(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 30/2009)በአማራ ክልል ለትግራይ ተወላጆች የተለየ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ተሰጠ። ትላንት በባህርዳር በተደረገ ሚስጥራዊ ስብሰባ በህወሀት የበላይነት ከተያዘው ብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት በመጡ ሰዎች አማካኝነት የቀድሞው ውሳኔ ተቀልብሶ ከዛሬ ነሀሴ 30 2009 ጀምሮ በአማራ ክልል ነዋሪ ለሆኑ የትግራይ ተወላጆች የ24ሰዓት ጥበቃ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ መተላለፉ ታውቋል። ከሶስት ሳምንት በፊት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው በመሩት ስብሰባ ሀሳቡ ቀርቦ ...
Read More »በትግራይ ክልል ያለው ልማት በሶማሌ ክልልም ቢተገበር በአካባቢው ለተከሰተው አሳሳቢ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይጠቅማል ተባለ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 30/2009)በትግራይ ክልል ያለው ልማት በሶማሌ ክልልም ቢተገበር በአካባቢው ለተከሰተው አሳሳቢ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይጠቅማል ሲሉ ሶስት ከፍተኛ የተባበሩት መንግስታት ባለስልጣናት አሳሰቡ። በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ሁኔታውን ለመገምገም ወደ ስፍራው የተጓዙት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለውን ልዩነትም መታዘባቸው ተመልክቷል። የተለያዩ ጥናቶችና ሪፖርቶች በትግራይ ክልልና በተቀሩት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰፊ ልዩነት እንዳለ ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል። ባለስልጣናቱ የሶማሌ ክልልን ህዝብ ...
Read More »የሕወሃት መንግስት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ከፍተኛ አመራር በራሳቸው ፈቃድ እጃቸውን ሰጡ ሲል መግለጫ አወጣ
(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 29/2009) የሕወሃት መንግስት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ከፍተኛ አመራር በራሳቸው ፈቃድ እጃቸውን ሰጡ ሲል መግለጫ አወጣ። የኦብነግ ከፍተኛ አመራር አብዱልከሪም ሼክ ሙሴ በሶማሊያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች እንዲሁም በፕሬዝዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትብብር ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው ባለፈው ሳምንት የተገለጸ ሲሆን ይህንንም የሚያረጋግጡ የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃዎች መሰራጨታቸው ታውቋል። የሕወሃት መንግስት ግለሰቡን በፈቃዳቸው እጃቸውን ሰጡ በሚል ለፕሮፓጋንዳ ሊጠቀምበት እንደሚችል ከግንባሩ ...
Read More »ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ የተሰኘውን የሙዚቃ አልበሙን ለማስመረቅ ያዘጋጀው መርሐ ግብር በመጨረሻው ደቂቃ እንዳይካሄድ ታገደ
(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 29/2009) ዝነኛው የሙዚቃ ሰው ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ የተሰኘውን የሙዚቃ አልበሙን ለማስመረቅ ያዘጋጀው መርሐ ግብር በመጨረሻው ደቂቃ መከልከሉ ብዙዎችን ማስቆጣቱ ተሰማ። ድምጻዊው ቴዲ አፍሮ ቴድሮስ ካሳሁንም ስለተፈጠረው ሁኔታ ማብራሪያ በመስጠት ከሕግ ውጪ የሆነ ድርጊት እንደተፈጸመበት አስታውቋል። ኢትዮጵያ በሚለው የሙዚቃ አልበሙ ይበልጥ ተወዳጅነቱ እየጨመረ የመጣውና በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር ሽፋን ያገኘው ቴድሮስ ካሳሁን በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በአለም አቀፍ ...
Read More »ለሀገር ነጻነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የቀድሞ የሀገር መከላከያና ፖሊስ ሰራዊት ማህበር ስራ አስፈጻሚ አባላት ገለጹ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 29/2009) ወጣቱ ትውልድ ለሀገር ነጻነት የሚያደርገውን ትግል በመደገፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የቀድሞ የሀገር መከላከያና ፖሊስ ሰራዊት ማህበር ስራ አስፈጻሚ አባላት ገለጹ። ማህበሩ 3ኛ አመታዊ በአሉን ባለፈው ቅዳሜ በአትላንታ ማካሄዱን በተመለከተ የስራ አስፈጻሚ አባላቱ ሻለቃ ደምሴ ዮሐንስና ሻለቃ ሱራፌል ዘውዴ ለኢሳት እንደገለጹት የቀድሞ ሰራዊት አባላት አሁን ባለው አገዛዝ ቢበተንም አሁንም ለሀገሩ ያለው ፍቅር ያልተነካ ነው። እናም ዛሬም ነገም አሁን ...
