የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄያ በአንድ ወር ለ6ኛ ግዜ ተቀጠረ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 2/2009)የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄ በአንድ ወር ለ6ኛ ግዜ ተቀጠረ። ፍርድ ቤቱ ብይኑን ዳኞች አልተሟሉም፣ዳኞች ታመዋል በሚል በማራዘም ላይ መሆኑም ታውቋል። የተመሰረተባቸው የአሸባሪነት ክስ ዝቅ ብሎ ጉዳያቸው በወንጀል ክስ እንዲታይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈው ከሶስት ሳምንት በፊት ቢሆንም የዋስትና ጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኝ ለ6ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ...

Read More »

በባህርዳር የተካሄደውን አድማ ተከትሎ ወጣቶች እየታፈሱ ነው

(ኢሳት ዜና —ነሐሴ 2/2009) በባህርዳር የተካሄደውን አድማ ተከትሎ በምሽት መብራት በማጥፋት ወጣቶች እየታፈሱ መሆናቸው ተነገረ። የወጣቶቹ መታሰር በህዝብ ውስጥ ቁጣን ፈጥሯል። ከአድማው መመታት በኋላ ከፓፒረስ ሆቴል ወደ ቡና ባንክ መሄጃ ማንነቱ ያልታወቀ ወጣት ተገድሎ ተገኝቷል። በባህር ዳር የንግድ መደብሮችና ሆቴሎች ረፋዱ ላይ ተከፍተዋል።ይሁንና የአገዛዙ ባለስልጣናትና ታጣቂዎች አሁንም በስጋትና በፍርሃት ውስጥ መሆናቸው ነው የተነገረው። አድማ በታኝ ወታደሮችና የጸጥታ ሃይሎች የርእሰ መስተዳድሩን ...

Read More »

በደብረታቦር የተጀመረው አድማ ቀጥሎ ዋለ

(ኢሳት ዜና– ነሐሴ 2/2009)በደብረታቦር ከተማ የተጀመረው አድማ ቀጥሎ መዋሉ ታወቀ። በከተማዋ ሁሉም መደብሮች እንደተዘጉ ናቸው። የአካባቢው ባለስልጣናት በከተማዋ እየዞሩ የንግድ ተቋማትን ማሸጋቸውንም ያገኘንው የምስልና የቪዲዮ ማስረጃ ያመለክታል። በደብረታቦር፣በወረታ፣በወልዲያና በተለያዩ አዋሳኝ አቅራቢያዎች የተመታው የህዝብ አድማ ሰበቡ ከግብር ጋር የተያያዘ ቢሆንም አጠቃላይ ምክንያቱ ግን በአገዛዙ መማረርና የአስተዳደር በደል ነው። በተለይ በደብረታቦር ህዝቡ እየደረሰበት ያለው ችግር ከትእግስት በላይ እንደሆነበት የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ይህንኑ ...

Read More »

የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 1/2009) የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች ዶክተር መራራ ጉዲናን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ የስራ ማቆም አድማ አደረጉ። በአምቦ ተሽከርካሪዎችና የንግድ መደብሮች ሙሉ በሙሉ ተዘግተው መዋላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የስራ ማቆም አድማው ለተከታታይ ቀናት ይቀጥላል ተብሏል። በአምቦና ወሊሶ እንዲሁም በአካባቢዎቹ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ዶክተር መራራ ጉዲናና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ነው። ዶክተር መራራና አቶ በቀለ ገርባና ሌሎችም ...

Read More »

ማንኛውም የንግድም ሆነ የግድግዳ ላይ ማስታወቂያዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አስገዳጅ ህግ ወጣ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 1/2009) ማንኛውም የንግድም ሆነ የግድግዳ ላይ ማስታወቂያዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አስገዳጅ ህግ ማውጣቱን የትግራይ ክልል መስተዳድር አስታወቀ። አዲስ አድማስ የክልሉን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጠቅሶ እንደዘገበው የንግድ ምልክቶቹ በተዘበራረቀ ቋንቋ መጻፍ የለባቸውም በሚል በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አስገዳጅ ህግ ተደንግጓል። ታዛቢዎች እንደሚሉት ደግሞ በትግርኛ ቋንቋ ብቻ የንግድ ምልክቶች በአስገዳጅ እንዲጻፉ በክልሉ ህግ የወጣው በራያና በወልቃይት ያሉ ነዋሪዎች ...

