በሰሜን ጎንደር ህዝበ ውሳኔ አንፈልግም ባሉት አራት ቀበሌዎች ላይ ውሳኔ ተላለፈ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 21/2010) በሰሜን ጎንደር ህዝበ ውሳኔ አንፈልግም ባሉት አራት ቀበሌዎች ላይ መንግስት ውሳኔ አስተላለፈ። በአንድነት መኖርን እንመርጣለን ባሉት በእነዚህ አራት ቀበሌዎች ላይ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ሁለቱ በቀደመው አስተዳደር ሁለቱ ደግሞ በቅማንት አዲስ መዋቅር ስር እንዲሆኑ ተደርገዋል። ከህዝብ ፍላጎት ውጪ በህወሀት መንግስት ውሳኔ የተሸነሸኑት ቀበሌዎች ጉዳይ በአካባቢው አዲስ ውጥረት እንዲቀሰቀስ ሊያደርግ እንደሚችል እየተነገረ ነው። ህወሀት ውዝግብ የተፈጠረባቸው አካባቢዎች ይላቸዋል። ህዝቡ ...

Read More »

በቤንሻንጉል ካማሽ ዞን በደረሰ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ አለ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 21/2010) በቤንሻንጉል ካማሽ ዞን በደረሰ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ ማለቱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በአካባቢው በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች መፈናቀላቸውም ታውቋል። የችግሩ ሰለባዎችም እስካሁን የሚደርስላቸው አካል እንዳላገኙ ተናግረዋል። የብአዴን ወኪሎች ወደ አካባቢው ቢመጡም ችግሩ ከሚገለጽ ይልቅ ቢሸፋፈን መምረጣቸውን ተፈናቃዮቹ አስታውቀዋል። በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የብሔር ግጭት ለማስነሳት በግለሰቦች ጸብ ስም በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። በክልሉ ካማሽ ዞን ...

Read More »

የኦሮሚያ ክልል ሚዲያ ቦርድ የተሳሳተ መረጃ አስተላልፏል ባለው ጋዜጠኛ ላይ ርምጃ ወሰደ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 21/2010) የትግራይ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ላይ ያቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ የክልሉ ሚዲያ ቦርድ ርምጃ መውሰዱ ተገለጸ። ቦርዱ የትግራይ አስተዳደር ያቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ ዘገባውን በሰራው ጋዜጠኛ ላይ ርምጃ መውሰዱን የገለጸ ሲሆን ስለተወሰደው ርምጃ ግን ያለው ነገር የለም። የትግራይ ክልል መንግስት በጥቅምት 20/2010 በጻፈው ደብዳቤ የኦሮሞ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ/ኦቢኤን/በሚያቀርባቸው ዘገባዎች ላይ በተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ቢያቀርብም ተቋሙም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት አዎንታዊ ምላሽ ...

Read More »

ግሎባል አልያንስ ለኢሉባቡር ተፈናቃዮች የላከው ገንዘብ ለተፈናቃዮቹ እንዳይደርስ ተከለከለ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 21/2010)በቅርቡ በኢሉባቡር ዞን በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች ግሎባል አልያንስ የላከው ከግማሽ ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገንዘብ ለተፈናቃዮቹ እንዳይደርስ ተከለከለ። በመላው አለም በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ለመታደግ የተቋቋመው አለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግሎባል አሊያንስ የኢሉባቡር ተፈናቃዮችን ለመታደግ የላከውን 700 ሺ ያህል ብር ለማድረስ የሄዱት ሰዎች ያለውጤት አካባቢውን እንዲለቁ ተገደዋል። በኢሉባቡር ዞን በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመታደግ አለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ...

Read More »

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 20/2010) የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ያለተቀናቃኝ በተካሄደው የሀገሪቱ 2ኛ ዙር ምርጫ 98 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸናፋቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ ይፋ አደረገ። ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉት የቅርብ ተፎካካሪው ራይላ ኦዲንጋ ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። በነሐሴ ወር በተካሄደው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፈጠሩ በተባሉ ቴክኒካል ችግሮች ምርጫው እንዲደገም ከውሳኔ ላይ መደረሱ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም አሸናፊነታቸው የተሰረዘባቸው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለዳግም ምርጫው ፈቃደኛ ...

