በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የድረሱልን ጥሪ አሰሙ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 23/2010)በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸውና በረሃ አቋርጠው በሊቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን አደጋ ውስጥ በመሆናቸው አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። ከ200 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሊቢያ የገቡት ባለፉት 10 ወራት ሲሆን በረሃ ላይ ጓደኞቻቸውን በሞት እንዳጡ በስልክ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረስልንም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ከጎንደር፣ ከአዲስ አበባ፣ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተሰደዱት ...

Read More »

የአሜሪካ ምክር ቤት ኤች አር 128 ሕገ ውሳኔን በአስቸኳይ እንዲያጸድቅ ማይክ ኮፍማን ጠየቁ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 23/2010)ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እንዲከበር እንዲሁም ሁሉን አቀፍ መንግስት እንዲቋቋም የሚጠይቀውን ሕገ ውሳኔ የአሜሪካ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲያጸድቅ የኮሎራዶ ተወካይ የሆኑት ማይክ ኮፍማን ጠየቁ። ማይክ ኮፍማን ትላንት በምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ምክር ቤቱ ሕገ ውሳኔውን እስካሁን ማዘግየቱ እጅግ ያሳዘናቸው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። በኮሎራዶ የ6ኛው የምርጫ ክልል ተወካይ የሆኑትና ከኢትዮጵያውያን ጋር በሰብአዊ መብትና ...

Read More »

በኒዮርክ በደረሰው የሽብር ጥቃት 8 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010) በኒዮርክ ትላንት አንድ ግለሰብ የእቃ መጫኛ መኪናን በመጠቀም ባደረሰው ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲሞቱ ከ10 በላይ ቆሰሉ። የሽብር ጥቃት ነው በተባለው በዚህ አደጋ ህይወታቸውን ካጡት መካከል ለጉብኝት የመጡ አምስት አርጀንቲናውያን ጓደኛሞች እንደሚገኙበት ታውቋል። ጥቃቱን የፈጸመው የ29 አመቱ ኡዝቤክስታናዊ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ቆስሎ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። የትላንቱን የኒዮርክ ጥቃት የ29 አመቱ የኡዝቤክስታን ተወላጅ የተከራየውን የእቃ መጫኛ መኪና ሰዎች በቢስኪሌት ...

Read More »

በአስመራ ለተቃውሞ የወጡ ተማሪዎች በፖሊስ ተኩስ ተበተኑ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)በአስመራ ከተማ ለተቃውሞ የወጡ ተማሪዎች በፖሊስ ተኩስ መበተናቸው ተዘገበ። በከተማዋ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት ለዜጎቹ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል። የተቃውሞው መነሻ የኮሚኒቲ ትምህርት ቤቶችን ወደ ሕዝብ ትምህርት ቤት ለመቀየር ከተያዘ ዕቅድ ጋር የተገናኘ መሆኑም ተመልክቷል። በተኩሱ የሞተም ሆነ የቆሰለ አለመኖሩ ታውቋል። የኤርትራ መንግስት ከሶስት አመት በፊት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደውን የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶችን ወደ ሕዝብ ትምህርት ቤት የመቀየር ርምጃ ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲና አረና ትግራይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)ሰማያዊ ፓርቲና አረና ትግራይ ሰላማዊ ሰልፎች መጥራታቸው ተገለጸ። ሰማያዊ በአዲስ አበባ፣ አረና ደግሞ በመቀሌ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድና ቅዳሜ የሚካሄዱ ናቸው። የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ ለኢሳት እንደገልጹት ‘’ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት” በሚል ርዕስ የተጠራው ሰልፍ እሁድ ጥቅምት 26/2010 በመስቀል አደባባይ ለተጠራው ሰልፍ የማሳወቂያ ደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ቀርቧል። በህጉ መሰረት የማሳወቅ ግዴታው መከናወኑን የጠቀሱት አቶ ጌታነህ ...

