(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) በጣና ሃይቅ ላይ የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር በባህርዳር ስታዲየም እንዳይካሄድ ታገደ። ውድድሩ በጠባብ ስታዲየም እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን ወሳኔውም በኳስ ሜዳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት መሆኑም ተመልክቷል። የእምቦጭ አረም በጣና ሃይቅ ላይ ያደረሰውን ጉዳትና የደቀነውን አደጋ ለማስገንዘብና ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ለመሳተፍ የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ቡድን ...
Read More »ኤች አር 128 እንዲጸድቅ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሳይዘናጉ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) በአሜሪካን ኮንግረስ ለውሳኔ የቀረበው ኤች አር 128 እንዲጸድቅ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሳይዘናጉ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ። በአውሮፓና በሌሎች ክፍለ አለማት የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እየሰጡ መሆኑም ታውቋል። በቀጣይም በመላው አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በግፍ ለታሰሩት ጋዜጠኞች፣የፖለቲካ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶች ተከራካሪ በመሆን በያሉባቸው ግዛቶች ለሚገኙ የምክር ቤት አባላት ቢሮአቸው በመገኘት፣በደብዳቤና በስልክ መልዕክታቸውን እንዲያደርሱ ጥሪ ቀርቧል። በዋሽንግተን ዲሲና ...
Read More »ከአባይ ግድብ ፕሮጀክት ከ2ሺህ በላይ ሰራተኞች መቀነሳቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010)ከአባይ ግድብ ፕሮጀክት ከ2ሺህ በላይ ሰራተኞች መቀነሳቸው ተገለጸ። በገንዘብ እጥረት ወደፊት መቀጠል ያልቻለው የግድቡ ግንባታ በመጀመሪያው ዙር ከተቀነሱት ሌላ በቀጣይ ሌሎችም እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ቀደም ሲል ለበዓል ወጥተው የነበሩ ሰራተኞች በዚያው እንዲቀሩ መድረጉንም ታውቋል። ከ8ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት የሚነገረው የግድቡ ፕሮጀክት በተከታታይ ዙሮች ሰራተኞቹን እንደሚያሰናብት የውስጥ ምንጮች ካደረሱን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የተለያዩ የፕሮጀክቱ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችም የግድቡን ...
Read More »እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ93 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) በአፋር ክልል በአምቤዬራ ዞን፣በጅማ፣በደቡብ ምስራቅና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከ93 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ። የአፍሪካ ጋዜጠኞች ማዕከል/ሲ ኤ ጄ/ እንደዘገበው አዲስ አበባን በሚያዋስኑ ልዩ ዞኖችና በተጠቀሱት አካባቢዎች ካለማቋረጥ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ 18 ሺ 628 ቤተሰቦች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአፍሪካ ጋዜጠኞች ማዕከል/ሲ ኤ ጄ/ ዘገባ እንዳመለከተው ከ93 ሺ በላይ ሰዎችን ከቀያቸው ...
Read More »የእሬቻ በአል ላይ የመከላከያ፣የፌደራል ፖሊስና የጸጥታ ሃይል እንደሚሰማራ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) እሁድ በሚከበረው የእሬቻ በአል ላይ የመከላከያ፣የፌደራል ፖሊስና የጸጥታ ሃይል እንደሚሰማራ የፌደራል ፖሊስ ገለጸ። ይህ ውሳኔ የተላለፈው የአባ ገዳዎች ምክር ቤት የታጠቀ የመንግስት ሃይልና ባለስልጣናት በበአሉ ላይ እንደማይገኙ ከገለጸ በኋላ ነው። በመንግስት ዛሬ የተሰጠው መግለጫ የአባገዳዎቹን ውሳኔ የሚሽርና መንግስት ቀደም ሲል ከሰጠው መግለጫ ጋር የሚጋጭ ነው ተብሏል። መግለጫው በበአሉ አከባበር ላይ ውጥረት እንዲነግስ ማድረጉንም ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ...
Read More »በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ከስራቸው ተባረሩ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር በኤምባሲው ሰራተኞች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈጸማቸው ከስራቸው መባረራቸው ታወቀ። በአዲስ አበባ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩት አምባሳደር ኪም ሙንሁዋን የቀረበባቸውን የወሲባዊ ትንኮሳ ድርጊት ሲመረምር የቆየው የደቡብ ኮሪያ መንግስት የዲሲፒሊን ቦርድ በድርጊቱ ተጠያቂ ስላደረጋቸው ከሃላፊነት እንዲነሱ ተወስኗል። ማክሰኞ ከአምባሳደርነታቸው የተባረሩት ሚስተር ኪም ሙንሁዋን በበርካታ የኤምባሲው ሴት ሰራተኞች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈጸም እንዲሁም ...
Read More »በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች ተጽእኖ ስር መውደቃቸው ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010)በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች ተጽእኖ ስር መውደቃቸውንና ለአደጋ መጋለጣቸውን ቢቢሲ ዘገበ። በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር ድርጊቱ አይፈጸምም ሲሉ ማስተባበያ ሰጥተዋል። ሒዩማን ራይትስ ዎች የተባለው አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች የድርጊቱን አሳሳቢነት በተመለከተ በሳምንቱ መጀመሪያ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። የብሪታኒያው የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ የአለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎችን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ባቀረበው ዘገባ የኢትዮጵያ መንግስት ...
Read More »የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ቴክኒክ የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም በማለታቸው ከተቋሙ ተባረሩ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010)የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ቴክኒክ ግቢ የ4ኛና 5ኛ አመት የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም በማለታቸው ከተቋሙ መባረራቸው ተነገረ። በፌደራልና በልዩ ሃይል ተከበው ከግቢ እንዲወጡ የተደረጉት ተማሪዎች ለፈተና ዝግጅት በቂ ጊዜ አልተሰጠንም በማለታቸውና ጥያቄ በማቅረባቸው ተቋሙን ኣእዲለቁ ተገደዋል። ተማሪዎቹ የመማር ማስተማሩን ተግባር ኢዲሞክራሲያዊና ኢፍትሃዊ በሆነ መልኩ አስተጓጉላችኋልም ተብለዋል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የፖሊ ቴክኒክ ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ለፈተና በቂ ጊዜ ይሰጠን ባሉ ጸረ ሰላምና ...
Read More »ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ከ2 መቶ ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ታስረው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ከእስር ተለቀቁ። አቃቢ ሕግ ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ኣንዲለቀቁ ያደረገው በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ እመሰክራለሁ በማለታቸው እንደሆነ ጉዳዩን ለሚከታተለው ችሎት ገልጿል። ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 የስኳር ፕሮጀክት ለዚሁ ተብሎ የተመደበውን በጀት ተቀናሽ በማድረግ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ...
Read More »በእሬቻ በዓል ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ንግግር አያደርጉም ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) ዕሁድ በሚከበረው የእሬቻ በዓል ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ንግግር እንዳያደርጉ መወሰኑን የኦሮሚያ አባገዳዎች ምክር ቤት አስታወቀ። በበዓሉ ላይ መሳሪያ የታጠቀ የመንግስት ሃይል እንደማይኖርም የኦሮሚያ አባገዳዎች ምክር ቤት ማስታወቁንም የቢቢሲ አማርኛው ክፍል ዘግቧል። በበዓሉ ላይ የመንግስት ሰዎች ንግግር እንዳያደርጉና ታጣቂዎች በስፍራው እንዳይኖሩ የተላለፈው የአባገዳ ምክር ቤት ውሳኔ የባለፈው ዓመት ዕልቂት ተጠያቂው ማን እንደሆነ ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው ተብሏል። ለተገደሉት ወገኖች ...
Read More »