Read More »

የሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ በኦሮሚያ ባለው ግጭት ሳቢያ ማምረት አቆመ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 20/2010) ከ16ሺ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉበት የሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ በኦሮሚያ ባለው ግጭት ሳቢያ ማምረት ማቆሙ ተነገረ። በተያያዘ ዜና 5 የዳንጎቴ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች በእሳት እንደጋዩ ለማወቅ ተችሏል። የሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተቃውሞ በሚያሰሙ ወጣቶች ከጥቅምት 14/2010 ጀምሮ በሆለታ ከተማ ተወሮ ምርት እንዲያቆም መገደዱን የአካባቢው ምንጮች አረጋግጠዋል። የሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር መስፍን አቢ ችግሩን ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና ...

Read More »

አቶ በቀለ ገርባ በዋስ እንዲፈቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 20/2010)የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በዋስ እንዲፈቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ። ነገ ከወህኒ ይወጣሉም ተብሎ ይጠበቃል። የወህኒ ቤቱ ሃላፊዎች አንዳንዴ ከህግ በላይ ስለሚሆኑ የሚሆነውን እናያለን፣አባቴ በዋስትና በመፈታቱ ግን እፎይታ ተሰምቶኛል ስትል ልጃቸው ቦንቱ በቀለ ለአዲስ ስታንዳርድ አስተያየቷን ሰጥታለች። በኦሮሚያ ክልል ከተካሄደው አመጽ ጋር በተያያዘ በታህሳስ 2008 ወደ ወህኒ የወረዱት አቶ በቀለ ገርባ ከታሰሩ ከአንድ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው የፖለቲካ ድባብና ቀውስ ሀገሪቱን ወደ መበታተን እንዳያመራት ያሰጋል ተባለ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 20/2010)ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው የፖለቲካ ድባብና ቀውስ ሀገሪቱን ወደ መበታተን እንዳያመራት ያሰጋል ሲሉ አንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ተናገሩ። ፓርቹጋላዊቷ የአውሮፓ ፓርላማ አባል አና ጎመሽ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ግጭትና የሕወሃት አገዛዝ እየተከተለ ያለው አካሄድ አስቸኳይ መፍትሄ ካልተሰጠው በሀገሪቱ ከፍተኛ ቀውስ እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድን ሊያውክ የሚችል ግጭት ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል። አሜሪካና አውሮፓ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምህላ አወጀ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 20/2010) በአቡነ ማትያስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የ14 ቀናት ጸሎተ ምህላ እንዲታወጅ ወሰነ። ቅዱስ ሲኖዶሱ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱትን ግጭቶች በመጥቀስ ስለሀገራችን ሰላምና የህዝብ አንድነት መጠበቅ ሲባል ጸሎተ ምህላው እንዲታወጅ መወሰኑን አስታውቋል። ከመንግስት ጋርም በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ለመነጋገር በሲኖዶሱ በኩል ውሳኔ ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል። ቅዱስ ሲኖዶሱ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በመላ ሀገሪቱ የ14 ...

Read More »

በመከላከያ ሰራዊት ርምጃ በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ሰዎች እየተገደሉ መሆናቸው ቁጣን ቀሰቀሰ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 20/2010)በመከላከያ ሰራዊት ርምጃ በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ሰዎች እየተገደሉ መሆናቸው በነቀምት ከተማ የሕዝብ ቁጣን እየቀሰቀሰ መሆኑ ተነገረ። በኦሮሚያ በአንድ ሳምንት ብቻ 30 ሰዎች ሲገደሉ 37 ደግሞ ቆስለዋል። በአምቦ የመከላከያ ሰራዊት በሕዝብ ላይ በከፈተው ተኩስ ግንባራቸውንና ልባቸውን ተመተው የተገደሉ መኖራቸውን የከተማዋ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ ገልጸዋል። በነቀምት በተነሳ ሕዝባዊ ተቃውሞም 3 ሰዎች በአካባቢው ነዋሪዎች መገደላቸው ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ...

Read More »