በመቃወም ለ3 ቀናት የተጠራው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ሰኞ ተጀምሯል። ባለፈው ሳምንት ተቃውሞአቸውን ወደ አደባባይ በመውጣት ያሰሙት የአምቦ ነዋሪዎች፣ ዛሬ የንግድ ድርጅቶቻቸውንና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በመዝጋት ተቃውሞአቸውን በመግልጽ ላይ ናቸው። በአምቦ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ ትምህርት ቤቶችና አንዳንድ ባንኮች ተዘግተዋል። ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶችም ተዘግተዋል። ...
Read More »በቡሌ ሆራ የኦህዴድ ካድሬዎች ወጣቶችን አደራጅተው “ዘረኝነት የተሞላበት ቅስቀሳ” ሲያካሂዱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት እሁድ የኦህዴድ ካድሬዎችና የቀበሌው ሊቀመንበር ወጣቶችን አደራጅተው፣ በከተማዋ የሚኖሩ የሌሎች ብሄረሰቦች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅተው እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሙስሊሞች እና በአንድ ግለሰብ መካከል የቀብር ቦታን አስመልክቶ የ ድንበር ውዝግብ መነሳቱን የሚገልጹት የአይን ምስክሮች፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ካቢኔዎችንና ታጣቂዎችን ሰብስቦ ወደ ቦታው ሲሄድ፣ በአካባቢው ከነበሩ ሙስሊሞች ጋር ...
Read More »በአርበኞች ግንቦት7 አባልነት በተከሰሱት ላይ ምስክሮች ተሰሙ
ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት አቃቢ ህግ በአርበኞች ግንቦት7 ስም በከሰሳቸው በእነ ትንሳኤ በሪሶ ላይ የደረጃ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል። የቀረቡት ሁለቱም ምስክሮች ማዕከላዊ ዐንጀል ምርመራ ቃላቸውን ሲሰጡ ታዝበናል ያሉ የደረጃ ምስክሮች ናቸው። እንዳልክ ዘርፉ የተባለው በአፍሪካ ህብረት ሰራተኛው በአቶ ትንሳኤ በራሶ ላይ የመሰከረ ሲሆን፣ አቶ ትንሳኤ “አይ ኤስ ...
Read More »ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ የዋስትና መብት ተፈቀደላቸው
ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው በእስር ሲሰቃዩ የነበሩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ሲል የቦሌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት ሀምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ብይን ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ተከሳሾች ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብሎ የዋስትና መብታቸውን ከመቀበሉ በተጨማሪ ጉዳያቸው ...
Read More »ደቡብ ሱዳን 14 ዳኞችን ከስራ አባረረች
(ኢሳት ዜና– ሐምሌ 7/2009)የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ከስልጣን የሚያባርሩት አመራር እየተበራከተ መቷል ይላል የሀገሪቱ የዜና ኮርፖሬሽኝ በዘገባው። ምናልባትም ሳልቫኪር ለመንግስታቸው ስጋት ናቸው ያሏቸውን ብሎም ከተቃዋሚ ሃይል ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል በሚል ፓርቲያቸው ጥርጣሬ ከገባው ያለምንም ምክንያት ባለስልጣናቱን ከቦታቸው ለማባረር ወደ ኋላ አይሉም ሲል ዘገባው ያክላል። ለዚህም ማሳያ አድርጎ የሚያቀርበው የሃገሪቱ የጦር አዛዥ የነበሩት ጄምስ ሆዝ ማይና የተለያዩ የፖሊስ ከፍተኛ ...
Read More »