Read More »

የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ በላይኛውና በታችኛው ካድሬ አጀንዳ አለመስማማት ተራዘመ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)በአዳማ እየተካሄደ ያለው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ በላይኛውና በታችኛው ካድሬ አጀንዳ አለመስማማት ተራዘመ። በጉባኤው የግል ስልክን ጨምሮ ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ እንዳይገባ ጥብቅ ፍተሻ ተደርጓል። እሁድ ጥቅምት 19/2010 በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በአንድ ቀን ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራርና የጉባኤው ተሳታፊዎች መካከል መግባባት ባለመቻሉ እስከ ጥቅምት 23 ድረስ ሊራዘም መቻሉን የኢሳት የውስጥ ምንጮች አስታውቀዋል። የጉባኤው ...

Read More »

በኢሉባቡር ለተፈናቀሉ ወገኖች የተሰበሰበ የእርዳታ ገንዘብ ታገደ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)በኢሉባቡር መቱ ከሳምንት በፊት በተነሳ ግጭት ለተፈናቀሉና በመጠለያ ጣቢያ ለሚኖሩ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ በተቋቋመ ኮሚቴ አማካኝነት የተሰበሰበ የእርዳታ ገንዘብ ከደህንነት መስሪያ ቤት በወጣ ቀጥተኛ ትዕዛዝ መታገዱ ተሰማ። ከ1500 በላይ ለሚሆኑት ለነዚህ ተፈናቃዮች የተሰበሰበው ገንዘብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 4 ኪሎ ቅርንጫፍ በተከፈተ ሒሳብ ቁጥር የተቀመጠ መሆኑም ታውቋል። በ4 ቀን ውስጥም ከ100 ሺ ብር በላይ መሰብሰቡንም የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ኮሚቴዎቹ ...

Read More »

አቶ በቀለ ገርባ በዋስትና እንዲወጡ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ ታገደ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በቀለ ገርባ በዋስትና እንዲወጡ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ ታገደ። በእስር ቤት እንዲቆዩም ተወስኗል። ርምጃው የተወሰደው ቤተሰቦቻቸው የተጠየቀውን ዋስትና አሟልተው ይፈታሉ ብለው በሚጠብቁበት ወቅት እንደሆነም ታውቋል። የአቶ በቀለ ዋስትና መታገዱን ይፋ ያደረገው የሕወሃቱ ኢፈርት ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና ነው። ሰኞ ጥቅምት 20/2010 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ30 ሺ ብር ዋስትና ጠርተው እንዲወጡ ...

Read More »

የካታላኑ መሪ ከ5 ሚኒስትሮቻቸው ጋር ከሀገር ተሰደዱ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 21/2010)ከስፔን በመገንጠል ነጻነቷን ያወጀችው ካታላን መሪ ከ5 ሚኒስትሮቻቸው ጋር ከሀገር ተሰደዱ። ስፔን ግዛቲቱን በመቆጣጠር የሀገሪቱን ባላስልጣናት በአዲስ መሪዎች የተካች ሲሆን የካታላን የራስ ገዝ መብትም ለጊዜው ታግዷል። ሙሉ በሙሉ የስፔን ግዛት ሆና እንድትቀጥል የሚያስችሉ ርምጃዎችም ተጠናክረው ቀጥለዋል። ባለፈው አርብ የካታላን ነጻነትን በይፋ መታወጅ ተከትሎ ቤልጂየም ብራስልስ የደረሱት የካታላን መሪ ካርለስ ፑጂሞንት ነጻነት ያወጁበትን ሀገር ጥለው ከሀገር ስለመውጣታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ...

Read More »

በህገወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የሚወጣው የአሜሪካን ዶላር እየተባባሰ ነው

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 21/2010)በህገወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የሚወጣው የአሜሪካን ዶላር እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ። በተለይ የብር የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በ15 በመቶ እንዲቀንስ ከተደረገ በኋላ ወደ ውጭ በህገወጥ መንገድ የሚወጣው ገንዘብና ገንዘቡን ለማውጣት የሚሞክሩ ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ታውቋል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችም ከኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የሚወጣው ገንዘብ በአመት ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ መድረሱን አረጋግጠዋል። የብር የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በ15 በመቶ እንዲቀንስ ከተደረገ በኋላ ወደ ...

Read More »