(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) ለሁለት ሳምንት ያህል ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ መቋረጡ ተገለጸ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም አሜሪካ መግባታቸው ታወቋዋል። በሌላ በኩል የኦህዴድና የብአዴን የፓርላማ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ካላነጋገርናቸው በፓርላማ መደበኛ ሰብሰባ ላይ እንደማይገኙ ማሳሰባቸውን ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን የፓርላም አባላቱን ማነጋገራቸው ታውቋል። የኦህዴድና የብአዴን የፓርላማ አባላት በህዝበ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና በሐገሪቱ ውስጥ ...
Read More »ሕወሃት ተቃውሞዎችን ለማፈን የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) የህወሃት መንግስት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ለማፈን የማይችልበት ደረጃ ላይ መደረሱ ተገለጸ። በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተነሱትን ተቃውሞዎች ለመቆጣጠር ከድንበር ሰራዊቱን እያንቀሳቀሰ መሆኑም ተገልጿል። የአባይን ግድብ የሚጠብቀው የህዳሴ ዲቪዥን በመባል የሚጠራው የፌደራል ፖሊስ አንድ ሻለቃ ጦር በአማራ ክልል በዩኒቨርስቲዎች የተነሳውን ተቃውሞ ለማስቆም ከግድቡ መንቀሳቀሱም ታውቋል። አገዛዙ የሰራዊት እጥረት በመግጠሙም የትግራይ ሚሊሻዎችና ደህንነቶችን የፌደራል ፖሊስ ዩኒፎርም ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተከሰተውን ግጭት ለማባባስና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ። በሕወሃቱ አመራር አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት መስሪያ ቤት ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ በሰፊው በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑንም መረጃዎች አመልክተዋል። ይህንን ለማስፈጸም የፓርቲና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም የመዝናኛ ጣቢያ ጋዜጠኞችን ጭምር የጉዞና የውሎ አበል ከፍሎ ማሰማራቱን መረዳት ተችሏል። የሕወሃት ተቋማት ከሆኑት ኢ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ...
Read More »የላይቤሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) የላይቤሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ተካሄደ። ባለፈው ጥቅምት በተካሄደው ምርጫ 50 በመቶ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ ባለመኖሩ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ተደርጓል። በምርጫው ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃና ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጆሴ ቦአካይ ዋና ተፎካካሪዎች መሆናቸው ታውቋል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከአሜሪካ ከባርነት ነጻ በወጡ አፍሪካውያን የተመሰረተችው ላይቤሪያ ላለፉት 73 አመታት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጎባት አያውቅም። የአሁኑ ምርጫ ከአንድ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲባረሩ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) ማላዊ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ 22 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲባረሩ ተወሰነ። ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ከሀገር እንዲባረሩ የተወሰነው ጉዳያቸውን በተመለከተ የሚያግዛቸው አስተርጓሚ በመጥፋቱ እንደሆነም ተመልክቷል። በሌላ ዜና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ 5 ኢትዮጵያውያን በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን አፍሪካ ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል። ማላዊ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገብታችኋል በሚል በቁጥጥር ስር የዋሉት 22 ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የማላዊው ጋዜጣ ናይሳ ...
Read More »ሃይለማርያም ደሳለኝ በፖሊስ ታስረው እንዲቀርቡ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በፖሊስ ታስረው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡላቸው አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤቱን ጠየቁ። አቶ ሃይለማርያም በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት በፍርድ ቤት ቢጠሩም ሕጉን አክብረው ግን አልተገኙም። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አቶ ሃይለማርያም በስራ መደራረብ ለምስክርነት መቅረብ እንዳልቻሉ ለፍርድቤቱ ደብዳቤ ፅፏል። በዚህ የክስ መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ግን አቶ ሃይለማርያምን ...
Read More »የበይነ መረብ ዘመቻ ሊካሄድ ነው
(ኢሳት ዲሲ –ታህሳስ 17/2010) የህሊና እስረኞችን ለማስታወስ ነገ የበይነ መረብ ዘመቻ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ። በሀገር ቤት የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎችና ጋዜጠኞች በጋራ ያዘጋጁት የበይነ መረብ ዘመቻ በተለያዩ ወህኒ ቤቶች የሚገኙ የህሊና እስረኞች ስቃይ እየተባባሰ መምጣቱን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል። ለአንድ ቀን በሚደረገው በዚሁ ዘመቻ እስረኞቹ ብቻቸውን እንዳልሆኑ ለማሳየት መሆኑም ተገልጿል። በማህበራዊ መድረኮች በፌስ ቡክና ቲውተር ዘመቻው እንደሚካሄድም ...
Read More »አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ እየተጠበቀ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል የአገዛዙ የደህንነት ሃይሎች ግቢውን በአይነቁራኛ እየተከታተሉ መሆናቸው ተነገረ። በዩኒቨርስቲው ትላንት ተቃውሞ ለመጀመር ተማሪዎች ቀጠሮ ይዘው እንደነበር ይነገራል። የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ሊመሩ ይችላሉ የተባሉ ተማሪዎች በጥርጣሬ ብቻ እየታፈኑ በፒካፕ ተሽከርካሪ ወደ ማጎሪያ ቦታ መወሰዳቸው ተነግሯል። ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲቪል የለበሱ በርካታ ፖሊሶች መግባታቸውንም የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል። የሕወሃት አገዛዝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ...
Read More »የፓርላማ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) በኢትዮጵያ በተፈጠረው ቀውስ ላይ ማብራሪያ ካልተሰጠን በመደበኛ ስብሰባ አንገኝም ያሉት የፓርላማ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ። በዝግ ለ3 ሰአታት በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ 4ቱ የኦሮሚያ፣የአማራ፣የትግራይና የደቡብ ፕሬዝዳንቶች ከአቶ ሃይለማርያም ጋር መገናኘታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአሜሪካ የሚገኘውን አይጋ ፎረም የሕወሃት ድረ ገጽ ጠቅሶ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ከፓርላማ አባላቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከተጠየቁ በኋላ ምላሽ ሳይሰጡ ሲያቅማሙ መቆየታቸው ታውቋል። በስተመጨረሻ ...
Read More »በዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሙሉ በሙሉ ትምህርት ማቆሙ ተገለጸ። በአዳማ ዩኒቨርስቲ ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ ትምህርት ተቋርጧል። በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ዓርብ በተነሳው ተቃውሞ የህንጻዎች መስታወት መሰባበሩንም ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በትግራይ ልዩ ሃይልና በአማራ ልዩ ሃይል መሃል ቅዳሜ ዕለት የትኩስ ልውውጥ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በአሶሳ ዩኒቨርስቲም ተቃውሞ ተጀምሯል። በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የታሰሩ ተማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታውቋል። ከ10ቀናት ...
Read More »