Read More »

በባህርዳር በሕወሃት አጋዚያን የተጨፈጨፉት ከ50 በላይ ወጣቶች ለማሰብ የተጠራው አድማ በስኬት ተጠናቀቀ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 1/2009) በባህርዳር በሕወሃት አጋዚያን የተጨፈጨፉ ከ50 በላይ ወጣቶችን ለመዘከር የተጠራው አድማ በስኬት ተከናወነ። የንግድ መደብሮች ሲዘጉ፣ተሽከርካሪዎች ደግሞ እንቅስቃሴ ባለማድረግ በግፍ የተገደሉትን የባህርዳር ወጣቶች በሐዘን አስታውሰዋል። አድማው ሌሎች የተወሰኑ የአማራ ክልል ከተሞችንም አዳርሷል። የባህርዳር ከንቲባ አቶ አየነው በላይና የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ዳኘው አድማው መደረጉን አምነው የንግድ ተቋማቱን ለማስከፈትና ተሽከርካሪዎችን ስራ ለማስጀመር የማግባባት ስራ መካሄዱን ገልጸዋል። የተወሰኑ ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል የቻይናውያን ንብረት የሆነው የቆዳ ፋብሪካ የሚያደርሰውን ጉዳት የተቃወመው የሰራተኛ ማሕበር ሊቀመንበር ከስራ ታገደ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 1/2009)በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ የቻይናውያን ንብረት የሆነው የቆዳ ፋብሪካ የሚያደርሰውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተቃወመው የሰራተኛ ማሕበር ሊቀመንበር ከስራ ታገደ። አንዲት ሰራተኛ ሁለት እጆቿን ሙሉ ለሙሉ ስታጣ፣ከስምንት በላይ ሰራተኞች ደግሞ ከፍተኛ አደጋ ደርሶባቸዋል። ከአምስት አመት በፊት ተገንብቶ ወደ ስራ የገባውና ከ1500 በላይ ሰራተኞች ያሉት ይህ የቆዳ ፋብሪካ ለሰራተኞች የደህንነት ጥበቃ የሚያደርጉ አሰራሮችንም ሆነ ቁሳቁሶችን ማሟላት አልቻለም በዚህም የፋብሪካው ...

Read More »

የውጭ ሀገር ምንዛሪ ይዛችሁ ተንቀሳቅሳችኋል የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 1/2009)የውጭ ሀገር ምንዛሪ ይዛችሁ ተንቀሳቅሳችኋል የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን በሳምንቱ መጨረሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የታሰሩት ግለሰቦች በአለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል። የውጭ ሀገር ምንዛሪ ይዛችሁ በሚል በተለይ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ተነጣጥሯል በተባለው በዚህ የእስራት ዘመቻ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የውጭ ዜጎችና ቤተሰቦቻቸው ጭምር ሰለባ መሆናቸው ...

Read More »

በአንድ ወጣት ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው ወላጆች ፍትህ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 28/2009) በአንድ ወጣት ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው ወላጆች ፍትህ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ። በአዲስ አበባ ጉለሌ አባዲና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ6 እስከ 8 አመት የሚሆናቸውን ዘጠኝ ህጻናት ወንዶችን የደፈረው ወጣት በእስር ላይ ቢሆንም እስካሁን ግን ፍትህ እንዳላገኙ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። የተደፈሩት ህጻናት ለከፍተኛ የጤናና የስነልቦና ችግር ተዳርገዋል። ሽንትና አይነምድራቸውን መቆጣጠር አልቻሉም።ወላጆቻቸው እንደሚሉት ህጻናቱን የደፈረው ወጣት ወላጅ አባት እያስፈራሯቸው ነው። በልጆቻቸው ላይ ከደረሰው ...

Read More »

በባህርዳር ከ50 በላይ ወጣቶች የተጨፈጨፉበትን ቀን ለማሰብ ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 28/2009) በአንድ ቀን ብቻ በህወሃት አጋዚያን ከ50 በላይ ወጣቶች የተጨፈጨፉበትን ቀን በሀዘን ለማስታወስ በባህር ዳር ነሐሴ 1/2009 ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ። የወጣቶቹን 1ኛ አመት ጅምላ ግድያ በሀዘን ለማስታወስ ከቤት ያለመውጣት አድማውን ለሰኞ የጠራው የባህርዳር ወጣቶች አስተባባሪ ኮሚቴ በሚል በህቡእ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው። በሕወሃት አጋዝያን ጭካኔ ኮብል በተባለ አካባቢ በአንድ ስፍራና ሰአት የተረፈረፉትን ወጣቶች ለማስታወስ የጎንደር ከተማ ህዝብም ከቤት ...

Read More »