Read More »የኢትዮጵያ ቀን በሜሪላንድ ግዛት ተከበረ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 29/2009)የኢትዮጵያ ቀን በሜሪላንድ ግዛት ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ በድምቀት ተከበረ። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም 3 /2017 የተከበረው ይሕ ቀን በርካታ ኢትዮጵያውያን በባህላዊ ምግቦች፣አልባሳትና ታሪካዊ ቅርሶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢሳት በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ያናገራቸው ታዳሚዎች ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በአገዛዙና በሌሎች ጠላቶች ዘመቻ በተከፈተበት ሁኔታ በሜሪላንድ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰጡት የአጸፋ ምላሽ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። በክብረ በአሉ ላይ የተገኙት የሞንጎሞሪ ካውንስል ፕሬዝዳንት ሮጀር ...
Read More »የኦብነግ ከፍተኛ አመራር ለህወሃት መንግስት ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ በሶማሊያ ሶስት ከተሞች ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 26/2009) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ከፍተኛ አመራር ለህወሃት መንግስት ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ በሶማሊያ ዛሬ በሶስት ከተሞች ተቃውሞ መቀስቀሱ ተሰማ። የኦብነግ አመራር አባል አብዱልከሪም ሼህ ሙሴ ተላልፈው የተሰጡት በዚህ ሳምንት ውስጥ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ እንደተወሰዱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህን በመቃወም ህዝቡ ዛሬ በሞቃዲሾ፣ ኪስማዩና በዶብሌይ ሰልፍ መውጣቱ ታውቋል። የሶማሊያ በርካታ መገናኛ ብዙሃንም ድርጊቱን በማውገዝ እየቀሰቀሱ ሲሆን በኬኒያ ...
Read More »የኢድ አልድሃ አረፋ በዓል ዛሬ በመላው ዓለም ተከበረ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 26/2009) የኢድ አልድሃ አረፋ በዓል ዛሬ በመላው ዓለም ተከበረ። ለ1438ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢድ አለድሃ በዓለ በተለይ የሙስሊሞች መዲና በሆነችው መካ ከ2ሚሊየን በላይ ተጓዦች ከመላው ዓለም በመሰባብሰብ ማክበራቸው ታውቋል። በዓሉ በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያም የተከበረ ሲሆን እዚህ በዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢው በፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን አማካኝነት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የኢድ አል አድሃን በዓል ማክበራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ ለዘንድሮ የሃጂ ...
Read More »በኢትዮጵያ የልማት ድርጅቶች የወሰዱት ብድር የመመለሺያ ጊዜው በመድረሱ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቁ ተሰማ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 26/2009) ኢትዮጵያ ያለባት እዳ 40 ቢሊየን ዶላር በደረሰበት በአሁኑ ወቅት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከተለያዩ ዓለምዓቀፍ አበዳሪዎች የወሰዱት ብድር የመመለሺያ ጊዜው በመድረሱ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መወደቁ ተሰማ። ሐገሪቱ በወጭ ንግድ የምታገኘው ገንዘብ ከአመት አመት እየቀነሰ በቀጠለበትና 3 ቢሊየን ዶላር ማድረስ ባልተቻለበት ሁኔታ መንግስት በዚህ አመት የሚጠበቅበትን የ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር መክፈል የሚችልበት አማራጭ እንደሌለውም የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ...
Read More »የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሐገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ እንዲካሄድ ወሰነ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 26/2009) የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሐገሪቱ በቅርቡ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ እንዲካሄድ ውሳኔ ሰጠ። በኬንያ በተቃዋሚው እጩ ፕሬዝዳንት ራይላ ኦዲንጋ የሚመራው ፓርቲ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ክስ መስርቶ ነበር። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም በተቃዋሚዎች የቀረበውን ማስረጃና ክርክር አድምጦ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኬንያውያን ድምጽ ሰጥተው የሐገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አሸንፈውበታል የተባለውን ምርጫ ሰርዞታል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ምርጫው እንደገና ይካሄድ ...
Read More »